የአማራ ሃይሎች አንዲት ነፍሰ ጡር ኦሮሞ ሴት አንገት ቀልተው ሲገድሉ 18 ተማሪዎችን ደግሞ አፍነዋል::
(የኦነግ-ኦነሠ ጋዜጣዊ መግለጫ)
በአብይ አህመድ እና በአማራ ታጣቂዎች በኦሮሞ ህዝብ ላይ የታወጀው የዘር ማጥፋት አሁንም በሰፊውና በሙሉ ሀይሉ ቀጥሏል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ሃይል እና ፋኖ የሚባሉ መንግስታዊ አሸባሪ ሃይሎች የወንጀል አውድማቸው እያደረጉት ሲሆን እነዚህ ሃይሎች ይህን ክልል የንፁሀን ኦሮሞዎች፣ የትግራይ ተወላጆች እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተወላጆች የጅምላ መቃብር ስፍራ ከሆነ ውሎ አድሯል።
እነዚህ የአማራ ልዩ ሃይል እና የፋኖ ታጣቂዎች ንፁሀን ዜጎችን እጨፈጨፉ እና የተጎጂዎችን ንብረት በጠራራ ፀሐይ እየዘረፉ መሆናቸውን ደጋግመን የገለፅን ቢሆንም ይህ መንግስታዊ አሸባሪነት ከመሻሻልና ከመቀነስ ይልቅ አሰቃቂና አሳሳቢ እየሆነ ቀጥሏል።
ማክሰኞ መጋቢት 15 ቀን 2022 (እኤአ) ብርሃኔ ረጋሳ የተባለች ነፍሰ ጡር የኦሮሞ ሴት እና የሰባት ልጆች እናት በሌላ የድንጋይ ዘመን አረመኔያዊ እርምጃ ጉሮሮዋን በስለት በመታረድ በአሰቃቂ ሁኔታ በአማራ ታጣቂዎች መገደሏን አረጋግጠናል። ይህ የፈሪዎች አረመኔያዊ ድርጊት የተፈፀመው በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዲባጤ ወረዳ ሲሆን ከሁለት ቀን በኋላ እንዲሁ መጋቢት 17 ቀን 2022 ጠዋት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ እነዚሁ የአማራ ወራሪና ተስፋፊ ሀይሎች አስራ ስምንት የኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎችን አግተው ወስደዋል። አፈናው የተፈፀመው በቤኒሻንጉል ዲባጤ ወረዳ ቢሻን አዲ እየተባለ በሚጠራው ቦታ ሲሆን ከአስራ ስምንቱ ታፍነው ከተወሰዱት መካከል 12ቱ እንደሚከተለው በስም ተለይተው ታውቀዋል። እነሱም:-
1ኛ. ኮልቴ ፈይሳ
2ኛ. ታረቀኝ አርጋታ
3ኛ. ደበላ ሥዩም
4ኛ. ረጋሳ ባጎንጆ
5ኛ. ጃቤሳ ተሾመ
6ኛ. ጌጤ ከበደ
7ኛ. አያንቱ ገመቹ
8ኛ. ሃይሌ በሴ
9ኛ. እመቤት ጋሮማ
10ኛ. ከፍያለው ዋቅጅራ
11ኛ. ጃለኔ ገመቹና
12ኛ ፈይሳ መኮንን ሲሆኑ እነዚህ ታጋቾች ያሉበት ቦታና ሁኔታ እስካሁን አልታወቀም::
በቅርቡ በዚሁ አካባቢ የአብይ አህመድ የጸጥታ ሃይሎች እና የወንጀል አጋራቸው የአማራ ልዩ ሀይል ዘጠኝ የትግራይ ተወላጆችን ግማሹን ገድለው ሌላውን በህይዎት እያለ በእሳት አቃጥለው በመግደል ማመን የሚያስቸግር አረመኔያዊ ድርጊት መፈፀማቸው የሚታወስ ነው::
አለም አቀፉ ማህበረሰብ በየትኛውም አካባቢ የሚኖሩ ሰላማዊ ዜጎችን የሰብአዊ መብት የመጠበቅና የማስጠበቅ ሃላፊነት አንዳለበት በመረዳት ይህን በአብይ አህመድ መንግሥትና የአማራ የጸጥታ ሃይሎች የሚፈፀመውን በሰብአዊነት ላይ የሚፈፀም ወንጀልእንዲያወግዝና ተግባሩንም በመንግስታዊ ሽብር (state terrorism) እንዲፈርጅ አጥብቀን እያሳሰብን ከላይ የተጠቀሱት ታጋቾች አንድም ጉዳት ሳይደርስባቸው ተለቀው ወደቄዬአቸው እንዲመለሱ አስፈላጊውን ጫና እንድታደርጉ እንጠይቃለን።
በተጨማሪም በዚህ አሸባሪ መንግሥት ቁልፍ የደህንነት: ወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መሠረተ አውታሮችና መሪዎቻቸው ላይ ትርጉም ያለው ማዕቀብ በመጣል ይህ ፀረ ህዝብ መንግሥት ወንጀሎቹን የሚደጉምበትን የገንዘብ አቅም በማዳከም ‘በራሱ’ ዜጎች ላይ የሚፈፅመውን የሽብር ተግባር እንዲያስቆም የኦነግ – ኦነሠ ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ በአንክሮ ይጠይቃል። በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደህንነት ላይም ትልቁ ስጋት አብይ አህመድ እና የአማራ አሸባሪ ቡድኖች መሆናቸውን አለማቀፉ ማህበረሰብ ማወቅ እንዳለበት ቅድመ-ማስጠንቀቂያችንን ልንሰጥ እንወዳለን።
በመጨረሻም በሕዝባችን ሰብአዊነትና ሁለንተናዊ ክብር ላይ የሚፈፀመው ግፍና በደል አስፈላጊውን ምላሽ ሳያገኝ የማይቀር መሆኑን ህዝባችን በእርግጠኝነት እንዲያውቀው እያሳሰብን የፈለገውን ጊዜ ቢፈጅና መስዋዕትነት ቢጠይቅም እነዚህ ወንጀለኞች ከፍትሕ እንደማያመልጡ ኦነግ-ኦነሠ በድጋሚ ያረጋግጣል::
ፍትሕ ለተጎዱት!!
ድል ለኦሮሞ እና ለተጨቆኑ ህዝቦች በሙሉ!
የኦነግ-ኦነሠ ከፍተኛው ዕዝ
ማርች 18፣ 2022

