Site icon Qeerroo Bilisummaa Oromoo

ነፃ ኦሮምያን ለማረጋገጥ ዛሬ በሁሉም አቅጣጫ ትግል ማድረግ የሁሉም ኦሮሞ ድርሻ ነው – (የኦሮሞ ወጣቶች ማህበር (ቄሮ) መግለጫ)

ነፃ ኦሮምያን ለማረጋገጥ ዛሬ በሁሉም አቅጣጫ ትግል ማድረግ የሁሉም ኦሮሞ ድርሻ ነው::

(የኦሮሞ ወጣቶች ማህበር (ቄሮ) መግለጫ) 18/7/22

ኦሮሞ በባርነት ሥር ከወደቀበት ጊዜ አንሥቶ አንድም ጊዜ ትግሉን አላቋረጠም:: ትግሉን አጠናክሮ በቀጠለ መጠን ጠላቱም የጭካኔው ልክ በሰው ልጅ ላይ የማይደረግንና በታሪክ ውስጥ የማይረሳ ከጊዜ ወደ ጊዜ ግፍና ስቃይ በእሮሞ ላይ እየጨመረ መቷል::

ኦሮሞ ላይ ይህ ግፍና ሥቃይ እንዳይለየው ካደረጉት ነገሮች ውስጥ ኦሮሞ መስለው ለጠላት መሥራት እንዲሁም ኦሮሞ በባርነት ሥር መኖሩን አለማወቅ ነው::

ለዘመናት በተበታተነ መንገድ በተለይ የኦሮሞ የነፃነት ትግል አጋር ማፍራት የራስን ወገን ማካተት እስከዛሬ ቢሄድም ነገር ግን በተፈጠሩ ስህተቶችና ጥፋቶች ህዝባችን ድል በጠላቶቻችን በመጠለፉ በአዲስ መልክ ባህሪውን ቀይሮ ለሌላ ሁለተኛ ዙር ባርነት ሥር ወድቋል:: አንዳንድ ኦሮሞዎችም ምንም የተጠለፈ ድል እንደሌለ እና ኦሮሞ ወደ ግቡ እንደሚደርስ ዛሬም የምያምኑ ያሉ በርካቶች ናቸው::

ዛሬም ኦሮሞ፣ ኦሮሞ በመሆኑ ብቻ ቀን በቀን እያለቀሰና እየተሰቃየ ከመኖር በታች ሆኖ እየንረ ነው:: ይህንን 4 ዓመታት ለየት ባለ መልኩ “አድስ ሥርዓት መሬት ለማስያዝ” በሚል በኦሮሞ መንደር ሀዘን ያልሆነበትና የሀዘን ድንኳን ያልተጣለበት የለም:: በዚህ ሥርዓት ውስጥ ባልና ሚስት በአንድ ላይ ይገደላሉ፣ በጅምላ አንድን ቤተሰብ፣ ሰላማዊ ሰዎችን በጅምላ መፍጀት፣ በአባትና እናት ፊት ሴት ልጃቸውን መድፈር፣ ባል እያየ ሚስትን መድፈር፣ የኦሮሞን ቤትና ንብረት ማቃጠል፣ የኦሮሞን መሬት መውረር፣ አባ ገዳዌችን መግደል፣ በአጎራባች ክልሎች ውስጥ ኦሮሞን እንደ ጠላት እንዲታይ ማድረግ፣ ኦሮሞን በጅምላ በየእሥርቤቶች ውስጥ ማሠቃየት፣ የኦሮሞ እሥረኞችን ከእሥርቤት አውጥቶ መረሸን…..ያልተዘረዘሩና መናገር የሚከብዱ በርካታ ነገሮች በኦሮሞ መንደር ተፈጽመዋል:: ይህ ውርደትና መስዋዕት የሚፈጽመው አፋን ኦሮሞ የሚያወራና ኦሮሞ መሆኑን በሚናገር ሰው ነው::

ኦሮሞ ከገበያውና ምርትን ከማምረት ከተገለለ ሰነባብቷል:: የኦሮሞ ገበሬ አመቱን ሙሉ ያመረተውን ምርት በግብር ምክንያት ቤቱንና መንደሩን ኦና አድርጎም ከዕዳ ነፃ መሆን አቅቶታል:: የተቀረው ደግሞ እንዳያመርት ተደርጎ ለረሀብ እንዲጋለጥ ተደርጓል::

ይሁ ሁሉ ችግር መፍትሄ ማግኘት የሚችለው በኦሮምያ ነፃነት ብቻ ነው:: የእሮሚያ ነፃነት ደግሞ መራራ ትግል የሚካሄድበትና ሺዌች የተሰለፉለት የራስን ደምና አጥንት መስዋዕት እየከፉሉበት ባለው እውን ይሆናል::

መበርታትና በአንድ ኃሳብ በመጓዝ ይህ የኦሮሞ የነፃነት ትግል ጠላቶችንን እንዲሁም ወዳጅ መስለው ጠላቶቻችንን ሆድ አስብሷል:: አብዛኛው እረፍት አተው ለመጨረሻ ጊዜ ለመጠቀም ውዥንብርና ጦራቸውን በአንዴ በማሰማራት ትግሉን ለማቀጨጭ እየሠሩም ነው::

እኛ ማሳየት ያለብን የኦሮሞ የነፃነት ትግል ምንም ያህል ከባድ ቢሆንም የሚጠይቀውን መስዋትዕትነት የሚከፈለው ተከፍሎ ግቡ ጋር መቅረባችንና መጨረሻው መድረሱ ነው:: በቀላሉ እዚህ አልደረስንም:: ከዚህም በኋላ በቀላሉ አንዘጋውም፤ ይበልጥ መጠንከርና መዘጋጀት እንዳለብን ያስገነዝበናል:: ረጅም እረቀት ሄደናል የቀረን ደግሞ በጣም አጭር መሆኑን መገንዘብ ጥሩ ነው:: ስለዚህ ጠላቶቻችን በእያንዳንዱ የኦሮምያ ጓዳዎች ውስጥ በባዕድ ወራሪዎችን በማሰማራት የማይረሳ ትላልቅ ጠባሳ እኛ ጋር የሚታወሱ እሮሚያ ለማፍረስና ታሪክ ለማድረግ ቀንና ሌሊት እየሠሩ ይገኛሉ::

ለዚህ ደግሞ ያለው ማስረጃ የነፍጠኛው ሚሊሻ፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖን ጨምሮ የሌሎች ክልሎችን ኃይሎች በምዕራብ ኦሮሚያ (ቄሌም ወለጋ፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ምሥራቅ ወለጋ፣ ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ ሸዋ) በማዕከላዊ ኦሮሚያ (ሰሜን ሸዋ፣ ምሥራቅ ሸዋና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ) ውስጥ በማሰማራት የኦሮሞን ልጅ በመግደል የኦሮሞን መንደር ንብረት በማውደም ላይ መሆናቸው ብቻ ማሳያ ነው::

ከቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ የተሰጠ መግለጫ፦

እንደ ኦሮሞ ነፃነት ትግል ወደ ግቡ እየቀረበ ሲሄድ ጠላቶቻችን ይበልጥ ተጠናክረው የመጨረሻውን ፍልሚያ እያደረጉ እኛ በኃይል ጠንክረን ከነበረን በላይ በርትተን መፋለማችን አስበርግጓቸው የሚይዙትንና የሚጨብጡትን አሳጥቷቸዋል:: ስለዚህ እኛ ማብቂያውን ማድረግ አለብን:: ለዛ ደግሞ የኦሮሞ ነፃነት ጦር በኦሮሚያ ውስጥ ጠላትን ፊት ቆም በመፋለም ላይ ባለበት ሰዓት ይህ ትግል የሚፈልገውን መስዋትነት በመክፈል ከጎን መቆም አለብን እንላለን::

የኦሮሞ ህዝብ በውስጥና በውጪ የዚህን ትግል ጉዳይ በበሰለ መንገድ በመያዝ ሌላ አካል ትግሉን ነጥቆ እንደገና አላስፈላጊ መስዋዕትነት ልጆቹ እንዳይከፍሉ አጥብቆ መጠበቅ አለበት:: በዚህ ላይ የትግሉ ባለቤት ራሱ እንደሆነ ማረጋገጥ አለበት እንላለን::

የኦሮሞ ልጆች በጠላት መንደር ውስጥ ቆማችሁ እየሠራችሁ፣ የወጣችሁበትን ህዝብ እየገደላችሁ፣ ቤት ንብረቱን እያቃጠላችሁ፣ እየደፈራችሁ፣ ከእሥር ቤት አውጥታችሁ እየገደላችሁ በምድር ላይ ለሰው ልጅ የማይፈጸሙ ግፎችን እየፈጸማችሁ ላላችሁ መልዕክት አለን:: እንደፈለገ ቢሆን የኦሮሞ ህዝብ ድል እና የኦሮሚያ ነፃነት የማይቀር ጉዳይ ነው:: ግን እናንተ እንደ አንድ ግለሰብ የወጣችሁበትን ህዝብ ግፍ እየሠራችሁበት ያላችሁበትን ህዝብ እረፍት ስጡት:: በኦሮሞ ነፃነት ትግል ውስጥ ተቀላቅለህ ከአንድ ኦሮሞ ልጅ የሚጠበቅብህን እንድትወጣ ለመጨረሻ ጊዜ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን:: ኦሮሞ ሆነህ በመከላከያ፣ የኦ.ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ደህንነት አባላት የሆናችሁ ህዝባችሁን መከራ ከታችሁ ካላችሁበት ሁኔታ አንድ ጊዜ ቆም ብላችሁ የኦሮሞን ደም ከማፍሰስ ለመጨረሻ ጊዜ እንድትቆጠቡ:: ነገ ከታሪክ ተጠያቂነት እራሳችሁንና ቤተሰባችሁን እንድትታደጉ አስረግጠን እናሳስባለን::

የወሎ እና የመተከል ህዝባችንን ከኦሮሞና ኦሮሚያ በመነጠል የግፍን ጥግ እያየ ይገኛል:: እንደ ኦሮሙማ ሌላው ኦሮሚያ ከሚከፍለው በተጨማሪ ማንነቴንና መሬቴን ለአንተ ሰጥቼ አልጠፋም በማለት ኦሮሞና ኦሮሚያ ከሚያየው በላይ እያየ ይገኛል:: ስለዚህ ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ ለወሎና ለመተከል ህዝባችን ታግለን አምባገነኑን ሥርዓት ገልብጠን የኦሮሞን ህዝብ ዕድል ወደ አንድ ቦታ ይመለሳል የምንለውን የምናይበት ጊዜ እረቅ አይሆንም:: መላው የኦሮሞ ህዝብ በውስጥና በውጪ የሚገኘው ህዝባችን የወሎና የመተከል ዋጋ እየከፈለ ያለው ወገኑን የሚያስፈልገውን መስዋዕትነት ሁሉ በመክፈል ከጎኑ መሆን እንዳለበት ማወቅ አለበት::

ባሌ ዞን ጉረ ደሞሌ ወረዳ ውስጥ አንባ ገነኑ መንግስት ከሀገር መከላከያ እና የሱማሌ ልዩ ኃይል የሶማሌ ሚልሻን ጨምሮ በህዝባችን ላይ በከፈተው ውጊያ ከአከባቢው እንዲፈናቀል የአምባገነኑ መንግሥት እንደምለው ህዝቡ በፍላጎቱ የሚፈናቀል አድርጎ እያወራ ቢሆንም ያለው ሀቅ ግን ጦርነት ተከፍትበት የተፈናቀለ መሆኑ ነው:: የሱማሌ ልዩ ኃይል ተሳትፎ በህዝባችን ላይ በከፈተው ውጊያ ከአከባቢው እንዲፈናቀል የአምባገነኑ መንግሥት እንደምለው ህዝቡ በፍላጎቱ የሚፈናቀል አድርጎ እያወራ ቢሆንም ያለው ሀቅ ግን ጦርነት ተከፍትበት የተፈናቀለ መሆኑ ነው::

የመጨረሻ መልዕክት፦

ኦሮሞ በየትኛውም ወሬ ግራ ሳይጋባ ነቅቶ አንድነቱን ጠብቆ የኦነግ/ኦነሠ እያካሄደ ባለው ትግል በመደገፍ ይህንን የዘመናት ባርነት ታሪክ እንዲያደርገው መልዕክት እናስተላልፋለን:: ቤታችን የሚገለን ጠላት ቁጭ ብለን ከማየት ያለን ብቸኛ አማራጭ ከኦነሠ ጋር በመሆን ታግለን እንድናሸንፍ እናሳስባለን::

ድል ለኦሮሞ ህዝብ 18/7/22

ፊንፊኔ, ኦሮሚያ

Exit mobile version