Site icon Qeerroo Bilisummaa Oromoo

በአብይ አህመድ መራሹ የብልጽግና ሰራዊት ቡድንና በአማራ ጽንፈኞች ቡድን ፋኖ በሰሜን ኦሮሚያ፣ በወሎ ኦሮሞዋች ላይ የተከፈተዉ የዘር ማጥፋት ጦርነት ተጠናክሮ ቀጥሏል 

መጋቢት 20/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

አብይ አህመድ መራሹ የብልጽግና ቡድን ሲያደራጅና እስከ ዛሬም ትጥቅ ከሚያቀርብለት ራሱን ፋኖ ብሎ ከሚጠራው ከአማራ ጽንፈኞች ቡድን ጋር ትብብሩን አጠናክሮ ቀጥሏል። የወሎ ኦሮሞዎች ከፊት ራሱን ፋኖ ብሎ ከሚጠራው የአማራ ጽንፈኞች ቡድን የተከፈተባቸዉን ጥቃት ለመመከት ጥረት እያደረጉ ባሉበት ሁኔታ አጋጣሚውን በመጠቀም ከኋላ በማጥቃት ለዚህ ጽንፈኛ ቡድን  አጋርነቱን እያሳየ ነዉ።

ይኽውም የሆነው መጋቢት 17/2024 ከቀኑ ስድስት ሰዓት ጀምሮ ህዝባችን ከፊት ራሱን ፋኖ ብሎ ከሚጠራው ከአማራ ጽንፈኞች ቡድን የተከፈተበትን ጦርነት በመከላከል ላይ ሳለ ለህዝባችን እገዛ ለመስጠት የመጣ በማስመሰል ኦሮሞ-ጠሉ የአብይ ቡድን ከኋላ በመኪና ጭኖ ያስከተለዉ ሰራዊት በወገናችን ላይ ከኋላ በከፈተዉ ተኩስ አራት ወገኖችቻን ሲገደሉ በአስሩ ላይ ደግሞ ከባድ የመቁሰል አደጋ እንዳደረሰ የአይን እማኞች ገልፀዉልናል።  የሞቱትና የቆሰሉት ወገኖቻችን ቁጥርም እየጨመረ መሆኑን ለማረጋግጥ ተችሎአል።

ከፊት ፋኖ ብሎ ራሱን በሚጠራው የአማራ ጽንፈኞች ቡድን፣ ከኋላ በፋሽስቱ አብይ አህመድ ጦር ቡድን ከተገደሉት ለጊዜው የስም ዝርዝራቸዉ ከደረሰን፦ ኡመር ሙሄ ከባጤ ቀበሌ፣ ኢብራሂም አደም አብደላ እና ሻሮ ማቃስ ከባልጪ ቀበሌ ይገኙበታል። እንዲሁም ከባድ  የመቁሰል አደጋ ከደረሰባቸዉ ወገኖቻችን  መካከል ሃሰን ሞሃመድ፣ ሄሳማና ሞሃመድ ሃሰን ሞሐመድ ከባጤ ቀበሌ እና ሰኢድ ሙሳ ኡማሬ ከጃዋሃ ቀበሌ መሆናቸዉና የደረሰባቸዉም ጉዳት ከፍተኛ እንደሆነ ምንጮቻችን ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ገልፀዋል።ከፊት ፋኖ ብሎ ራሱን በሚጠራው የአማራ ጽንፈኞች ቡድን፣ ከኋላ በፋሽስቱ አብይ አህመድ ጦር ቡድን ከተገደሉት ለጊዜው የስም ዝርዝራቸዉ ከደረሰን፦ ኡመር ሙሄ ከባጤ ቀበሌ፣ ኢብራሂም አደም አብደላ እና ሻሮ ማቃስ ከባልጪ ቀበሌ ይገኙበታል። እንዲሁም ከባድ  የመቁሰል አደጋ ከደረሰባቸዉ ወገኖቻችን  መካከል ሃሰን ሞሃመድ፣ ሄሳማና ሞሃመድ ሃሰን ሞሐመድ ከባጤ ቀበሌ እና ሰኢድ ሙሳ ኡማሬ ከጃዋሃ ቀበሌ መሆናቸዉና የደረሰባቸዉም ጉዳት ከፍተኛ እንደሆነ ምንጮቻችን ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ገልፀዋል።

የነዚህ የአማራ ጽንፈኞች ቡድንና የአቢይ መራሹ ቡድን ዋነኛዉ አላማ የኦሮሞ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀልን መፈጸም ነው። ስለሆነም ሆን ተብሎ ‘የአማራን ህዝብ ትጠብቃላችሁ’ በሚል ሰበብ ያደራጃቸዉ ያስታጠቃቸዉና እንዲጠናከሩ የረዳቸዉ እራሱ የነፍጠኞች አዉራ የሆነዉ ፋሽስቱ አብይ አህመድና በእርሱ የሚመራዉ ቡድን መሆኑ የሚታወስ ነዉ።

በተያያዘ ዘገባም የዞኑ አስተዳዳሪ አህመድ አሊና ተባባሪዎቹ የሃረዋ ከተማ አስተዳደር የሆነዉ ሁሴን አህመድ ኢቢራሂምን ጨምሮ መጋቢት 16/2024 ለስብሰባ ወደ ባሕርዳር በመሄድ ከነዚህ የአማራ ጽንፈኞች ጋር ሲወያዩ እንደነበረም ምንጮቻችን መረጃ ሰጥተዉናል።

ከወሎ ሕዝባችን ጎን በአንድነት እንቁም!

Exit mobile version