ሚያዚያ 6/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
ኢምፓየሪትዋን ወደ ከፍታ እየወሰድኩዋት ነው የሚለው የፋስሺስት አብይ አህመድ ብልጽግና ቡድን የኦሮሞን ህዝብ በሃይል አምበርክኮ ስልጣኑን ለማራዘም ዜጎችን በሃሰት እየወነጀለ እና እያሰረ ይገኛል። የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትን ትረዳላችሁ በሚል የሃሰት ዉንጀላ የዝርፍያ፣ የማስፈራሪያ፣ የእስራት፣ የድብደባ እና ግዲያ ድርጊቶችን በመላው ኦሮሚያ መተግበር ከጀመረም አመታትን አስቆጥረዋል።
በዚሁ መሰረት መጋቢት 19/2024 በቡኖ በደሌ ዞን፣ ጫዋቃ ወረዳ፣ ቡርቃ በረካ ቀበሌ ቁጥራቸው ከ14 በላይ የሆነ ንጹሃን ኦሮሞዎች ላይ ከባድ ድብደባ ካደረሱባቸው በሁዋላ የተወሰኑትን ሲያስሩ ከሌሎች መኖርያ ቤት ደግሞ ሚሊሺያዎቻቸውን የሚቀልቡበትን ምግብ እና እህል እንዲሁም የእጅ ስልኮቻቸዉን ወስደውባቸዋል። የዚህ ድርጊት ሰለባ ከሆኑት መካከል ሰማቸዉን ያገኘነው የሚክትሉት ናቸው።
ከከባድ ድብደባ በሁዋላ ምግብ እና እህል የተወሰደባቸዉ ስም ዝርዝር፦
- ሸሪፍ አደም፣
- ሁሴን አሒመድ፣
- ጀማል ያሲን፣
- ጀማል ዑመር፣
- አብደላ አሒመድ፣
- አብዶ አሊዪ እና
- ሻዚል አህመድ ናቸው።
ከከባድ ድብደባ በሁዋላ ወደ እስር ቤት የተወሰዱት፦
- ኤሊያስ ኑሬ፣
- ዮሐንስ ተሾማ፣
- አብራሒም አደም እና
- ጃፋር አሒመድ የተባሉት ንጹህዋን ናቸው።
ድብደባም ከፈጸሙባቸዉ በሁዋላ የእጅ ስልካቸዉ የተወሰደባቸው፦
- አብደላ ሺዴ፣
- ቴዲ ቀንዓን እና
- ሌንጮ አብደላ ናቸው።
ንጹሃን ኦሮሞዎችን በመደብደብ፣ በማሰር እና ሃብት ንብረታቸውን በመዝረፍ የነፃነት ትግሉን ወደ ኋላ እንደማይመልሰዉ ጠላትም ሆነ ወዳጅ ሊገነዘበው ይገባል።

