Site icon Qeerroo Bilisummaa Oromoo

የብልፅግና ባለስልጣናት በኦሮሚያ ላቀዱት ወረራ ማስፋፍያ ይረዳቸው ዘንድ በጂማ ዞን የነዋሪውን ሕዝብ ቤትና ንብረቱን በመውረስ፣ ያላቸውን ገንዘብ ወደ ብልፅግና ባንክ እንዲያዘዋውሩ፣ በቦንድ ስምም ገንዘብ እያስከፈሉና አስረውም እያሰቃዩ መሆኑን ለማወቅ ተችሎዋል

ግንቦት 18፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ 

(ONM-ABO)

ሰው-በላው የብልፅግና ስርዓት ኦሮሚያ ውስጥ ሰላማዊ ኦሮሞዎችን ከመኖሪያ ቤታቸው ካለምንም ምክንያት ማፈናቀልን፣ ለምን እንፈናቀላለን ብለው ጥያቄ ያቀረቡትን ማሰር፣ ማሰቃየት ከዚያም መግደልን፣ በማስፈራራት ንብረት መዝረፍን አጧጡፎ ቀጥሏል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በቦንድ በማሳበብ ገንዘብ መሰብሰብን እና ሌላ ባንክ ውስጥ ያላቸውን ገንዘብ በብልፅግና ወደ ሚደገፍ ባንክ እንዲያዘዋውሩ ትዕዛዝ መስጠትን ተያይዞታል። 

በጂማ ዞን፣ ቀርሳ ወረዳ

በዚሁ መሰረት በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የፋሺስት አብይ አህመድ ብልፅግና ቡድን የሚተገብረው አርመኔያዊ ተግባር ከዕለት ዕለት እየጨመረ ነው። በጂማ ዞን፣ ቀርሳ ወረዳ፣ ሰርቦ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ቤተሰቡ እንዳያየው በማገድ ከሁለት ወር በላይ በብረት ሰንሰለት እግርና እጁን አስረው እያሰቃዩት ያለው መሐዲ አባ ጀበል አባ ጎዱ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰበት መሆኑን ምንጮቻችን ነግረውናል። ከዚህም በላይ ቤተሰቡ ምግብ እና ልብስ ይዘውለት ወደ ታሰረበት ሲሄዱም “እዚህ የለም” በማለት በረሃብ እየቀጡትም መሆኑን ቤተሰቦቹ አክለው ነግረውናል።

በሌላ ዜና በዚሁ ወረዳ ውስጥ የብልፅግና ካድሬዎች የኦሮሞን ቤት እና መሬት ያለምንም ካሳ ለባለሀብቶች በመስጠት እያፈናቀሉዋቸው መሆኑን ለአቢኦ ተናግረዋል። ነዋሪዎች አክለውም “የምንፈናቀለው ምንም ዓይነት ካሣ ሳይከፍሉን ሲሆን፣” “ለምንድነው የምታፈናቅሉን” ብሎ የጠየቀ ሰው ይደበደባል፣ ይታሰራል፣ በእስር ቤትም ይሰቃያል። “ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ጥያቄ የጠየቁ ሰዎችን በፊታችን ስላዋረድዋቸው መጠየቁን በመፍራታችን ያለምንም ካሳ ተገደድን እየተፈናቀልን ነው። የመብት ጥያቄ መጠየቅ አለመቻላችን አሳስቦናል።” ብለው ጭንቀታቸዉን ለአቢኦ ጨምረው ገልጸዋል።

ጂማ ከተማ

በጂማ ከተማና አከባቢዋ፣ የባጃጅ ባለንብረቶች የሆኑትን እያንዳንዳቸው 50.000 ብር የብልፅግና ባንክ ወደ ሆነው “ሲንቄ ባንክ” በቁጠባ መልክ እንዲያስገቡ በማስገደድ እናም ለማስግባት የማይችሉትን ደግሞ የብልፅግና ካድሬዎች በማስፈራራት ላይ መሆናቸውን ለአቢኦ ተናግረዋል።

በተያያዘ ዜናም ለአባይ ግድብ ቦንድ ግዢ እንደ ግዴታ በማድረግ ከእያንዳንዱ ነዋሪ 500 ብር ከመዝረፋቸውም በላይ የፋሽስቱ ብልፅግና ካድሬዎች ከ3ኛ ክፍል በላይ ተማሪ ልጅ ያላቸው ቤተሰቦች በእያንዳንዱ ልጃቸው ስም 100 ብር ለመስጠትም እየተገደዱ ነው። 

ፋሺስት አቢይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦

“የኦሮሞን ሕዝብ በተለያየ ስልት በመዝረፍ፣ ከቤቱ እና መሬቱ በማፈናቀል ለረሃብ፣ ለእርዛት፣ ለመጠለያ አጥነት አጋልጦ ለመግዛት እና የኦሮሞን ሕዝብ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ለማድረግ፣ መንበር የተሰጠው የፋሺስታዊ መንግስት መሪ።”

Exit mobile version