Site icon Qeerroo Bilisummaa Oromoo

የኦሮም ነፃነት ሰራዊት በምሥራቅ እና በምዕራብ ወለጋ ዞኖች የፋሺስቱ ብልፅግና ወንበር ጠባቂ ሰራዊት ላይ ከባድ እርምጃ መውሰዱ ታውቋል

ሐምሌ 14፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

የኦሮሞ ህዝብ ጋሻና መከታ የሆነው የኦነሰ የምዕራባዊ ዞን የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ   በፋሺስት ብልፅግና ሰራዊት ላይ የሚወስደውን እርምጃ በማጠንከር በምሥራቅ ወለጋ ዞን፣ በገሊላ ከተማ አስተዳደር ውስጥ እና በምዕራብ ወለጋወለጋ ዞን፣ ቦጂ ጨቆርሳ ወረዳ፣ ፊጋ ከተማ አስተዳደር አጠገብ የማጥቃት እርምጃ በመውሰድ አኩሪ ድል መጎናፀፉን የኦነሰ ቃል-አቀባዮች ለአቢኦ ገልፀዋል።

በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ ሐምሌ 4፣ 2024 ከንጋቱ ላይ 11.00 እስከ ምሽቱ 1.30 ሰዓት ድረስ የብርሃኑ ጁላ ልጆች ካምፕን አድፍጦ በመግባት በባሩዳ ሽታ እያጥናቸውና እያሯሯጠ በመምታት ሙትና ቁስለኛ አድርጓቸዋል።

በዚህም የድንገተኛ ማጥቃት እርምጃ ከብልፅግና ዘብ ጠባቂዎች 30 ወዲያው መሞታቸውና 20 ደግሞ ክፉኛ መቁሰላቸውን የአካባቢው የጦር ቃል አቀባይ ለአቢኦ አሳውቆዋል። የብልፅግናው ጦር በቅርብ ያገኙዋቸውን ቁስለኞች እያከሙ እና በየጥሻውም የወደቁትን በመፈለግ ላይ እንደነበሩም ታውቋል።

አምበሳው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በዚሁ ዕለት ከቀኑ 9.00 ሰዓት በኋላ በምዕራብ ወለጋ ዞን፣ ቦጂ ጨቆርሳ ወረዳ፣ ፊጋ ከተማ አስተዳደር አጠገብ ያሉትን የጠላት ሃይል ከቦም የፀረ-ሽምቅ ኃይል አዛዥ ነኝ ባዩን ሳጅን አብዲን ከአፈር ከመቀላቀሉም በላይ 5 የጦር አባሎቹንም አቁስሏል።

#የሺኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ ይቀጥላል!

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያወጀው የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት እና የሀገር ባለቤትነት እስኪረጋገጥ ድረስ በተለየ መልኩም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሎአል።

ድል ለኦሮሞ ህዝብና ለጭቁን ብሔር ብሔረሰቦች!

Exit mobile version