አካለ ጉዳተኛን “ታውቀናለህ?” ሲሉት “አይ አላውቃችሁም።” በማለቱ ገድለው ወደ ገደል የሚወረውሩ አረመኔዎች ሆነዋል
ሐምሌ 15፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
የፋሺስት አብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂው ጦር ቡድን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን በፍልሚያ ሜዳ ላይ መቋቋም አቅቶት ሰራዊቶቹ ወደ ከተማና ህዝብ ወደሚኖርበት መንደር እየገቡ ንፁሃንን መግደል፣ ማሰር፣ ማሰቃየት፣ ንብረት መዝርፍ እና ቤት ከነንብረቱ በእሳት አጋይቶ ማውደም ስራዬ ብለው ከያዙት አመታት አስቆጥረዋል።
ምሥራቅ አርሲ ዞን፣ ዝዋይ ዱግዳ ወረዳ
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ሐምሌ 8፣ 2024 በወሰደው አድፍጦ የማጥቃት እርምጃ መቋቋም ያልቻለው የፋሺስት ብልፅግና ሰራዊት ወደ ኋላ አፈግፍጎ አካባቢውን ለቅቆ ሄዷል። ዝዋይ ከተማ ወዳለው ካምፓቸው እየተመለሱ ሳለ ኢይቱ በተባለው መንደር አካባቢ አሚዶ ከድር የተባለውን አካል ጉዳተኛ ቄሮ በአምስት ጥይት መግደላቸውን የዓይን እማኞች ለአቢኦ ተናግረዋል።
ይህንን ቄሮ በአምስት ጥይት ተኩሰው በመግደላቸውም ሳይረኩ፣ ከገደሉት በኋላም መሬት ላይ በመጎተት ቤተሰቦቹ አስክሬኑን አንስተው እንዳይቀብሩት ገደል ውስጥ ወርውረውት መሄዳቸውን የዓይን እማኞች ጨምረው ገልጸዋል።
የአከባቢው ሰዎችም ይህ ቄሮ በአካል ጉዳተኛነቱ ምክንያት እራሱን ችሎ መኖር ያልቻለ እና በፖለቲካ ውስጥ ምንም ሚና ያልነበረው እንደነበር ለአቢኦ ተናግረዋል። በተጨማሪም እነዚህ ወታደሮች መንገድ ላይ ሲመጡበት “ታውቀናለህ?” ሲሉት “አይ አላውቃችሁም።” ሲላቸው “የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን ስለምታውቅ እኛን አታውቀንም።” በማለት እዚያው እምስት ጥይት አርከፍክፈው ሕይወቱን አጠፉት በማለት ገልፀዋል።
በምዕራብ አርሲ ዞን፣ ሲራሮ ወረዳ
ሰላማዊ ሰዎችን ማሰቃየት በኢምፓየርቷ ውስጥ የፖለቲካ መፍትሄ ይሆናል በማለት ከዘሙኑ ጋር የማይጣጣም እና መፍትሄ የማይሆነውን መንገድ በመጠቀም የፋሺስቱ ብልፅግና ስርዓት አገልጋይ ታጣቂዎች እና ካድሬዎቻቸው ታላቁን የኦሮሞ ህዝብ በጅምላ በማሰር እያሰቃዩዋቸው ይገኛሉ። ሃብት ንብረታቸውንም መዝረፍ አጠናክረው መቀጠላቸው የአቢኦ ምንጮች ገልፀዋል።
በሉኬ ከተማ 01 ቀበሌ ውስጥ ኦቦ ቱሱ ጉዴ እና ኦቦ ገመዲ ኦገቶ የተባሉ ግለሰቦችን ያለ አንዳች ጥፋት “የእናንተ ወንድሞች የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባል እና ሜዳም ናቸው” በማለት በሰኔ ወር የመጨረሻ ሳምንት ላይ ንብረታቸውን ዘርፈው ክፉኛ እየደበደቡ ወደ እስር ቤት ወስደዋቸዋል። እስከ አሁንም በእስር ቤት እያሰቃዩዋቸው እንደሆነ የከተማው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል። ከዚህም በላይ የፋሺስት አብይ የጦር ወንጀል ቡድኖች በወረዳው ውስጥ በነዋሪዎች ላይ የተለያዩ ወንጀሎችን እየፈፀሙ መሆኑንም ጠቁመዋል።
ፋሺስት አብይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦
“የኦሮሞን ሕዝብ መዝረፍ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ማድረግ፣ ከዚህም እልፎ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ እና ለዱር አራዊትም እንዲጣሉ ትዕዛዝ የሚሰጥ የ አውሬነት ባህርይ የተላበሰ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኤምፓየሪትዋ ያስተናገደች፣ ሰብዓዊነት የጎደለው የለየለት ጨካኝ አምባገነ መሪ ነው።”
#የሺኒጋው_የቃልኪዳን_ዘመቻ ይቀጥላል

