በኦሮሞ ነፃነት ግንባር – ኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (የኦነግ-የኦነሰ) እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል ምንም አይነት ውይይት እየተካሄደ አይደለም። የኢትዮጵያ ባለስልጣናት አየር በተነፈሱ ቁጥር የተሳሳተ መረጃዎችን ያሰራጫሉ። በዚህ ወቅት ይሄ ለሁሉም ግልጽ መሆን አለበት።
ኦነግ-ኦነሰ በሀገሪቱ የፀጥታ እና ፖለቲካዊ ቀውስን በሚመለከት እና ስርአታዊ ችግሮችን ለመፍታት በሚደረግ ውይይት ላይ ለመሳተፍ ፅኑ አቋም አለው።

