Site icon Qeerroo Bilisummaa Oromoo

የመካከለኛው ዞን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በተለያዩ ቦታዎች ጠላትን የሚገባውን ቅጣት ሰጥቶ ሸኝቷል

ነሐሴ 11፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

የኦሮሞ ህዝብ ክንድ እና ጋሻ የሆነው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በፋሽስት የብልፅግና ጦር ላይ የሚወስደውን የማያዳግም እርምጃ መውሰዱን ቀጥሎበታል።

ሱሉልታ ወረዳ

ነሐሴ 10፣ 2024 ሸገር ሲቲ ከተማ፣ ጨለለቃ ቀበሌ ውስጥ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በፋሽስት የብልፅግና ጦር ላይ በወሰደው የማያዳግም እርምጃ አንድ የሺ አለቃ አዛዥ እና ጠባቂዎቹን በመግደል መሳሪያዎቻቸውን ከላያቸው ላይ በመፍታት ለነፃነት ትግል ገቢ አድርጓል።

በኤካ ቀበሌ ውስጥ ነሐሴ 11፣ 2024 በብልፅግና ተላላኪዎች ላይ በወሰደው እርምጃ በሙት እና በቁስለኝነት ቀጥቷል።

ሰሜን ሸገር ዞን፣ ደገም ወረዳ

ነሐሴ 11፣ 2024 ጠዋት በሸኖ ቀበሌ በእግር እና በመኪና በመጓዝ ላይ የነበረውን የማፍያው ብልፅግና ጦር ላይ በወሰደው እርምጃ አኩሪ ድል አስመዝግቧል። በዚህም እርምጃ የጠላትን ኃይል በሙት እና በቁስለኝነት በመቅጣት አንድ ፓትሮል መኪና ከጥቅም ውጪ አድርጓል።

ነሐሴ 10፣ 2024 እንበሳው የኦነሰ በሀምቢሶ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በኢትዮጵያ ኢምፓየር ወታደሮች ላይ በወሰደው አድፍጦ የማጥቃት እርምጃ አንድ ፓትሮል ሙሉ አመድ አድርጓል። በውስጡም አንድ የመቶ አለቃ ከሁለት ጠባቂዎቹ ጋርም ነበር።

#የሺኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ ይቀጥላል!

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያወጀው የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት እና የሀገር ባለቤትነት እስኪረጋገጥ ድረስ በተለየ መልኩም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሎአል።

ድል ለኦሮሞ ህዝብና ለጭቁን ብሔር ብሔረሰቦች!

Exit mobile version