Site icon Qeerroo Bilisummaa Oromoo

የብልፅግናው አገዛዝ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ እየፈጸመ ያለው ግፍ የገዛ ሰራዊቱ እንኳ እየከዳው እንዲሄድ ማድረጉ የራሱን ውድቀት እራሱ እያፈጠነ መምጣቱን የሚያሳይ መሆኑን እና በተቃራኒው ደግሞ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ሕዝቡንና ሐገሩን ከጥቃት ለመከላከልና ብሎም ከጭቆና ነፃ ለማውጣት በሚያደርገው ትግል የሚያስመዘግበው ድል ከምን ጊዜውም በላይ አመርቂ ሆኖ እንደቀጠለ ነው

አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO) መጋቢት 12/2024

በፋሺስቱ አብይ እና የአማራ ብልፅግና አመራሮች የተደራጀው እና እየታገዘ ያለው የአማራ ፋኖ የሽብር ቡድን መጋቢት 4-6/2024 በወሎ ኦሮሞዎች ላይ በከፈተው ጥቃት ከ15 ሰዎች በላይ ሲገደሉ ከስድስት ሰዎች በላይ ደግሞ መቁሰላቸው ተስምቶአል። ከተገደሉት 15ቱ ንፁሃን ኦሮሞዎች ስማቸው የታወቀው፦ ጀማል አህመድ ኢማም፣ ሻምበል ኡመር ኢንዲሮ፣ ኡመሮ ሙሳ፣ ሃሰን ሞሐመድ አባ ጉሎ፣ አሊ ጉሬ፣ አደም አማድ፣ ሃሰን ዲሩ፣ ሁሴን አረብ፣ አህመድ ጦይብ፣ አወል ኢብራሂም፣ ሃሰን ሞሐመድ፣ አቢቴ እና አዳድ ሲሆኑ ከቆሰሉት ደግሞ የ ሁሴን ደዌን ስም ከመረጃ ምንጮቻችን ማግኘት ችለናል።

እነዚህም አሸባሪ የአማራ ታጣቂዎች በኦሮሞ ላይ ጥቃቱን የከፈቱት በብዙ አቅጣጫ ሲሆን ፉርሴ ከተባለዉ ስፍራ ጀምረው ከኢንታሌ እስከ ካራ ቆሪ ድረስ ወረራዉን ፈጽመዋል። ይህም ብቻ ሳይሆን የቤት ቁሳቁስ፣ የሱቅ ሸቀጣ ሸቀጥ ዘርፈው እና ከ20 በላይ የቀንድ ከብቶችም በጥይት መግደላቸዉን ምንጮቻችን ነግረውናል።  የሰዴቆ (ቤሎ) ቀበሌ ኦሮሞዎች አንድም ንብረት ከቤት ዉስጥ ማሸሽ ባልቻሉበት ሁኔታ መኖሪያ ቤቶቻቸዉን ሙሉ በሙሉ በእሳት አዉድመዉባቸዋል። ይህም ሕዝባችን ምን ያህል ዉስብስብ ችግር ዉስጥ እንዳለ የሚያመላክት ነው።

በተያያዘ ዜና በምዕራብ አርሲ ዞን ገደብ አሳሳ ወረዳ የሁሉቆ ቀበሌ ነዋሪዎች የነበሩ ሙሳ እና ገቢዮ ቡሩቃ የተባሉ ወንድማማቾችን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ደጋፊዎች ናቸው በሚል ሰበብ ካስርዋቸው በኋላ መጋቢት 1/2024 እዛው የታሰሩበት ቦታ በጥይት ደብድበው እንደገደሏቸው ከወረዳው ነዋሪዎች ከደረሰን መረጃ ማወቅ ችለናል።

የኢምፓየሯ አገዛዝ በየጊዜው እድሜና ፆታ ሳይገድበው ሕዝቡን ለወታደራዊ ስልጠና በማስገደድ የሚወስድ ቢሆንም በዚያው መጠን የመከላከያ ሠራዊት የነበሩ የኦሮሞ ልጆች ስርአቱን በመክዳት ወደ ሕዝባቸው ትግል መቀላቀላቸውን ቀጥለዋል።

የብልጽግና ሥርኣት በሁሉም የኦሮሚያ ክፍሎች፣ የፈረሰበትን መደበኛ የሲቪል መዋቅሩን ለመተካት ሲባል፣ ጥረው ግረው ቤተሰቦቻቸውን እያስተደሩ ያሉትን የቤተሰብ አስተዳዳሪዎች በግዳጅ በማፈን ለሚልሻነት በመመልመል፣ እሳት ውስጥ ለመማገድ  ጠንክሮ እየሰራ መሆኑ ታውቋል። በዚሁ መሰረት፣ በምዕራብ ወለጋ ዞን፣ ማና ስቡ ወረዳ፣ ዜጎችን በማሳቀየት ላይ የተመሰረተ ወታደራዊ የግዳጅ ምልመላ የጀመረው ሶስት ወራትን ያስቆጠረ መሆኑ እና በዚህ ሳምንት ደግሞ ይህ ምልመላ በተለየ ሁኔታ ተጠናክሮ መቀጠሉን ነዋሪዎች በመናገር ላይ ይገኛሉ። ይህም አፈና ከዞኑ የወረዳ ገጠር ቀበሌዎች ለሥራ ወደ ከተሞች የሚሄዱ አባቶችን እንደሚጨምርም ይናገራሉ።

በሌላ በኩል መጋቢት 6 እና 7/2024 የመከላከያ ሰራዊት አባላት ማለትም፣ ከቄለም ወለጋ ዞን፣ አንፊሎ ወረዳ፣ ሙጊ ከተማ ሁለት፣ ከምስራቅ አርሲ ዞን ጃጁ ወረዳ አንድ ከነሙሉ ትጥቃቸዉ ወደ ኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ተቀላቅለዋል። በጥቅሉ 3 የቱርክ AKM፣ 6 የእጅ ቦምቦች ፣ 650 ጥይቶች እና የጦር መሳሪያዎች ለትግሉ ገቢ አድርገዋል። እነሱ የነበሩበት የስርኣቱ ሰራዊት በኦሮሞ ህዝብ ላይ የሚያደርሰዉን ሰብአዊ መብት ረገጣ ተፀይፈዉ ለሕዝባችን መስዋእት መሆን ይሻለናል በማለት ወደ ኦሮሞ ነፃነት ትግል እንደተቀላቀሉ ገልፀዉ፤ በኢምፓየሯ ሰራዊት ዉስጥ ለቀሩት የኦሮሞ ልጆች የእነሱን ፈለግ እንዲከተሉ እና በማይመለከታቸው ጦርነት ዉስጥ ህይወታቸውን ከሚያስገብራቸው እና የሕዝባቸውን ስቃይ ከሚያስቀጥለው ከኢምፓየሪትዋ ህልም እራሳቸውን እንዲያወጡ እና ወደ ሕዝባቸው የነፃነት ትግል እንዲመጡ ጥሪ አቅርበውላቸዋል። 

ወደ ኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ጦር ለመቀላቀል የመጡትም ሆነ እጅ የሰጡት የብልፅግና ወታደሮች እንደ ተናገሩት፤ የብልፅግና ካምፕ የወታደር ብዛት እና ፕሮፖጋንዳ እንጂ በራዕይ የሚታይ አንድነት እንደሌላቸውና በአንድ ውጊያ ብቻ መቶና ከዚያ በላይ ወታደሮች ህይወታቸውን የሚያጡና በብዘት የሚማረኩ መሆናቸውን አስረድተዋል።

ጀግናው የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ሰሞኑን ካስመዘገቡዋቸው የድል ዜናዎች መካከል፤
መጋቢት 8/2024 በምሥራቅ ወለጋ ዞን ሌቃ ዱለቻ ወረዳ ከጦርሴ ካምፕ ለአሰሳ ወጥቶ ወደ ቁበና ሆሮ ቀበሌ ሲንቀሳቀስ የነበረውን የፋሽስት ኃይል ከበባ ውስጥ በማስገባት ድባቅ የመታ ሲሆን የተረፉትንም አሳደው ካምፓቸው ድረስ በመሄድ አጥቅተዋል። በትጥቅ በኩል በዚህ ውጊያ 23 የቱርክ AKM ከ 1400 ጥይት ጋር፣ 4000 የብሬን ጥይቶች፣ 10 እጅ ቦምቦች እና 9 ትጥቅ ለኦሮሞ ነፃነት ትግል ገቢ ማድረግ ተችሎዋል።

መጋቢት 9/2024 በምሥራቅ አርሲ ዞን ሙኔሳ ወረዳ ቶያ ቀበሌ ዉስጥ የሚንቀሳቀሰውን የኦሮሞ ጠላት በአካባቢው በሚንቀሳቅሰው የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ማለትም ጭብራ ጃል ነdhi ገመዳ ቅጣቱን አግኝቷል። በዚህ ውጊያ ሶስቱን በሞት ሰባቱን ደግሞ በከባድ ቁሰል የቀጡዋቸው ሲሆን በተመሳሳይ በሲርካ ወረዳ እንዲሁ ጭብራ መዳ ወላቡ በአሰሳ ምክንያት ወደ ገለቤ አመጃ ሲጓዙ የነበሩትን  የፋሽስቱን ሠራዊት ከበባ ውስጥ በማስገባት ስድስቱን በሞት አስሩን ደግሞ በከባድ ቁስል ሽኝቷቸዋል።

አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

Exit mobile version