ሚያዚያ 29/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
የከፋ ጭቆናና ክፋት በኦሮሞ ህዝብ ላይ እያካሄደ የሚገኘው የኮሎኔል አብይ አህመድ ቡድን በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ገደብ የለሽ ግፍን እይፈፀመ ይገኛል። በኢኮኖሚ ኋላ ቀር ከማድረግም በላይ ቤት ንብረታቸውን ከእህል ጋር በማቃጠል በጎዳና፣ በሜዳ ወይም በጫካ ዉስጥ ለመኖር ከመገደድም አልፈው የእለት ጉርሳቸውን ከሱው እጅም እየጠበቁ ያሉ በ100ሺ ይቆጥራሉ። በጅምላ መታሰር፣ እስር ቤት ዉስጥ መሰቃየት እና ተገድለውም ለዱር አራዊት መጣል የኦሮሞ ሕዝብ የዕለት ዕለት ዜና ሆኖዋል። በዚህም ምክንያት ሕዝባችን በከባድ ስጋት ውስጥ ይገኛል።
መጋቢት 26/2024 ጢሎ ቀበሌ ነጋ ፈርዳ በተባለ ስፍራ የፋሺስት አቢይ ጦር የዘረፋ እና ንብረት አውዳሚ ቡድንን በማሰማራት ማጓጓዝ የሚችሉትን በመዝረፍ ያልቻሉትን ደግሞ ከቤቶቻቹው ጋር በእሳት እጋይተዋል። ለዚህም እኩይ ተግባር ሰለባ የሆኑ ንፁሐን ኦሮሞዎች ስማቸው የደረሰን የሚከተሉት ናቸው፦
- ኦቦ ያሲን በለጣ ሹሬ 22 ኩንታል እህልና ሙሉ የቤት ዕቃቸውን፣
- ኦቦ አቡሉ አሊ ለሙ 23 ኩንታል እህል ከሙሉ የቤት ዕቃ ጋር እና
- ኦቦ ከማል ወንድሙ ለሙ 10 ኩንታል እህል
የተዘረፈባችው ሲሆኑ፤ ከዚህ በታች ያሉት ድግሞ
- ኦቦ ኪበቡ ጃርፉ ሞሳ ቤታቸውን ከሙሉ ንብረታቸው ጋር፣
- ኦቦ ጂባ ሰንበቶ ቤት ንብረታቸውን እና በጎተራቸው የነበረ እህልም፣
- ኦቦ ዳዊት ታፈሳ ተሊላ የቤት ውስጥ ንብረትን የነበራቸውንም እህል ጨምሮ እና
- ኦቦ ገመቹ አያና ቤት ከነንብረቱ እና እህልም በጎተራ
በእሳት የወደመባቸው መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአራታ ቢዮሌሳ ተናግረዋል።
ሆሮ ዶንጎ ቀበሌ ልዩ ስሙ መሎ
የፋሺስቱ ብልፅግና ቡድን ኦሮሞን ለስቃይ ለመዳረግ ምንም ይሉኝታ የሌለው ስብስብ መሆኑን በግልፅ እያሳየ ነው። ይህንንም በመመርኮዝ ይኸው የፋሺስቱ ቡድን ፖለቲካችንን አንቀበልም፣ አንደግፍምም አሉን፣ እንዲሁም የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (የኦነግ) – የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ኦነሰ) አባል ቤተሰቦች ናችውም በማለት በርካታ ሰዎችን አስረው በማሰቃየት ላይ ይገኛሉ።
በዚህ አካባቢም የተስማሩት የማፍያው ቡድን የኦነግ-ኦነሰ አባል የሆነዉን ጃል በንቲ መገርሳ ቤተሰብን ማሰቃየት ለረጅም ግዜ ቀጥለዋል፦
ሚያዚያ 5/2024 የባለቤቱን አዴ ደገቴ አያናን ወንድሞች፦
- ኦቦ Dhiና አያና፣
- ኦቦ ዋቅጂራ አያናና እና
- ኦቦ ዲንቃ ሰርዳን በማሰር ለሶስት ቀን ሲያሰቃዩዋቸው ከቆዩ በኋላ ሚያዚያ 8/2024 ለቅቀዋቸዋል።
ሚያዚያ 8/2024 ደግሞ ሳይነጋ በጠዋት የጃል በንቲ መገርሳ መኖሪያ ቤት በመሄድ ባለቤታቸውን አዴ ደገቴ አያና፣ ደበላ ሰንበቶን እና ዮሴፍ ዋጋሪን ከእንቅልፋቸዉ በመቀስቀስ ከያዙ በኋላ እዛው ሆሮ ዶንጎሮ ቀበሌ ዉስጥ ኦብ ኮምቦሺ ኢዶሳን በመጨመር ወደ ጊዳሚ ወረዳ ቄሌም ከተማ አስተዳደር በመውሰድ አስረዋቸዋል።
ምንጮቻችን እንደሚሉት አዴ ደገቴ አያናን ባለቤትሽንና ሶስቱ ልጆችሽ ያሉበትን ንገሪን እያሉ እየፎከሩባቸው ሲሆን ቤት የቀሩት ልጆቻቸው በኑሮ በጣም እየተቸገሩ መሆናቸውንም አሳዉቀውናል።
ከዚህ በፊትም የፋሽስት እብይ ብልፅግና ጦር ቡድን አዴ ደገቴን “ባለቤትሽንና ሶስት ልጆችሽን ከኦነሠ እንዲመለሱ አድርጊ” በማለት እስር ላይ መቆየታቸውና እንዲሁም ቤታቸውንም አቃጥለው ንብረት ዘርፈው እንደነበረም ዘግበን ነበር።
ፋሺስት አቢይ አህመድ አሊ በቅርሰ ማህደር የሚታወሰው፦
“የኦሮሞን ሕዝብ ንብረትና ቤት በማዉደም ለረሃብ፣ ለእርዛት፣ ለመጠለያ አጥነት አጋልጦ ለመግዛት እና የኦሮሞን ሕዝብ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ለማድረግ፣ መንበር የተሰጠው የፋሺስታዊ መንግስት መሪ።”

