የኦሮሚያ ብሔራዊ ሚድያ
በአብይ አህመድ በሚመራዉ የኢትዮጵያ ኢምፓየር ግዛት ውስጥ አሰቃቂ ግዲያ፣ ድብደባ፣ እስራት፣ እስር ቤት ውስጥ መሰቃየት የኦሮሞ ሕዝብ የዕለት ተዕለት ፅዋ መሆን ከጀመረ እነሆ አምስተኛ አመቱን እያገባደደ ነው።
የኢምፓየሯ ኃይሎች ማለትም፣ የመከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የክልል ፖሊስ፣ እና ሚሊሻ፣ ፋሺስት አቢይ አህመድ የነደፈውና በኦሮሚያ ክልል ፕሬዘዳንት ሺመልስ አብዲሳ የሚመራው በ2018 እንደተቋቋመና ብዙ ግዲያዎችን የፈጸመ ስለመሆኑ በቅርቡ በሮይተርስ ሰፊ የጥናት ዘገባ የተጋለጠዉ ህቡዕ ሚስጢራዊ ገዳይ ቡድን እንዲሁም በፋሺስት አቢይና በአማራ ክልል መሪዎች እየታገዘ የተደራጀው የአማራ ፋኖ የሽብር ቡድን በተቀናጀ መልኩ በመላው ኦሮሚያ በእኩይ ተግባር ላይ ተሰማርተዋል። እነኚህ የጥፋት ሃይሎች በኦሮሚያ የተለያዩ ወረዳዎች፣ ከተማዎችና የገጠር መንደሮች ዉስጥ በመሰማራት ሰላማዊውን ህዝብ አያመሱና እያሸበሩ ከፍተኛ የስጋት ምንጭ ሆነው ይገኛሉ።
እስራት፣ ስቃይና ግድያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከበፊቱ ለየት ባለ መልኩ በጂማ ዞን የተለያዪ ወረዳዎች ጅምላ እስርና ግድያ ተጠናክሮ ቀጥሏል። መጋቢት 1/2014ዓ.ም በጂማ ዞን ቀርሳ ወረዳ ጉንጁ ቀበሌ ውስጥ የዕለት ሥራቸውን እየሰሩ የነበሩና በጅምላ ታፍሰዉ ከታሰሩት ዉስጥ ፈይድ ታሽድ፣ አምዲላዲ አህመድ፣ ፊርዶሳ ቢያ፣ አይሻ አባመጫ፣ ናዝሚና ዛሊካን ሰርቦ ከተማ ባለዉ እሥር ቤት ዉስጥ እየተሰቃዩ እንደሚገኙ ለማውቅ ተችሎአል እንደሚገኙ ለማውቅ ተችሎአል። በተጨማሪም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በርካታ ሰዎች ከቄያቸው እየተፈናቀሉ እንደሆነም ታውቋል።
የፋሺስቱ አቢይ መከላከያ ሠራዊት አባሎች በምዕራብ ወለጋ ዞን ከቂልጡ ካራ ወረዳ አስተዳደር ጋር በመቀናጀት መጋቢት 3/2024 ዓ.ም በማለዳ ወደ ቡኬ አካቼ መንደር ተጉዘው ወጣት ሻረጋ ታማና አብዲሳን በጥይት ደብድበው ከገደሉት በኃላ አራት ሰዎችን፦ ለሜሳ ሞኮንን (እድሜ18 ዓመት)፣ ኦቦ ዮሴፍ ካባ (እድሜ 45 ዓመት)፣ ሚካኤል አበያ (እድሜ 25 ዓመት) እና ተረፈ ሃፍቴ (እድሜ 16 ዓመት) ደግሞ ወደ ጦር ካምፕ ይዘዋቸው በመሄድ እያሰቃዩዋቸው መሆኑ ታውቆዋል።
በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ቶሌ ወርዳ ሃቤቤ ከተማ፣ መጋቢት 3 ቀን 2024 ዓ.ም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሁለት ወንድማማቾችን ከቤተ-ክርስትያን ወስደው አፍነዉ በከተማው ወደ ሚገኘው የገበያ ስፍራ በመውሰድ ጥላሁን ተሰማን በሕዝብ ፊት ሲረሺኑ ወንድሙን ግን ይዘውት የሄዱ ሲሆን እስካሁን ዬት እንዳደረሱት አይታወቅም።
የኤምፓየሩ ሠራዊት የግድያ መረብ ክንፍ መጋቢት 3/2024 ዓ.ም አቶ ታደለ ቶሎሳን በምዕራብ ሸዋ ዞን ጀልዱ ወረዳ ቆፍቱ መንደር ውስጥ ቀዬአቸው ድረስ በመሄድ በጥይት ደብድብው ገድለዋቸዋል። አቶ ታደለ በአካባቢው የተከብሩና የተወደዱ የሀገር ሽማግሌ ነበሩ። ከመገደላቸውም በፊት ንብረታቸውን ዘርፈው መኖሪያ ቤታቸውንም በእሳት አዉድመዋል። አቶ ታደለ ቶሎሳ “ልጅህ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊትን ለቅቆ ወደ ቤት ካልመጣ እንገድልሃለን” የሚል ተደጋጋሚ ማስፈራርያ ሲደረሳቸዉ እንደነበረና በዚሁ መሰረት መገዳላቸዉ ታዉቋል። ለአቅመ ኣዳም የደረሰ ልጅ ለፈጸመው ድርጊት ወላጅ የሚጠየቅበት የህግም ሆነ የሞራል አግባብ አለመኖሩ እየታወቀ ይህ ጸያፍ-ድርጊት መፈጸሙ የስርኣቱን ከንቱነት በደንብ ያሳየ ተግባር ነዉ።
በተያያዘ ዜናም በባቱ ከተማ አስተዳደር በቶሌ ወረዳ የፋሺስት አቢይ ሰራዊት የማታ እንቅስቃሴው አጠናክሮ በመቀጠል ሰላማዊ ኦሮሞዎችን አፍኖ ወደ እስር ቤት መወርወሩን ቀጥሏል። ከነዚህም መካከል መጋቢት 3/2024 ዓ.ም ማታ 5:00 ሰዓት ገደማ ወደ አቶ ለገሰ ከበደ ቤት በመሄድ ይዘውት ወደ ጦር ካምፕ እስር ቤት ከወረወሩት በኃላ በማግስቱ ወደ መኖርያ ቤቱ ተመልሰዉ በመሄድ ልጁን ሚሊዬን ለገሰንም ጨምረዉ ማሰራቸዉ ታውቋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የፋሺስቱ አቢይ ሠራዊትና ለተለያየ እኩይ ተግባር ልዩ ስልጠና የወሰደ ቡድንና የደህነንት ሐይሎቹ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የሚፈጽሙትን የሰብዓዊ መብት ረገጣ በመላው ኦሮሚያ በማጧጧፍ ዘረፋ፣ ድብደባና ንፁሃንን ማሰርን በመላዉ ኦሮሚያ ቀጥለውበታል። ከዚህ ጋር በተያያዘም በምዕራብ ሐረርጌ ዞን በጪሮ ወረዳ በዋጩ ሊማይ መንደር የካቲት 30/2024ዓ.ም ከአቶ ሺመልስ ሱቅ 3,400 ብር የሚግምት ሸቀጥ ሲዘርፉ ከአባድ ጀማል፣ አሜ እሊዪ፣ አወል ኡመሬና ሐሮን ዱdhaኪሶ ደግሞ 18 ኩንታል እህል፣ አንድ ሞባይል ስልክ፣ በጥቅሉ 100 ሺህ ጥሬ ብርና 14 ፍየሎች ዘርፈዋል። ከዚህም በላይ በዚሁ መንድር ዉስጥ መጋቢት 1/2024 ዓ.ም ወጣት ሼይቢ ሞሐመድ፣ ወ/ሮ ፋሚያ ኢንድሪስንና ወ/ሮ ሲቲ ኣብዱላን ይዘው ክፉኛ ከደበድቡዋቸው በኃላ እንዳሰርዋቸዉም ታውቆዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በምዕራብ ሸዋ ዞን ጀልዱ ወረዳ ቆፍቱ፣ ሳሪቲና ቦኒ መንደሮች ዉስጥም ግፉ ተጠናክሮ የቀጠለ መሆኑን ለመረዳት ተችሎአል። በዚሁ መሰረት ኦቦ ሞቲቻ አቶምሳ፣ – በጥይት ተደብድበው የተገደሉት የኦቦ ታደለ ቶሎሳ ወንድም፣ ወንድማቸውን ጥይት እንደ ዝናብ አርከፍክፎባቸው ከገደሉ በኃላ በዚያኑ ዕለት ማለትም መጋቢት 3/2024 ቆፍቱ መንደር የሚገኘውን መኖሪያ ቤታቸውን ከነንብረቱ ካቃጠሉ በኃላ አምስት የቀንድ ከብቶች፣ በርካታ በጎችና ፍየሎችንም ዘርፈው ሄደዋል።
የፋሽስቱ ስርኣት የድብደባ፣ የዝርፍያ ግዲያና እስር ቡድን መጋቢት 4/2024 በዚሁ አካባቢ በሳሪቲ መንደርም ኦቦ ገመቹ ባኢሳ የተባሉ የተከበሩ አዛውንት ቤትም በመሄድ የመኖርያ ቤታቸዉን ከነሙሉ ንብረቱ በእሳት አውድሟል። በዚሁ ዕለት በቦኑ መንደርም ከአቶ ጉዴ ዲባባ ቤት አንድ ላምና በርከት ያሉ በጎችን በመዝረፍ እሳቸውን በወቅቱ ከቤት በማጣታቸው የሶስት ወር ነፍሰ-ጡር ባለቤታቸውን አስረዋል። ከአቶ ጉደታ ፈይሳ ቤትም 3 ኩንታል እህል በመዝረፍ አባታቸው አቶ ፈይሳ ላይ ደግሞ ድብደባ ፈጽመዋል። በተጨማሪም ሂርጳ ኢዴሳንና ሙልኢሳ ዲባባን ከባድ ድብደባ ካደርሱባቸው በኃላ ወደ ቦኒ ከተማ ወስደው በከተማዉ አስተዳደር በሚገኘዉ እስር ቤት ዉስጥ አስረዋቸዋል።
የስርኣቱ ተመሳሳይ ድርጊት በምዕራብ ወለጋ ዞን ለታ ሲቡ፣ ነጆ እና ጃርሶ ወረዳዎችም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነዉ። የአለቆቹን ኦሮሞን ዝረፍ፣ደብድብና እሰር መርሆ በመቀበል የተሰማራዉ አረመኔዉ የስርኣቱ ወታደራዊ ሃይል መጋቢት 4/2024 ዓ.ም ከምዕራብ ወለጋ ዞን ለታ ሲቡ፣ ነጆ እና ጃርሶ ወረዳዎች ዉስጥ ብቻ ከሕዝባችን ላይ 184 ኩንታል ቡናና ሌላም ንብረት ዘርፈዋል። ዝርፍያ ከተፈጸመባቸዉ ወገኖቻችንን መካከል የለታ ሲቡ አሙማ አለልቱ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ፀጋዬ ቀጄላ 175 ኩንታል ቡና፣ 1 የቡና ሚዛን፣ ሱቃቸው ዉስጥ የነበሩ ሸቀጣ-ሸቀጦች መጠጥና መቶ ኪሎ ማርን ጨምሮ በርካታ ንብረቶች ተዘርፈዋል። ይህ ዝርፍያ የተፈጸመዉ አቶ ፀጋዬን ቀደም ብለው እሥር ቤት ካስገቧቸው በኋላ ነው ።
በተመሳሳይ መልኩ የህክምና ባለሙያ ከሆኑት ሂካ ቱጁቤም 4 ኩንታል ቡናና አልባሳትን ሲዘረፉ፣ ከአቶ ኤሊያስ ቂጣታ ደግሞ 4.5 ኩንታል ቡናና 200,000 ብር ዘርፈዋል። በተጨማሪም ከአቶ ጋቢሳ የቡና ሚዛን፣ ከወንጌላውዊ ቃናኒ ሱቅ ውስጥ የነበረ ንብረት ሚዛን ሳይቀር ሲዘርፉ የእድሜ ባለጸጋ ከሆኑት ከአባት ጎባይን ዋቅዋያ ደግሞ ንብረታቸውን በሙሉ ዘርፈው ጭነው ሄደዋል። የዚህ ፋሽስታዊ መንግሥት ሠራዊት የዘርፋ ቡድን በወረዳዎቹ ሥር በሚገኙ ቀበሌዎችም ውስጥ እየዞረ በመዝረፍ ላይ የሚገኝ ሲሆን አንዳንዱን በቁጥር እንኳን ለማስቀመጥ ይከብዳልም ተብሏል።
የፋሽስቱ እቢይ አህመድ እገዛዝ ለድብደባው፣ ለዝርፊያው፣ ቤት ንብረት ለማቃጠሉና ለማውደሙ፣ ለእስራቱና ለግፍ ግድያው የሚሰጠው ምክንያት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን ትረዳላችሁ፣ ልጆቻችሁ ወንድሞቻችሁ እህቶቻችሁ አባታችሁ ወይም ዘመዳችሁ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ትግልን ተቀላቅሏል፣ ተቀላቅላለች፣ እነሱንም እንዲመለሱ መምከርም ሆነ መመለስ አልቻላችሁም፣ የመንግስት ኃይል ያለበትን አካባቢ ለኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት የምትመሩት እና መረጃ የምትሰጡት እናንተ ናችሁ በማለት ነው። ሆኖም ግን በምድር ላይ ያለው ተጨባጭ እውነታው ግን በሚኒሊክ የተጀመረና ከኢምፓየሪቱ ገዢዎች ሲወርድና ሲዋረድ ዛሬ የደረሰ ኦሮሞን በኦሮሞነቱ (በማንነቱ) ለማጥቃት የሚደረግ የግፍ ፕሮጀክት ነው።
ዬትኛዉም ሰብአዊነት የሚሰማዉ ቡድን ይኼንን በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለዉ ግፍና መከራን ማዉገዝ ሰብአዊ ግዴታዉ ነዉ እንላለን።
የኦሮሚያ ብሔራዊ ሚዲያ
የጭቁኖች ድምፅ!

