Site icon Qeerroo Bilisummaa Oromoo

በአሸባሪው የብልፅግና ጦር ሰራዊት በኦሮሚያ የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች ዉስጥ እየተፈጸመ ያለዉ ዘግናኝ ግድያ፣ ዘረፋ፣ ቤትና ንብረት ማዉደም ተጠናክሮ ቀጥሏል 

መጋቢት 18/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

ከጅምሩ ጸረ ኦሮሞነቱ ካለፉት የኢምፓየሪቱ መሪዎች የተለየ እንዳልሆነ በመታወቁ በኦሮሞ ህዝብ የተተፋዉ የአብይ አህመድ ቡድን የበቀል እርምጃዉን በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየወሰደ ቀጥሏል። የቡድኑ ታጣቂዎች በየደረሱበት ሁሉ ንጹሃንን መግደል፣ ማሰር፣ የህዝባችንን ንብረት መዝረፍና ይዘው መንቀሳቀስ ያልቻሉትን ቤት፣ ንብረቱን ደግሞ በእሳት ማዉደሙን እና ሴቶችንም መድፈር እንደቀጠሉ ነዉ።

በሚዳቀኚ፣ በግንደበረት፣ በጀልዱ እና በደንዲ ወረዳዎች ዉስጥ የአሸባሪው አብይ ታጣቂ ኃይሎች ከንብረት ማዉደምና ቤት ከማቃጠል በላይም ሶስት ንጹሃን ኦሮሞዎችን ረሽነዋል። ዝርዝሩም እንደሚከተለው ነው፦

መጋቢት 10/2024 በምዕራብ ሸገር ዞን በሚዳቀኚ ወረዳ በቀኚ ከተማ የሰፈረው የአሸባሪው የብልፅግና ሰራዊት አዴ ያደሺ የተባለች ነፍሰጡር እንደ ኦሮሞ ባህል ለመውለድ ቤተሰቧ ጋ ሄዳ የመውለጃዋን ቀናት እየቆጠረች ባለችበት ያለምንም ጥፋት በግፍ ተገድላለች። 

በግንደበረት ወረዳ በሙካ ዲማ ሶተሎ ቀበሌ መጋቢት 9/2024 ለጥፋት የተሰማራዉ የአብይን ስልጣን ጠባቂ ጦር የአርሶ አደሮችን መኖርያ ቤቶች ከእህልና ከብቶቻቸዉ ጋር በእሳት አቃጥለዋል። በእለቱ የጥፋቱ ሰለባ የሆኑት፦

  1. ኦቦ በቀለ ቡሎ የሶስት ልጆች አባት ሲሆን ቤቱን ከ5 ኩንታል እህል ጋር፣ 
  2. ኦቦ አራርሳ ቶሎሳ የሰባት ልጆች አባት ሲሆኑ ቤታቸውን እና እቤት ውስጥ ታስሮ የነበረ ጥጃንም አብሮ አቃጥለዋል፣
  3. የኦቦ በንቲ ቱፋን አንዱን ቤታቸውን ሲያቃጥሉ ሁለተኛውን ደግሞ ሰባብረዋል 
  4.  ኦቦ ዶሪ ባዬ የስድስት ልጆች አባት ሲሆኑ መኖርያ ቤታቸዉና አቃጥለውባቸዋል።  

ከዚህ ብላይ ስማቸው የተዘረዘረዉ ሁሉ ከእነ ቤተሰቦቻቸዉ ያለመጠለያ ከቀሩት መካከል ይጠቀሳሉ።

ከዚሁ ዞን ሳንወጣ በጀልዱ ወረዳም በተመሳሳይ መልኩ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀልን እያካሄደ ያለዉ ሰራዊት የአምስት ልጆች አባትና ገበሬ ኦቦ ሶሪ አበራ ፈይሳን መጋቢት 13 ቀን 2024 በdhaስ ቆርቻ ቀበሌ ውስጥ ረሽነዋል። የተረሸኑትም ‘የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትን ትቀልባለህ’ በሚል የውሸት ዉንጀላ እንደሆነ ከስፍራዉ የደረሰን መረጃ ያሳያል። በዞኑ ደንዲ ወረዳ ጋሌሳ ከተማ እና ዳኒሳ ጠንቆ ቀበሌ ውስጥ ሰፍረው ያሉት የስርዓቱ ታጣቂዎች ህዝቡን በጦር መሳሪያ በማስፈራራት ከአምስት ሺ እስከ መቶ ሃምሳ ሺ ብር እየሰበሰቡ መሆኑን ነዋሪዎቹ በተጨማሪ ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ገልፀዋል። በስፍራዉ የሰፈሩት የአብይ አህመድ ነዉረኛ ወታደሮች የአስገድዶ መድፈር ወንጀልም እየፈጸሙ ይገኛሉ። 

በምዕራብ ወለጋ ዞን ቦቶሮ ጩቁርሳ ቀበሌ ውስጥ ገረመው ቱሊ የሚባል ወጣት ሲገደል ባለፉት 5 አመታት ብቻ በኢምፓየሪቱ ታጣቂዎቹ የተገደሉትን የቤተሰቡን ቁጥር አምስት አድርሶታል ተብሏል። በዚሁ ወረዳ

በአሌ ቀበሌ ሰርግ ላይ በነበሩ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ተኩስ የከፈተዉ የኢምፓየሪቱ ሰራዊት ታሊላ ደረጀና ገመዳ መላኩ የተባሉ ሰዎችን ሲገድል ሌሎች አራት ወገኖቻችንን አቁስሏል። 

የኦሮሞን ሕዝብ ቤትና ንብረት አልባ ማድረግ ንጹሃንን በኦሮሞነታቸው ብቻ በቤተሰቦቻቸው እና በሕዝብ ፊት መግደል የኦሮሞ ሕዝብን የነፃነት ትግል ወደ ፊት ከመሄድ  አያግደዉም።

Exit mobile version