ግንቦት 9፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
የብልጽግናው አምባገነን ቡድን በግዳጅ ለሚሊሻ ሰልጣኝነት እና ለጤና መድህን ክፍያ በሚል ሰበብ በንፁሃን ኦሮሞዎች ላይ የሚፈጽመውን ወንጀል እና ግፍ አጠናክሮ ቀጥሏል።
በተመሳሳይ መልኩ በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሸናን Dhuጏ ወረዳ የብልጽግና ቡድን ህብረተሰቡን በተለያየ ግዜ የጤና መድህን እንዲከፍሉ እያስገደደ መክፈል ያልቻሉትን ደግሞ እያሰቃየ መሆኑን ነዋሪዎቹ ሲገልጹ ይህንንም እንደ መርሆዉ አድርጎ አሁን ደግሞ የሁለተኛው ምዕራፍ የግዴታ ክፍያ ብሎ ብቅ ማለቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል።
በሸናን Dhuጋ ወረዳ ባሉት ቀብሌዎች ውስጥ የሚኖሩ ኦሮሞዎች ለመድህን ኢንሹራንሱ የተመደበባቸውን ገንዘብ መክፈል ያልቻሉትን በወረዳው በሚገኙ እስር ቤቶች ዉስጥ እየተሰቃዩም መሆኑን ነዋሪዎቹ አክለው ገልጸውልናል።
በሌላ ዜና ደግሞ በወረዳው የሚገኙ ወጣቶችና አዛውንቶችን በሚሊሻ ስልጠና ሰበብ እንደተያዙም ታውቋል::
ወላጆቻቸው ወይም የዕለት ጉርስ አቅራቢያቸው የታሰሩባቸው ቤተሰቦች የሚበሉት አጥተው በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንዳሉም የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል።
ለህፃናት ክትባት፣ አስፈላጊ የወረርሽኝ መከላከያም ሆን አስፈላጊ መድኃኒትን ማቅረብ ያልቻለ እና የጤና ጣቢያዎችን ለጦሩ ካምፕ ያደረገ የማፍያ ቡድን የሚሰበስበው ገንዘብ ለምን እያዋለው እንደሆነ ለማወቅ የሚቸገር ኦሮሞ ይኖራል ብለን አናስብም።
ኦሮሞ ይህንን የፋሺስት ብልፅግና አሳሪ፣ አሰቃይ እና ገዳይ ቡድን በቃኝ በል!

