መስከረም 8፣ አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች ውስጥ የፋሺስት ብልፅግና ጦር ቡድን በሃሰት “ከየኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር ግንኙነት አላችሁ!”፣ “ቤተሰባችሁ የኦሮሞ ኑፃነት አባል ነው።” እና “ገጠር እየኖርክ ከተማ እየመጣህ የምታስተምረው የኦነግ – የኦነሰ ስለምትረዳ ነው።” ብለው በሃሰት በመወንጀል ሰላማዊ ኦሮሞዎችን፣ የኦነሰ ቤተሰቦችን እና መምህራንን ማሰር እና ለረጅም ወራትና አመታት በእስር ቤት ውስጥ ማሰቃየቱን አጠናክረው ቀጥለዋል።
በምዕራብ ሸገር ዞን፣ ጀልዱ ወረዳ
ከሐምሌ የመጨረሻ ሳምንት ጀምሮ ታስረው ከሚሰቃዩት መሃከል ስማቸውን አቢኦ ያገኘው፦
- ኩማ ደንደአ፣
- ኩማ ቱጆ፣
- ቦኪ ፈይሳ፣
- ግርማ ጋዲሳ እና
- በሸነና ጉተማ ሲሆኑ፣ ከእነርሱም ጋር ከ22 ኦሮሞዎች በላይ ተይዘው መታሰራቸውን አቢኦ ከምንጮቹ አግኝቷል።
ምሥራቅ ወለጋ ዞን
ከሁለት ዓመት በላይ በዋማ ሀገሎ ወረዳ አስተዳደ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ታስረው ከሚሰቃዩት ቄሮዎች መሃከል፦
- መገርሳ Dhiንሳ፣
- Dhuጉማ ሞሲሳ እና
- ፈዬራ ደበላ ይገኛሉ።
ሐምሌ 28፣ 2024 በሳሲጋ ወረዳ አስተዳደ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ከታሰሩት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ቤተሰቦች መሃከል፦
- ካሪቱ በልኢና፣
- ኤጄርሶ ኢተፋ፣
- ድርቤ ከባዳ እና
- ጊቦ አብዲሳ ይገኛሉ። የአካባቢው ሰዎችም ወንጀለኛው የብልፅግና ቡድን እነዚህን ንፁሃን በከፍተኛ ደረጃ እያሰቃዩዋቸው መሆኑ አክለው ለአቢኦ ገልፀዋል።
ምዕራብ ወለጋ ዞን
የብልፅግናው ጦር ቡድን ሐምሌ 29፣ 2024 የከተማ ኑሮ የከበዳቸው እና በላሎ አሰቢ ወረዳ ገጠር እየኖሩ ወደ ኢናጎ ከተማ እየመጡ የሚያስተምሩ መምህራንን “ገጠር እየኖርክ ከተማ እየመጣህ የምታስተምረው የኦነግ – የኦነሰ ስለምትረዳ ነው።” በሚል የሃሰት ወንጀል ይዘው በኢናጎ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ አስረው እያሰቃዩዋቸው መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል።
መምህራኖቹም፦
- ሽማ ለሚ፣
- ብርቄ ዋቅቶላ እና
- አዱኛ ቶላ ሲባሉ በአካባቢው ሰዎችም ሆነ በተማሪዎቻቸው የሚከበሩ እና የሚወደዱ እንዲሁም በፖለቲካ ውስጥ ሚና እንዳልነበራቸው የአካባቢው ሰዎች አክለው ገልፀዋል።
ፋሺስት አብይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦
“የኦሮሞን ሕዝብ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ለማድረግ፣ በአሰቃቂ ሁኔታ መግደል መንበር የተሰጠው የፋሺስታዊ መንግስት መሪ።”
#የህዝብ_ተቃውሞው_ይቀጥላል❗
#የሺኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ ይቀጥላል❗️

