Site icon Qeerroo Bilisummaa Oromoo

ሊወድቅ አንድ ሐሙስ የቀረው የፋሺስት ብልፅግና ቡድን በምዕራብ ወለጋ፣ በምሥራቅ አርሲ እና ምሥራቅ ጉጂ ዞኖች ሰላማዊ ኦሮሞዎችን ማሰሩን ቀጥሏል

ነሐሴ 14፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ

(ONM-ABO)

ህዝባችን ለስርዓቱ ያለው እምቢተኝነት ስላስደነገጠው የፋሺስት አብይ አህመድ ብልፅግና ጦር ቡድን ኦሮሞን አስፈራርቶ ለመግዛት ያለአንዳች ማቅማማት ህዝቡ ላይ ይቅር የማይባል ግፍ እየፈጸመ ይገኛል።

ምዕራብ ወለጋ

ሐምሌ 19፣ 2024 በላሎ አሰቢ ወረዳ ውስጥ የእግር ኳስ ጨዋታ ፕሮግራም ዝግጅት ላይ የተሳተፉትን የፋሺስት ብልፅግና ቡድን የዝግጅቱ አላማ ሌላ ነው በማለት በሃሰት በመወንጀል ህዝቡን ወደ እስር ቤት እያጋዘ ይገኛሉ። ከታሰሩትና በእስር ቤት እየተሰቃዩ ካሉት ንፁሃን መካከል አቢኦ ስማቸውን ያገኘው፦ 

  1. ዘውዱ ቶማ
  2. ዘገየ ጉተታ
  3. ገረሙ ኦልጂራ
  4. አበቡ ሞሲሳ
  5. ባጩ በላይ ናቸው።

ምሥራቅ አርሲ ዞን

ሐምሌ 19፣ 2024 በመርቲ ሆባ ወረዳ ውስጥ አህመድ ሙስጠፋ የተባለን ግለሰብ እና አንድ ስሙን ለግዜው ያልታወቀ ግለሰብ ጋር ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር ግንኙነት ይኖራቸዋል በሚል ጥርጣሬ  አስረው እያሰቃዩዋቸው መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል።

እነዚህም ግለሰቦች ያለምንም ጥፋታቸው ተይዘው ቢታሰሩም ከአቅማቸው በላይ የተተመነ ገንዘብ ከፍለው እንዲወጡ ካልከፈሉ ግን እንዲገደሉ ትዕዛዝ መተላለፉን ነዋሪዎቹ አክለው ለአቢኦ ገልፀዋል።

ምሥራቅ ጉጂ ዞን

በጎሮ ዶላ ወረዳ ውስጥ የብልፅግናው ቡድን የታጋይ ቤተሰቦችን ማሰሩንና ማሰቃየቱን አፋፍሞ ቀጥሎበታል። 

የፋሺስት ብልፅግና ጦር ቡድን በዋቶ ቡሬ ቀበሌ ውስጥ ኦቦ አለሙ ሃልኬ የተባለን ግለሰብ “ሴት ልጃችሁ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ውስጥ አለች!” በማለት ቤታቸውን ከነንብረቱ በእሳት አጋይተው ካወደሙ በኋላ ከባለቤታቸው ጋር አስረው እያሰቃዩዋቸው እንደሆነ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናገሩ። ነዋሪዎቹም አክለው እነሱን ማሰቃየት አልበቃ ብሎዋቸው ሁለት ልጆቻቸውንም ወደ እስር ቤት እንደወረወሯቸው ለአቢኦ ገልፀዋል።

ፋሺስት አብይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦

“የኦሮሞን ሕዝብ ንብረትና ቤት በማዉደም ለረሃብ፣ ለእርዛት፣ ለመጠለያ አጥነት አጋልጦ ለመግዛት እና የኦሮሞን ሕዝብ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ለማድረግ፣ ከዚህም እልፎ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ ትዕዛዝ እንዲሰጥ መንበር የተሰጠው የፋሺስታዊ መንግስት መሪ።”

#የሺኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ ይቀጥላል!

Exit mobile version