Site icon Qeerroo Bilisummaa Oromoo

በቄሌም ወለጋ፣ በደቡብ ምዕራብ ሸገር እና በምሥራቅ አርሲ ዞኖች የፋሺስቱ ብልፅግናው ቡድን ሰላማዊ ሰዎችን ወደ እስር ቤት ማጋዙን እና ከእስር ቤት አውጥቶ መረሸኑን ቀጥሏል

ነሐሴ 27፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

የኦሮሞ ሕዝብ በቤቱም፣ ከመስሪያ ቤትም ሆነ ከቤቱ ወጥቶ በሰላም የመመለስ ዕድሉ እየመነመነ ሄዶዋል። የሰብዓዊ መብቱ በፋሺስት አብይ አህመድ ትዕዛዝ እና በሎሌዎቹ ተግባር፣ ከተነፈገም ስድስት ዓመት አልፎታል። ይህም የሰብዓዊ መብት ጥሰት በድብደባ አካለ ስንኩል ማድረግ፣ በእስር ቤት ውስጥ የሰውነት አካልን እና አዕምሮን የሚነካ ስቃይ ከመትገበራቸውም በላይ፣ ከእስር ቤታቸውም አውጥተው መረሸንና ለዱር አራዊት መስጠት የተለመደ አረመኔያዊ ተግባራቸው ነው። 

ቄሌም ወለጋ ዞን፣ ዳሌ ወራባ ወረዳ

የፋሺስቱ ብልፅግና ቡድን በወረዳው ውስጥ የኦሮሞን ህዝብ ማሰር እና ትዕዛዛቸውን ባልተቀበሉትም ላይ ዛቻቸውን ቀጥለዋል። ይህንንም ለመተግበር የፋሽስት ብልፅግና ቡድኑ የትለያየ የሃሰት መወንጀያ መርሆንም ነድፏል።

ሐምሌ 22፣ 2024 የብልፅግናው ቡድን “የፈረሰውን መዋቅር መልሶ ለመግንባት!” በሚል መርሆ ሰላማዊ ሰዎችን በማስፈራራትና አስሮ በማሰቃየት ላይ ይገኛል። የአካባቢው ነዋሪዎች በህዝቡ ላይ እየደረሰ ባለው ዛቻ እና ስቃይ ሀሳብ ውስጥ መግባታቸውን ለአቢኦ ተናግረዋል። 

ደቡብ ምዕራብ ሸገር ዞን

የብልፅግናው ቡድን “የኦሮሞን ብሔርተኝነት ማጥፋት!” በሚል ባወጣው አዋጅ መሰረት ያለምንም ወንጀልና በማን አለብኝነት ሰላማዊ ሰዎችን እያሰቃየ ይገኛል። ይህንንም በመመርኮዝ ሐምሌ 24፣ 2024 ከዚህ በታች ስማቸው የተዘረዘሩትን፦

  1. ቶሌራ ደጀኔ
  2. ተስፋዬ ጫልቺሳ
  3. ፍራኦል ሙለታ
  4. ደጀኔ ቀናሳ
  5. ነጋ ሌሊሳ እና
  6. መላኩ ሲሳይ 

“የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን ትቀልባላችሁ” በሚል የሃሰት ወንጀል የዕለት ስራቸውን ከሚያከናውኑባቸው ቦታ ላይ ተይዘው እስር ቤት አጉረዋቸዋል። ይህንንም የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ አሳውቀዋል።

ከዚህም በላይ የፉሺስት ብልፅግና ቡድን ይቅር የማይባል ግፍ በአርሲ የተለያዩ ዞኖች ውስጥ ማካሄዳቸውን ቀጥለዋል። 

ምሥራቅ አርሲ ዞን፣ መርቲ ወረዳ

በመርቲ ወረዳ በሁሉም ቀበሌዎች ኦሮሞ ከቤቱ ወጥቶ መመለስ ከተነፈገ አመታትን አስቆጥሯል። 

ሐምሌ 18፣ 2024 ንፁሃንን አስረው እያሰቃዩ ሲሆን አንድ ሰላማዊ ግለሰብንም ከእስር ቤት አውጥትው ገድለውም ተጥለው ተገኝተዋል።

  1. ባዪሱ ሃጂ፣
  2. አብደላ በዳ፣
  3. አብደላ ኑራ፣
  4. ብሎ አማን፣
  5. ፍርድ ኑሩ፣
  6. ሙራድ ኑሩ፣
  7. ስልት ቃሲም፣
  8. ገኖ ፋቆ፣
  9. ቃሲም ገለቶ እና
  10. አብዱሮ ጁኔዲ

የተባሉትን ግለሰቦች አስረው እያስቃዩዋቸው ሲሆን ሃጂ አማን የተባሉ ግለሰብንም የፋሺስት ብልፅግና ገዳይ ቡድን ከእስር ቤት አውጥቶ እንደገደሉዋቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል። 

ፋሺስት አብይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦

“የኦሮሞን ሕዝብ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ማድረግ፣ ከዚህም እልፎ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ፣ እና ለዱር አራዊትም እንዲጣሉ ትዕዛዝ የሚሰጥ የ አውሬነት ባህርይ የተላበሰ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኤምፓየሪትዋ ያስተናገደች፣ ሰብዓዊነት የጎደለው የለየለት ጨካኝ አምባገነ መሪ ነው።”

#ጨቋኙ_ኃይል_በኦነሰ_ኃይል_ይገረሰሳል!

#የሺኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ ይቀጥላል!

Exit mobile version