ነሐሴ 7፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮምያ
(ONM-ABO)
የኢትዮጵያ ኢምፓየር ከተመሰረተበት ግዜ ጀምሮ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የሰብዓዊ እና የማህበራዊ መብት ገፈፋ እየተካሄደ ይገኛል። በፋሺስት አብይ አህመድ አገዛዝ ደግሞ የሚያስተገብረው የስብዓዊ መብት ጥሰት አላረካህ ብሎት በህዝቡ ላይ የጦር ወንጀልም እያስፈፀመበት ይገኛል።
በተለይም የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባል ቤተሰቦችን አብረው ከሚኖሩት ማህበረሰብ ውስጥ ለየት ያለ አመለካከት እና በበታችነት እንዲታዩ የፋሺስቱ ብልፅግና ቡድን ስልት አውጥቶ እየተገበረ ይገኛል። ወላጆቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን፥ “ወደ ቤት እንዲመለሱ አድርጉ ካልተመለሱ ግን ቅጣታችሁን ተቀበሉ።” በሚል መርሆ እየተመሩ መዝረፍ የሚችሉትን ንብረታቸውን ዘርፈው፣ የተረፈውንም ንብረት ከቤታቸው ጋር በእሳት እያወደሙ፣ እያስሩ፣ በእስር ቤት ውስጥ እያሰቃዩዋቸው እና ግድያም እየፈፀሙባቸው መሆኑ ታውቋል።
ምስራቅ ወለጋ ዞን
ሐምሌ 15፣ 2024 በዋመ ሀገሎ ወረዳ፣ በርካታ ቀበሌዎች ውስጥ 16 ሰዎችን ይዘው በእስር ቤት አጉረው እያሰቃዩዋቸው ይገኛል። የፋሺስት ብልፅግና ጦር ቡድን የእስረኞቹን ቤተሰቦች ከፍተኛ ገንዘብ ከፍለው ከእስር ቤት እንዲያስወጡዋቸው በማስገደድ ላይ እንዳሉም የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል።
ደቡብ ምዕራብ ሸገር ዞን
በደቡብ ምዕራብ ሸገር ዞን ስር በሚገኙ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ውስጥ በኦሮሞዎች ላይ እስራትና ስቃይ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በታጅብ ሰዮ ወረዳ፣ ቡሳ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ካሉት ስማቸውን ለግዜው ያገኘነው፦
- ኦቦ ቢራኑኑ በቀላ፣
- ኦቦ አሸናፊ በቀላ፣
- ኦቦ አያና አበባ እና
- ኦቦ አሸናፊ ናቸው።
የታሰሩትም የፋሺስት ብልፅግና ቡድኑ “ፖለቲካችንን ተቃወሙ” በማለቱ እንደሆነና እነዚህም ግለሰቦች የግል ኑሮዋቸውን በሰላማዊ መንገድ የሚያካሂዱና ምንም አይነት ፖለቲካዊ ተሳትፎ የሌላቸው መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ነግረዋል።
ፋሺስት አብይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦
“የኦሮሞን ሕዝብ መዝረፍ፣ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ለማድረግ፣ መንበር የተሰጠው የፋሺስታዊ መንግስት መሪ።”
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ለህዝቡ ነፃነት የሚያደርገዉ ትግል አጠናክሮ ይቀጥላል!

