ነሐሴ 9፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
የፋሺስቱ ብልፅግና ቡድን ሰላማዊውን የኦሮሞ ህዝብ ማሰቃየት የዘወትር ስራው አደረጎ ከጀመረ ስድስት ዓመት አልፎታል። በለተይም ካለፉት ሁለት ዓመታት ጀምሮ ጩኸቱን ሊያሰማ እና በግዜ ሊደረስለት የማይቻለውን የኦሮሞ አርሶ አደር ማህበረሰብ ላይ በማተኮር በድብደባ አካለ ጉዳተኛ እያደረገ፣ አስሮ እያሰቃየ፣ በእርሻ ላይም ሆነ እቤታቸው ድረስ እየሄደ በዘግናኝ መንገድ እየገደለ፣ ንብረት ቁም ከብቶችን ሳይቀር አርዶ ከመብላትም አልፎ ዘርፎ በመኪና እያጋዘ፣ እህል በማሳና በጎተራ እንዲሁም ቤት ንብረት በእሳት እያወደመ እና ከቀዬአቸውም እያፈናቀለ ይገኛል።
ምስራቅ ወለጋ
የፋሺስቱ ብልፅግና ቡድን በዲጋ ወረዳ ውስጥ ‘ከ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር ግንኙነት አላችሁ።” በሚል የሃሰት ወንጀል ሰላማዊውን የኦሮሞ ህዝብ ወደ እስር ቤት እያጋዘ ይገኛል።
ሐምሌ 22፣ 2024 አዴ አረጋሽ ነገሮ የተባሉትን እናት “የአንቺ ልጅ የአሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባል እና እየወጋንም ነው።” በማለት በወረዳው የፖሊስ ጽህፈት ቤት ውስጥ አስረው እያሰቃዩዋቸው እንደሆነ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናገሩ።
ቄለም ወለጋ
ሐምሌ 19፣ 2024 የፋሺስት አብይ አህመድ ጦር ቡድን በሀዋ ገላን ወረዳ ኦቦ ዑመር ከበዳ የተባሉትን አርሶ አደር በማሳው ውስጥ ይዘዋቸው ከባድ ድብደባ ከፈፀሙባቸው በኋላ ወደ እስር ቤት እንደወሰዷቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል።
በጊዳሚ ወረዳ ውስጥ “የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን ትቀልባላችሁ።” በሚል የሃሰት ወንጀል በመፈብረክ በርካታ ኦሮሞዎችን ወንጅለው በጅምላ ወደ እስር ቤት እየወሰዱዋቸው ይገኛሉ።
ከታስሩትና በፋሺስት ብልፅግና ቡድን እስር ቤቶች ውስጥ እየተሰቃዩ ከሚገኙት መሃከል ስማቸው የደረሰን፦
- አሸናፊ ኢሚሩ
- ሴና ኢሚሩ
- መልካሙ ቡሊ
- ካሳሁ ጋዲሳ እና
- ሮማኔ ሙለታ ናቸው።
የተጠናከረውን የጅምላ እስርና ስቃይ በመፍራት የአከባቢው ማህበረሰብ ህይወቱን ለማትረፍ ከቀዬው መሰደድ እንደጀመረ ነዋሪዎች ለአቢኦ ገልፀወል።
ፋሺስት አብይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦
“የኦሮሞን ሕዝብ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ለማድረግ፣ መንበር የተሰጠው የፋሺስታዊ መንግስት መሪ።”
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ለህዝቡ ነፃነት የሚያደርገዉ ትግል አጠናክሮ ይቀጥላል!

