• Sat. Mar 14th, 2026

በምሥራቅ ወለጋና በደቡብ ምዕራብ ሸገር ዞኖች ውስጥ የፋሺስቱ ብልፅግና ካድሬዎችና የጦር ቡድኑ በመቀናጀት የጅምላ እስር በኦሮሞዎች ላይ እየፈጸሙ ይገኛል

Aug 18, 2024

ነሐሴ 7፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮምያ

(ONM-ABO)

የኢትዮጵያ ኢምፓየር ከተመሰረተበት ግዜ ጀምሮ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የሰብዓዊ እና የማህበራዊ መብት ገፈፋ እየተካሄደ ይገኛል። በፋሺስት አብይ አህመድ አገዛዝ ደግሞ የሚያስተገብረው የስብዓዊ መብት ጥሰት አላረካህ ብሎት በህዝቡ ላይ የጦር ወንጀልም እያስፈፀመበት ይገኛል። 

በተለይም የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባል ቤተሰቦችን አብረው ከሚኖሩት ማህበረሰብ ውስጥ ለየት ያለ አመለካከት እና በበታችነት እንዲታዩ የፋሺስቱ ብልፅግና ቡድን ስልት አውጥቶ እየተገበረ ይገኛል። ወላጆቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን፥ “ወደ ቤት እንዲመለሱ አድርጉ ካልተመለሱ ግን ቅጣታችሁን ተቀበሉ።” በሚል መርሆ እየተመሩ መዝረፍ የሚችሉትን ንብረታቸውን ዘርፈው፣ የተረፈውንም ንብረት ከቤታቸው ጋር በእሳት እያወደሙ፣ እያስሩ፣ በእስር ቤት ውስጥ እያሰቃዩዋቸው እና ግድያም እየፈፀሙባቸው መሆኑ ታውቋል።

ምስራቅ ወለጋ ዞን

ሐምሌ 15፣ 2024 በዋመ ሀገሎ ወረዳ፣ በርካታ ቀበሌዎች ውስጥ 16 ሰዎችን ይዘው በእስር ቤት አጉረው እያሰቃዩዋቸው ይገኛል። የፋሺስት ብልፅግና ጦር ቡድን የእስረኞቹን ቤተሰቦች ከፍተኛ ገንዘብ ከፍለው ከእስር ቤት እንዲያስወጡዋቸው በማስገደድ ላይ እንዳሉም የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል።

ደቡብ ምዕራብ ሸገር ዞን

በደቡብ ምዕራብ ሸገር ዞን ስር በሚገኙ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ውስጥ በኦሮሞዎች ላይ እስራትና ስቃይ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በታጅብ ሰዮ ወረዳ፣ ቡሳ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ካሉት ስማቸውን ለግዜው ያገኘነው፦

  1. ኦቦ ቢራኑኑ በቀላ፣
  2. ኦቦ አሸናፊ በቀላ፣
  3. ኦቦ አያና አበባ እና
  4. ኦቦ አሸናፊ ናቸው።

የታሰሩትም የፋሺስት ብልፅግና ቡድኑ “ፖለቲካችንን ተቃወሙ” በማለቱ እንደሆነና እነዚህም ግለሰቦች የግል ኑሮዋቸውን በሰላማዊ መንገድ የሚያካሂዱና ምንም አይነት ፖለቲካዊ ተሳትፎ የሌላቸው መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ነግረዋል።

ፋሺስት አብይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦

“የኦሮሞን ሕዝብ መዝረፍ፣ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ለማድረግ፣ መንበር የተሰጠው የፋሺስታዊ መንግስት መሪ።”

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ለህዝቡ ነፃነት የሚያደርገዉ ትግል አጠናክሮ ይቀጥላል!

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading