ግንቦት 16፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
የብልጽግና ቡድን በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለው አፈና እና ጭቆና በዘር ማጥፋት ላይ ያተኮረ ሲሆን የግፍ ስራውም እጅጉን እንደተባባሰ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ገልጸዋል ።
ሚያዝያ 16፣ 2024 በምዕራብ ወለጋ ዞን፣ በነጆ ወረዳ ውስጥ የፋሺስቱ የብልፅግና ጦር ኦቦ ገነቲ የተባሉ ግለሰብ በጥይት ደብድበው ገድልው ቀበሌ 02 ውስጥ ጥለዋቸውም ሄደዋል። ኦቦ ገነቲ ሰላማዊ ሰው፣ በፖለቲካ ውስጥ ምንም ተሳትፎ ያልነበራቸው እና በንግድ ስራ የሚተዳደሩ እንደነበርም ለማወቅ ችለናል።
ኦቦ ገነቲ ለሞት የሚዳርግ ምንም አይነት ወንጀል እንዳልሰሩ እና ያለ ምንም የፍርድ ውሳኔ ይዘው እንደገደሉዋቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናገረዋል።
ከዚሁ የግድያ ዜና ጋር በተያያዘ ቦጂ ጨቆርሳ ወረዳ፣ ሰቦ ሜጢ ቀበሌ ነዋሪ የነበሩት ኦቦ አየላ ቢራሳ ሁለት ልጆቻቸው የኦነሰ አባል ስለሆኑ ብቻ ሚያዚያ 17፣ 2024 ወደ ሲቡ ሄቢቻ ቀበሌ በመውሰድ ገድለው ጥለዋቸው መሄዳቸው ተነግሮናል።
ኦቦ አየለ፣ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አባላት አባት በፋሽስቱ ብልጽግና ጦር ቡድን ተይዘው ለአንድ ቀን ሲሰቃዩዋቸ ቆይተው በመጨረሻም ነፍሳቸው በዚሁ አረመኔ የብልጽግና ሰራዊት እጅ ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ጨምረው ገልጸውልናል።
ፋሺስት አብይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦
“የኦሮሞን ሕዝብ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ማድረግ፣ ከዚህም እልፎ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ እና ለዱር አራዊትም እንዲጣሉ ትዕዛዝ የሚሰጥ የ አውሬነት ባህርይ የተላበሰ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኤምፓየሪትዋ ያስተናገደች፣ ሰብዓዊነት የጎደለው የለየለት ጨካኝ አምባገነ መሪ ነው።”

