Site icon Qeerroo Bilisummaa Oromoo

በምዕራብ ወለጋና በምሥራቅ አርሲ ዞኖች የብልፅግናው ስርዓት ሰራዊት የእሮሞን ህዝብ ማሰር፣ በእስር ቤትም ማሰቃየት እና መግደልም ቀጥለዋል

ሰኔ 20፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

በኮሎኔል አብይ አህመድ የሚመራው የብልፅግና ሰራዊት በሰላማዊ መንገድ የሚኖር እና በፖለቲካ ውስጥ ምንም ዓይነት ተሳትፎ የሌለውን ህዝብ ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር ትቀራረባላችሁ በማለት በገፍ አያሰሩና እየገደሉ ይገኛሉ።

ምዕራብ ወለጋ ዞን

ቆንዳላ ወረዳ

በዚህ ወረዳ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የሚካሄደው ግድያ የቀጠለ ሲሆን ሰኔ 5፣ 2024 ሊቅጢ ከተማ አስተዳደር ውስጥ አንድ ቄሮ ገድለው መንገድ ላይ ጥለውት ተገኝቷል። ሆኖም ግን ከሌላ አካባቢ አምጥተው ስለገደሉት ለጊዜው ማንነቱን ማለትም ስሙንና አድራሻውን ለማወቅ አልተቻለም።

በዚሁ ወረዳ ውስጥ ኦቦ አቡ ገነሞ የተባሉ ግለሰብን ከገደሉ በኋላም ቤታቸው ውስጥ የነበረውን ንብረት ሙሉ በሙሉ፣  ቀይ ሽንኩርት ጭምር በአንድ መኪና ጭነው መዝረፋቸውን እና ቤታቸውንም አፈራርሰው መሄዳቸውን ለአቢኦ ምንጮቹ አሳውቀዋል።  

ሰኔ 4፣ 2024 የፋሺስቱ ብልፅግና ሰራዊት ገዳይ ቡድን አባኦ የተባለውን ቄሮ ሊቅጢ ከተማ ውስጥ ከገደሉት በኋላ ቤተሰብ የልጃቸውን አስክሬን አንስቶ እንዳይቀብር መከልከላቸውንም አቢኦ በምንጮቹ በኩል አረጋግጧል። 

በዚሁ ሳምንት መጨረሻ ላይ እዚሁ ዞን በቤጊና ቆንዳላ ወረዳዎች ውስጥ ንፁሃን ሰዎችን ገድለው መንገድ ላይ ጥለው መሄዳቸው ተዘግቦ ነበር።

በመነ ሲቡ ወረዳ

የማፍያው ብልፅግና ጦር ቡድን ግንቦት 29፣ 2024 በዋጂቲ ቂልጡ ሉቦ ቀበሌ በሰላም ስራቸውን የሚሰሩ እና ምንም የፖለቲካ ተሳትፎ ውስጥ የሌሉ ሰዎችን በሃሰት “የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን ትደግፋላችሁ” ብለው በመወንጀል

  1. ኦቦ ሮባ አብዲሳ፣ 
  2. ኦቦ ሰለሞን ማቲዎስ እና 
  3. ኦቦ ሚልኬሳ ጅሬኛ የሚባሉትን ይዘው በመንዲ ከተማ እስር ቤት ውስጥ እያሰቃዩዋቸው እንደሆነ ተረጋግጦዋል።

በለታ ሲቡ ወረዳ

ግንቦት 27፣ 2024 በአንገሬ ቀበሌ ውስጥ የፋሺስት አብይ አህመድ ጦር ቡድን ሁለት ሰላማዊ ሰዎችን መግደላቸው የአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ምንጮች ያረጋገጡ ሲሆን፣ ከእነሱ ውስጥ ለጊዜው ስሙ የታወቀው ኡሴን የሚባልን ሰው ከተማ ውስጥ ገድለው እንደጣሉት ታውቋል። 

በምስራቅ አርሲ ዞን

ግንቦት 22፣ 2024 በኢንዳቶ አፍረን ቀበሌ ውስጥም ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል ምክንያት በቁጥር ከ50 በላይ ሰዎችን ያለ አንዳች ጥፋት በኦሮሞነታቸው ብቻ ወንጅሎ በእስር ቤት እያሰቃያቸው መሆኑንም የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። 

ከታሰሩት ሰዎች ለጊዜው ለማወቅ የቻልነው፦ 

  1. ተማም ሸሚል፣ 
  2. ሙሃመድ አበዳር፣ 
  3. ሙዳሲር አባ ዱሪ፣ 
  4. ሙራድ ሁሴን፣ እና ወንድሙ 
  5. ኡመር ሁሴን ሲሆኑ 

የአንዲት ህፃን ልጅ እናትን ጭምር በእስር ቤት ውስጥ እያሰቃዩዋቸው ይገኛሉ።

ይህ የብልፅግና ቡድን ተስፋ በመቁረጡ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት እየፈፀመ፣ በኦሮሚያም ውስጥ ሰላም ማሳጣት ላይ አትኩሮ እየሰራ መሆኑን የአቢኦ ምንጮች አያይዘው ገልጸዋል። የኦሮሞ ህዝብ ባለበት ቦታ ሁሉ በአንድነት የነፃነት ትግሉን እያገዘ ስረዓቱን ከላዩ ላይ መንቀል እንዳለበትም አሳስበዋል።

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያወጀው የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት እና የሀገር ባለቤትነት እስኪረጋገጥ ድረስ በተለየ መልኩም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሎአል።

Exit mobile version