ሰኔ 10፣ 2024 አራት ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
የፋሺስቱ ብልፅግና ስርዓት “ኮሬ ነጌኛ” ወይም “የሰላም ኮሚቴ” ተብሎ ባቋቋመው ገዳይ መዋቅሩ በመላው ኦሮሚያ ጭካኔ የተሞላበት ግድያዎች፣ እስራት እና ማሰቃየት በስፋት እየፈጸመ እንደሆነም ታውቆዋል።
ወጣት እና ሽማግሌ ሳይል ኦሮሞን ወደ ጦርነት ሜዳ ልኮ ለማስጨረስ በገፍ ማፈስን የብልፅግናው ቡድን ጦር ቀጥሎበታል። በምዕራብ ሐረርጌ እንደ ጭሮ፣ ጡሎ ጉባ ቆርቻ እና ገመቺስ ወረዳዎች ሕዝቡ ቤቱን ለቅቆ በጎዳና ላይ እንደሚኖሩ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ገልጸዋል። በምስራቅ ሐረርጌ እንደ በደኖ፣ ቀርሳ፣ ሃረማያ፣ ኮምበልቻ፣ ቡርቃ ቲርቲራ፣ ባቢሌ እና ደደር ቄሮዎችን በግዳጅ ወደ ጦር ማሰልጠኛም እየወሰዱ ነው።
ምዕራብ ሐረርጌ
በዚሁ መሰረት “የሰላም ኮሚቴ” ብሎ በሚጠራው የገዳያ ቡድን የሚታዘዘው የሚልሻ ቡድን በቅርቡ፣ በምዕራብ ሐረርጌ፣ ኦዳ ቡልቱም ወረዳ የሚከተሉትን ንፁሃን ኦሮሞዎች ገድለዋል።
- ጃዋር ኢብርሃም፣
- መሃመድ ዛኮ እና
- ኢብሳ ሻሙጥ
የተባሉት ግለስቦችን ጨምሮ ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቁትን በመግደል ዉሃ ውስጥ እንደጣሏቸው የአቢኦ ምንጮች ገለፁ።
ምሥራቅ ሐረርጌ
ግንቦት 11፣ 2024 የቡርቃ ከተማ አስተዳዳሪ የሆነው ሙሐመድ አህመድ የከተማውን አዛውንት የኦነሰ ደጋፊ ናቸው ብሎ የሃሰት ወንጀል በመመስረት አንድ ገዳይ ሚሊሻውን ወደ ኦቦ ሙሐመድ አሊዪ ቤት ሄዶ እንዲገድል ልኮ፣ ሚሊሻዉም እቤታቸው በመሄድ ተኩሶ የገደላቸውም መስሎት ቢሄድም እኝህ የተከበሩት አዛውንት የተመቱት እጃቸው ላይ ስለነበረ ህይወታቸው መትረፋን የአቢኦ ምንጮች ተናግረዋል።
በዚሁ ምሥራቅ ሐረርጌ ዞን፣ በደል ወረዳ “ልጆቻችንን እትውሰዱብን እኛን የሚረዳን የለንም” ያሉትን ወላጆች ድብደባና ስቃይ እየደረሰባቸው መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ገልጸዋል። ከእነዚህም መካከል ስማቸው የተገኘው፦
- ኦቦ ጀማል ኡስማኢል፣
- ኦቦ ዑመር ዩሱፍ፣
- ኦቦ ከድር ጀማል፣
- ኢፍቱ ቶፊክ እና
- መስራ አብዶ ናቸው።
ፋሺስት አብይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦
“የኦሮሞን ሕዝብ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ማድረግ፣ ከዚህም እልፎ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ እና ለዱር አራዊትም እንዲጣሉ ትዕዛዝ የሚሰጥ የ አውሬነት ባህርይ የተላበሰ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኤምፓየሪትዋ ያስተናገደች፣ ሰብዓዊነት የጎደለው የለየለት ጨካኝ አምባገነ መሪ ነው።”

