በዛሬው ዕለት በፊንፊኔ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍንጥሪውን በድጋሜ አቅርቧል። ለእውነተኛ ሰላም መስዋዕትነት የከፈለ ድርጅት እንደመሆናችን መጠንበሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም ይሰፍን ዘንድ የአሜሪካ ኤምባሲ ያቀረበውን ጥሪ በደስታ እንቀበላለን። ቀጣዩ ጊዜከጥቃት እና ጭቆና ተላቆ ፍትህ እና የሰው ልጅ ክብር የሚሰፍንበት ይሆን ዘንድ ይህ የሰላም ጥሪየራሳችን የማያወላውል ቁርጠኛ አቋማችን በመሆኑ በኛ በኩል የምንቀበለው ጥሪ ነው።
ሆኖም ይህ ተማጽኖ የቀረበው የሰላም ፅንሰ ሃሳብን አኮላሽቶ በተደራጀ መንገድ ወደ መጨቆኛ መሳሪያነት ቀይሮ ወደ ለየለት ጦር መሳሪያነት ላሸጋገረው ገዥ ቡድንም ጭምር ነው። በዚህ አገዛዝ ስር ሰላም ማለት ኦርዌሊያዊ ቅንብር ሆኖ፣ ትርጉም የለሽ እና በደም የተጨማለቀ/የጨቀየ ከሆነ ቆይቷል። በመሆኑም የአብይ መንግስት ሰላም ሲል፡-
በመጀመሪያ፣ ጦርነት እንዳይታይ ለማድረግ የሚደረግ ሙከራ ነው። አብይ እና በርሱ ዙሪያ ያሉት በፊንፊኔ ውስጥ ለውስጥ በሹክሹክታ ስለ ሰላም እና እርቅ ሲናገሩ፣ ወታደሩ በመላ ሀገሪቱ ያሉ መንደሮችን ያቃጥላል። አገዛዙ “ሰላም” የሚለውን ቃል ጥቅም ላይ የሚያውለው የፖለቲካ ግጭቶችን ለመፍታት ሳይሆን ህጋዊ ተቃውሞን ለማስወገድ የሚያደረገውን ሙከራ እንዲሽፍንለት ብቻ ነው።
ሁለተኛ፣ ለአብይ አህመድ ሰላም ማለት በሀይል አስገድዶ ዝም የማስባል ከንቱ ሙከራ ነው። አገዛዙ ሰላም ብሎ የሚጠራው እና ለማሳካት ያቀደው ብሄር ተኮር የዘር ማጥፋት ወንጀሉን ተከትሎ የሚከሰተው “ዝምታ” እና አገዛዙን በመቃወሙ ምክንያት በደረሰበት በደል የተጎዳ ህዝብ የሚያሳየውን ጊዜያዊ መራር እርጋታ ተከትሎ የሚመኘውን ዝምታ ነው።
ነፃ ሚዲያዎች ከተዘጉ፣ ሰላማዊ ሰልፎች ከተከለከሉ፣ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ከተገደሉ ወይም ከተሰደዱ በኋላ፣ የሚፈጠረውን የዝምታ ውጤት እነ አብይ አህመድ “ሰላም” ሊሉት ነው። የአብይ“የሰላም” ምኞት ከግዳጅ ዝምታ የሚገኝ፣ የሀሳብ ልዩነትን በጥይት ወደ መቃብር በመላክ ከመቃብር አከባቢ ዝምታ የሚገኝ፣ ከሳንሱር እና ከጅምላ እስራት የሚመነጭ ነው።
በሶስተኛ ደረጃ ሰላም የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ነው:: በተለያዩ ግንባሮች ጦርነት ከፍቶ እያለ የውጭ ዕርዳታን ለማግኛ የተዘረጋ አይን ያወጣ ውሸት ነው። ከምዕራባውያን ለጋሾች ገንዘብ የማሰባሰቢያ የአስመሳይነት ዘዴው ነው:: የጦርነት ዘመቻውን ያለማቋረጥ እየቀጠለ የውጪ ዕርዳታንም ለማግኘት በማሰብ የሚያሳየው የተለመደው የአስመሳይነት ትወና ነው።
በጥቅሉ በአብይ አህመድ ዘንድ “ሰላም” ማለት ውሸት፣ ማጭበርበር እና ሁከትን ጨምሮ የግዴታ ዝምታን ለማምጣት በማናቸውም መንገድ የሚደረግ ሙከራ ነው። የሀገሪቱ እና የቀጠናው ሰላም መሆን ስትራቴጂያዊ ጥቅሟ ጋር የተቆራኘ እንደመሆኑ መጠን ዩናይትድስቴትስ ከሚከተሉት እርምጃ ጀምሮ የራሷን አቅም መጠቀም አለባት።
- እንደ አይ.ኤም.ኤፍ እና የዓለም ባንክ ያሉ የገንዘብ ተቋማት ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያዎችን ብቻሳይሆን ሊረጋገጥ በሚችል የሰላም ግንባታ ላይ የሚታየው ውጤት ታይቶ የገንዘብ ድጋፍእንዲያደርጉ ቅድመ ሁኔታዎችን ማድረግ። ህጻናትን የሚገድል አገዛዝ ከአሁን በኋላ ያለገደብእንደፈለገ የሚጠቀምባቸው ባዶ ቼኮች እንዳይኖሩት ማድረግ።
- በመላ አገሪቱ የተፈፀመውን ግፍ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ መጠየቅ።
- ቁልፍ የሆኑ ግጭት ጠንሳሽ የፖለቲካ እና ወታደራዊ ተዋናዮች ላይ፣ ፕሮፓጋንዲስቶች ላይእንዲሁም የገንዘብ ምንጮቻቸውን በየቦታው ለማድረቅ ማእቀብ ማድረግ፣ ማገድ።
ያለበለዚያ “የሰላም” ቋንቋው ከገዥው ቡድን ጦር መሳሪያዎች ውስጥ እንደ አንዱ ሆኖ ጭቁኖችን አፍየሚያስይዝ እና ንፁሃንን የሚገድል ሆኖ ማገልገሉ አይቀርም።
የኦነግ-ኦነሠ ከፍተኛ ዕዝ
ግንቦት 23 ቀን 2025

