Site icon Qeerroo Bilisummaa Oromoo

“ጦርነት ሰላም፣ ነፃነት ባርነት፤ መሃይምነት ኃይል ነው” ዘመን ተሻጋሪው የኦርዌል ማሳሰብያ (የኦሮሞ ነፃነት ግንባር-የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት መግለጫ)

የአብይ ስረዓት ህዝቡ በሰላም ዙረያ ያለውን አመለካከት ለመቆጣጠር፣ ህዝባችን በንፁህ ልቦና እና
በተስፋ መቁረጥ እያካሄደ ያለውን የሰላም ሰልፍ መጥለፉን ቀጥሎበታል። ህዝባችን ቀጣይነት ላለው
የሰላም ፍላጎት የዘውትር ኣክብሮታችንን እየገለፅን፣ የስረዓቱን ማንነትን ማጋለጥ እና ደጋግሞ
መግለፅም አስፈላጊ ነው። ህዝባችን ለሚገባው እውነተኛው ሰላም ሰላማዊ ሰልፍ ብያደርግም
(የብልጽግናን ካድሬን ሰምቶ የወጣው እንዳለ ሆኖ)፣ ኣገዛዙ ያልፈቀደው ሰልፍ ወይም የፖለቲካ ትርፍ
ላገኝበት አልችልም ብሎ የማያምንበት ስብሰባ በሱ ቁጥጥር ስር ባሉ ማንኛውም የሀገሪቱ ክልል ውስጥ
አይሞከርም። አገዛዙ ሰላም ብሎ የሚጠራው፣ በየኦርዌሊያን ድርብ፡አነጋገር፣ ጦርነት ነው። ደግመን
እንደገለፅነው የአገዛዙ የሰላም ጥሪ ሰላም አይደለም፣ አገዛዙ የሚፈጽመውን ግፍና በደል እንዲቀጥል
ይበልጥ ያለማንም ከልካይ ለማስቻል የህዝቡን የመከላከል ዐቅም ለመንጠቅ የተነደፈ ከንቱ የትጥቅ
ማስፈታት ዘመቻ ነው። በመሆኑም የሚከተሉትን የኣገዛዙን ዕኩይ ተግባራትና ስልቶችን በድጋሚ
እናስታውሳለን፣ እንገልፃለን። የአብዮታችንን ዲሞክራሲያዊ እሳቤዎች የጠለፈው እና የከዳው ይህ አገዛዝ
ነው ።

  1. ለቁጥር የሚታክቱ የቄሮ ንቅናቄ ጀግኖችን መስዋእትነት ያዋረደ፣ ከዚያም ከአብዮቱ ጽንሰሀሳቦች
    በተቃራኒ ዓላማ በሚያገለግሉ አካላት የተሞላ ስረዓት ነው። ክቡር የሆነውን ሁሉ
    በመጥለፍ እኩይ ተግባራቸው አሁንም አብዮቱን የጠለፉበትን የግል አጀንዳ ለማስፈጸም ህዝባዊ
    የሰላም ጥሪውን ተቀምጠዋል።
  2. በማንኛው ውጤታማ ተግባሮች ውጤት አለባ ሆኖ ሳለ፣ የኦሮሞን ሆነ የሌላውን ማህበረሰቦች ድምጽ የማፈን ጥበብን ግን ተክኖበታል። ከስድስት ዓመት በፊት በኦሮሞ ላይ ጦርነት በማወጅ የተጀመረው ጦርነት በኣሁኑ ግዜ በመላ ሀገሪቱ ተዳርሶ ይገኛል። እምነታቸውን በስረዓቱ ላይ በማድረግ ለሰላም እድል የሰጡ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ታጋዮችን ገደለ፣ በመቀጠል የተደራጁ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን የማፍረስ እርምጃ ወሰደ፣ እነ አርቲስ ሀጫሉ ሁንዴሳ፣ ጃል በቴ ኡርጌሳ እና ሌሎች ስፍር ቁጥር የሌላቸው የህዝብ ልጆች ላይ አሰቃቂ ግድያዎችን ፈፀመ። ግልፅ እንሁን፦ የመጠየቅ ነፃነቱን የተነጠቀ ማህበረሰብ በሰላም ሳይሆን፤ በከበባ ስር ነው ያለው። አገዛዙ የህግ አግባብነት ያለው የትጥቅ ትግልን ከአመጽ ጋር ብቻ የሚያያይዘው፣ ኣጀንዳው ስልጣኑን ማጠናከር ብቻ ስለሆነ ነው ።
  3. የሰው እና የቁስ ሀብታችንን በመዝረፍ ከተገመተው ሁሉ በበለጠ ሁኔታ ህዝባችንን ለሰቆቃ የዳረገ አገዛዝ ነው። ወጣቶቻችን ከዩኒቨርሲቲ ውሰጥ አስገድዶ ወደ ጦር ካምፕ በመላክ፣ ችሎታቸውን እና ምኞታቸውን በማፈን ላይ ይገኛል። እጅግ በጣም ጥሩ በሆነው ሴናሪዮ/ሁኔታ፣ ሀብት ካላቸው ቤተሰብ የተወለዱ ሰዎች ከገቡበት ወጥመድ ለአገዛዙ ወታደሮች/ካድሬዎች ብዙ ቤዛ ከከፈሉ በኋላ ሊፈቱ ይችላሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ በትምህርት እና በልማት መሰረቶች ላይ ኢንቨስት ከማድረግ ይልቅ፣ ሀብታችንን በአሸብራቂ ፖርኮች፣ የመንገድ ዳር መብራቶች፣ እና ሪዞርቶች መንግስት ሊሰራቸው የማይገቡ ፕሮጄክቶች፣ ለወደፊት እጣ ፋንታችን አንዳች የአምራችነት
    ዓለማ የማያገለግሉ፣ እና የህዝባችንን አጣዳፊ ፍላጎት ማሟላት በማይችሉ ፕሮጄክቶች ላይ
    ያባክናል። ሁሉም ሀብት የአብይ አህመድ የግል ቅዠት ለማገልገል እየባከነ ይገኛል።
  4. ከነችግሮቹም ቢሆን፣ ሀገሪቷን አንድ ላይ ይዞ ያለውን ስርዓትና ማህበራዊ ዕሴት ለግለሰብ ስልጣን ብሎ ከማፍረስ ያለፈ ለሀገር የወደፊት ዕጣ ፈንታ ወጥ የሆነ እቅድም ሆነ ራዕይ የሌለው አገዛዝ ነው።
  5. ከላይ የተጠቀሱትን በደሎችን እና ሙስናዎችን ለማስቀጠል አገዛዙ የሰላሙን ቋንቋ እንደ አንድ
    መሣሪያ ይጠቀማል። ከየኦሮሞ ነፃነት ግንባር-የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በተቃራኒ የአገዛዙ የሰላም
    ጥሪዎች ከፅንሰ፡ ሃሳቡ የራቁ ናቸው። የእነሱ ሰላም ከላይ የተጠቀሱትን በደሎችን መከላከል
    ወይም ማስቀረት ሳይሆን ያለከልካይ ማስቀጠልን ያለመ ከንቱ ጥሪ ነው። ለዚህ ነው በደል ከልካዮችን (በትጥቅ የተደራጁ የነፃነት ታጋዮችን) ትጥቅ ለማስፈታት ሰላም ተብዬው ጥሪ ተደረገ እያለ የሚቃዠበት።

ህዝቦቻችን እውነተኛ እና ዘላቂ ሰላም አጥብቆ ይፈልጋሉ። እኛም ለረጅም ጊዜ እውነተኛውን ሰላም
ለማስፈን ጥሪ ስናደርግ ቆይተናል። ጦርነትን የምናውቀው ከ፬፡ ኪሎ ፅህፈት ቤት ውስጥ በምናየው በድሮን የተቀረጹ ሽርፍራፊ ቪዲዮዎች ሳይሆን፣ እለት ከእለት እየኖርነው ነው። የሰላምን እንቁነት ከማንም በተሻለ ሁኔታ እንገነዘባለን። ይሁን እንጂ አብይ አህመድን ኣሳውሮ የያዘው ያልተገባ ፬፣ኪሎ ሰራሽ ምቾትና ድንቁርናን እስከምናዛባ ድረስ ሰላም የማይገኝ እና የኦርዌሊያን ድርብ፡አነጋገር ምርኮኛ ሆኖ ይቀጥላል::

የኦነግ-ኦነሰ ከፍተኛ አዛዥ

ህዳር 14 2024

Exit mobile version