አዲሱን ዓመት (የግሪጎሪያኑን አቆጣጠር) በምንቀበልበት ወቅትም፣ አብይ አህመድ የስልጣኑን አይቀሬ ውድቀት ለመታደግ ሲል የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎቹን ከሦስት እርስ በርሳቸው ከተያያዙ፣ ነገር ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተንኮታኮቱ ባሉ ምሰሶዎች ላይ እንደተንጠለጠለ ቀጥሏል።
የመጀመሪያው ምሰሶ ኃላፊነት በጎደለው መልክ ከፍተኛ የሆነ የሀገር ሀብትን ወደ ወታደራዊ ወጪዎች ማዘዋወር ላይ የተመሠረተ ነው። የአገዛዙ ጦር እስካአሁን መቆት የቻለው እጅግ ብዙ የህዝብ አንጡራ ሀብቶች እና የውጭ እርዳታዎችን ጭምር ከሃገሪቱ እና ከሕዝቦቿ ጥቅምና ፍላጎት በተቃራኒ ለጦር መሳሪያና የውግያ ሎጅስቲክስ መግዣ ስላዋለ ብቻ ነው። ሆኖም፣ የተጋነነ የሀገር ሀብትን በመጠቀም ጭምር ከየሠራዊት ቁጥር ማብዛት እንዲሁም አንዳንድ ቴክኖሎጂዎችን ከመሸመት ያለፈ ውጤት አላስገኘለትም። ቁጥሮች ብቻቸውን ውጤታማ ኃይል አይፈጥሩም። የወታደራዊ/ሙያዊ ብቃት ወይም የሞራል ወይም ቁርጠኝነት ምትክ አይደሉም። ከእንግዲ ታክቲካል የሆነ ወታደራዊ ቴክኖሎጂም ቢሆን በብቸኘነት በስርዓቱ ቁጥጥር ስር መሆኑ አብቅቶለታል፤ ለመብት ተፋላሚ ኃይሎችም ተደራሽ እየሆነ መጥቷል።
የፀጥታ ዘርፉም ቢሆን የተበታተነና የታዳከመ ነው። አብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኃይል (ENDF) ክፍሎች፣ ፌዴራል ፖሊስ፣ የደህንነት መረጃ አገልግሎቶች እና ክልላዊ ኃይሎች አጠቃላይ ክፍሎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እርካታ እያጡ ነው – በየደረጃው ባለው የፀጥታ መዋቅር ውስጥ ያለው አድሏዊ የሆነ የሀብት ክፍፍል ወይም አብይ አህመድ ሃገሪቱን እየመራ ባለበት የፖለቲካ አቅጣጫ የተነሳ ግራ መጋባት ውስጥ ገብተዋል።
ከእነዚህ ኃይሎች ያሉ ክፍሎች በዋናነት የፖለቲካ ማስገደጃ መሳሪያዎች ሆነው መስራታቸውን ቀጥለዋል። ባለፈው ዓመት የተለየ ሃሳብ ያላቸውን ለማፈን፣ ማህበረሰቦችን ለማስፈራራት እና ቁጥጥር ያላቸው መሆኑን ለማሳየት ተሰማርተዋል። ሆኖም ግን፣ የENDF ታማኝ እምብርት በጦር ሜዳ ኪሳራዎች፣ በጅምላ መባረር እና በሞራል ውድቀት መሸርሸሩን ቀጥሏል። አገዛዙ አሁን ማዕረጉን ለመሙላት በግዳጅ ምልመላ፣ በአስቸኳይ የቅጥር እንቅስቃሴዎች፣ በሐሰተኛ ሚሊሻዎች እና መደበኛ ባልሆኑ አደረጃጀቶች ላይ ይተማመናል። በብዙ ግንባሮች በተከፈተበት ጥቃት አገዛዙ ላይ ከመጠን በላይ መስፋፋት የዕዝ ሰንሰለት፣ በሎጂስቲክስ እና በስትራቴጂካዊ ትስስር ረገድ በከፍተኛ ደረጃ ደከማ መሆኑ የተጋለጠበት ነበር። ባለፈው ዓመት የኦሮሞ ነጻት ሠራዊት ከእነዚህ ኃይሎች ጋር የነበረው ውግያ ለዚህ ተጠቃሽ ግልፅ ምስክር ሆኖ ያገለግላል።
የወታደራዊ ዘመቻዎቻችን ማጠቃለያ
በጂኦግራፊያዊ እና በጊዜ ወሰን
ምዕራባዊ ዞን እዝ፡ ምዕራባዊ ክፍል እና የወለጋ ዞኖች፡- በተደጋጋሚ ወታደራዊ ካምፖችን ከቦ ማጥቃት፣ የአቅርቦት መስመሮችን ማቋረጥ እና በአገዛዙ መከላከያ ሃይል (ENDF) ክፍሎች እና ሚሊሻ ኃይሎች ላይ የተፈፀሙ ጥቃቶች፤
ማዕከላዊ ዞን እዝ፡ ሸገር/ሸዋ ዞኖች (ሰላሌ/ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብ ሸዋ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ሸገር ልዩ ዞን/ከተማ)፡- በዋና ዋና የሎጂስቲክ ኮሪደሮች እና በዋና ከተማው አቅራቢያ ተደጋጋሚ ጥቃቶች፤
ምስራቃዊ እና ደቡባዊ፡ አርሲ፣ ሃረርጌ፣ ጉጂ፣ ቦራና፣ ወሎ፣ ማታካል፣ ቤኒሻንጉል፡- የነጻነት ፍልሚያውን ጂኦግራፊያዊ ስርጭት በማስፋት አገዛዙ ማንኛውንም ኦፕሬሽን ላይ የመቆጣጠር አስቸጋሪነት የሚያንፀባርቁ ዘላቂ ዘመቻዎች።
የአላማ ጽናት ዘመቻ (1ኛ ሩብ-2025)፡- ዘመቻው ወደ ባለብዙ ግንባር የተቀናጀ ጥቃት የተሸጋገረ ሆኖ በአገር አቀፍ ደረጃ የተደረገ ነው።
የሺህ ግንባር ዘመቻ (ኤፕሪል 2025)፡- በ50 ወረዳዎች በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ ለተከታታይ 10 ቀናት የዘለቁ ጥልቅና ተደራሽነታቸው ሰፊ የሆኑ ዘመቻዎች፣ የአገዛዙን ሀይል በስኬት መበታተን የቻሉ ሺህ ግንባሮች ናቸው።
ተከታታይ ዘላቂ ዘመቻዎች (2ኛ ሩብ – 4ኛ ሩብ፡ 2025):- በሁሉም የኦሮሚያ ዞኖች እና ከዚያም ባሻገር ተከታታይና አስጨናቂ የሆኑ ኢላማቸውን፣ የአገዛዙን የዕዝ መዋቅሮች፣ የአቅርቦት መስመሮች እና የሠራዊት ምልመላ ጥረቶች ማክሸፍን ማዕከል ያደረጉ ዘመቻዎችን አድርጓል።
አጠቃላይ የሠራዊታችን ድሎች/ተፅዕኖዎች (ከጥር እስከ ታህሳስ 2025):
የአገዛዙ የሰው ኃይል ኪሳራ፡ በሁሉም ዋና ዋና ዘመቻዎች በትንሹ፣ ከ7,500 በላይ በውጊያ ውስጥ ተገድለዋል እና ከ8,000 በላይ ቆስለዋል።
የሠራዊታችን የቁሳቁስ ትርፍ፡ በሺዎች የሚቆጠሩ ትናንሽና የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያዎች፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ የቡድን ጦር መሳሪያዎች (PKM፣ DShK፣ ስናይፐር ጠመንጃዎች) እና ብዛት ያላቸው የጥይት ክምችቶች ተይዘው ለነፃነት ትግሉ ገቢ ተደርገዋል።
ሌሎች ተፅዕኖዎች፡ እስር ቤቶች ላይ በተደረጉ ፍተሻዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞች ከእስር ነፃ ሆነዋል፣ ወሳኝ በሆነው የኢትዮ-ጂቡቲ የወጪ ገቢ የአቅርቦት ኮሪደር ላይ ተደጋጋሚ እገዳዎች ተጥለዋል፣ እንዲሁም የደህንነት ሁኔታው እጅግ በመባባሱ የአገዛዙ ሲቪል መንግሥት ኃላፊዎች ለጥበቃቸው በሚል ከሲቭል ነዋሪነት በግድ ተነጥለው በወታደራዊ ካምፖች ውስጥ እንዲኖሩና ከዛው ለመስራት መገደዳቸው ተጠቃሽ ናቸው።
የአብይ ህልውና ወታደራዊ ምሰሶ በስም ብቻ የቀጠለ ሲሆን፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተለጠጠ መጥቶ የሚበጠስበት ጥግ ላይ መድረሱ፣ የተከላካይነት ውይም መልስ ሰጪ እና በውጭ የገንዘብ እና የፖለቲካ ድጋፍ ላይ የተመሰረተ ነው።
ሁለተኛው የአብይ አህመድ አገዛዝ ምሰሶ የፕሮፓጋንዳ ስምሪቶች፣ የመረጃ ፍሰት ቁጥጥር እና የማጭበርበር ስልታዊ ትርክት ቁጥጥርና ስርጭት ነው። የመንግስት ሚዲያዎች፣ ተባባሪና የአገዛዙ ተቀጥያ ፕሮክሲዎች እና የሳይበር ሠራዊት ክፍሎች ለአገዛዙ ቅቡልነትን ለማስገኘት ህጋዊነትን፣ የተቃዋሚ ኃይሎችን ስም ለማጉደፍ እና አላግባብ መጠቀምን ለመሸፈን የታለሙ ትረካዎችን ያዘጋጃሉ። በገለልተኛ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ላይ ያለው እቀባ፣ የኢንተርኔት መዘጋት፣ የተለያዩ መገናኛ መድረኮች ገደቦች እና የነፃ ጋዜጠኞችን በወንጀል መፈረጅ፣ የተሰሩ እኩይ ገደቦች የስርዐቱ መደበኛ አሰራር ሆነው ቀጥለዋል። የተቀናጁ የመስመር ላይ ዘመቻዎች ወታደራዊ ውድቀቶችን እንደ የአንድ ግዜ ክስተቶች ለማሳየት እና የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችን ሕገ-ወጥ ወይም ውጫዊ በሆነ አካል እንደሚንቀሳቀሱ ለማስመሰል ይሞክራሉ።
ይህ ለቀድሞው አገዛዝ የህልውና መራዘምም ሁነኛ መሳሪያ ነበር። አብይ አህመድን የሚለየው ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ የተዛባ መረጃን በኩራት የሚጠቀምበት መጠን እና ድፍረት ነው። አገዛዙ ‘ተያዙ’ ተብለው የሚቀረቡ የተቃዋሚ ተዋጊዎች በተመለከተ የውሸት ምስሎችን በግልጽ ያዘጋጃል፣ የውክልና ጦርነት የሚዋጋለትን የራሱ ሚሊሻ ያሰማራል፣ እንዲሁም ምናባዊ እጅ የመስጠት ትወናዎችን ከምንም ተነስቶ ይደርሳል፤ ያዘጋጃል። ለምሳሌ፣ በቅርቡ ለብዙ ዲፕሎማቶች “ከ40,000 በላይ የኦነሠ ተዋጊዎችን እንደገደለ” ያለ አንዳች ሀፍረት አሳውቋል።
እንዲሁም በእድገት፣ በዋጋ ግሽበት እና በአጠቃላይ ማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸም ላይ ያለውን የኢኮኖሚ መረጃ በመደበኛነት የተጭበረበሩ አሃዞችን ይፋ ያደርጋል። ይህ በከፊል ትክክለኛ ሪፖርት ለማቅረብ የሚያግዙ ተቋማዊ አሰራሮችን በማፍረስ የተፈቀደ ሲሆን፣ ይህም እንደ ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ያሉ ተቋሞች፣ ካድሬ ያልሆኑ ባለሙያዎችን ከስራ ካባረሩ በኋላ የሙያ ብቃትን የሚመስል ነገር ማስወገድን ያካትታል።
ለተወሰነ ጊዜ እነዚህ ስልቶች አብይ አህመድን ሥልጣን በመደገፍ ረግድ ረድተዋል። ዛሬ ግን ወደ ማይቀረው ተፈጥሯዊ ገደባቸው እየተቃረቡ ነው። ገለልተኛ ሀገራዊ ሚዲያዎች ይፋዊ ትረካዎቹን ለማስተጋባት እየጣሩ አይገኙም። የተቃዋሚዎች ድምፅ አዳዲስ መድረኮችን እየፈጠሩ ነው። የማህበራዊ ሚዲያ፣ የዲያስፖራ ልሳኖች እና የዜጎች ግለሰባዊ ዘገባዎች በስርዓቱ ውስጥ የሚነሱ ጥያቄዎችን እና ተቃርኖዎችን ማጋለጡን ቀጥለዋል።
ከደህንነት ተቋሙ እና ከክልል አስተዳደሮች የሚወጡ መረጃዎች፤ ውስጣዊ ስብራት እና ክፍፍሉን በሚገባ ያሳያሉ። ጭቆናን እንደ “ሪፎርም/reform”፣ የምጣኔ ሃብት የአስተዳደር ብልሹነትን እንደ “የዋና ከተማ ገፅታ ግንባታ” እና ተጠያቂነት አለመኖርን እንደ “የሽግግር ፍትህ” ለማቅረብ የሚደረጉ ሙከራዎች በሀገር ውስጥ እና በውጭ አገር እየጨመረ ባለው ጥርጣሬ እየታየ ነው።
ሶስተኛው የአቢይ አህመድ የህልውና ምሰሶ በተቃዋሚዎች መካከል የሚኖረውን ትብብር ወይም አንድነት ዘላቂ እንዳይሆን መከላከል፤ ተፈጠሯዊ የሆኑ ነባራዊ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና የማንነት ልዩነቶችን ሆን ብሎ እኩይ በሆነ መንገድ የግጭት ምንጭ አድርጎ የማስፋፋት ሙከራ ነው። የአካባቢ ግጭቶች ይቀጣጠላሉ ወይም በመሳሪያነት ይያዛሉ። የጎሳ እና የማህበረሰብ ማንነቶች ተመርጠው ይንቀሳቀሳሉ። በማህበረሰቦች መካከል ጥርጣሬ ይበረታታል።
አብይ ይህንን በዋናነት የሚጠቀመው ድንበር ተሻጋሪ የትግል ትብብሮችን አስቸጋሪ ለማድረግ ነው። በዓመቱ ውስጥ፣ ይህ አካሄድ የአካባቢ ጥቃት እና የበቀል ዑደቶችን አደጋ ለመጨመር እና የተለያዩ የፖለቲካ ትብብር ተስፋዎችን ለማዳከም ሞክሯል።
እነዚህ የአገዛዙ ሙከራዎች ቢኖሩም፣ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ከዋና ዋና የኦሮሞ ተቃዋሚ መሪዎች እና በአገዛዙ ውስጥ ካሉ ቁልፍ ደጋፊዎች ጋር በመሆን የኦሮሞን ትግል አንድነት ለማጎልበት የምናደርገው ውስጣዊ ጥረት ፍሬ ማፍራቱን ቀጥሏል። ወደፊትም የበለጠ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
ከኦሮሞ የፖለቲካ ማእቀፍ ባሻገር፣ ዴሞክራሲያዊ ምኞታችንን ከሚጋሩ ሁሉም ኃይሎች ጋር በመርህ ላይ የተመሠረተ ትብብር ለመገንባት ያለን ቁርጠኝነት ሁልግዜም የማይናወጥ ነው። ህዝባችን የራሱን መዳረሻ በነፃነት እና በአንድንት መወሰን እንዲችል ለማብቃት ስንል ከሁሉም የተቃዋሚ ኃይሎች ጋር በሙሉ ቁርጠኝነት መስራታችንን እንቀጥላለን። ከፊታችን ያለው ዓመት ወሳኝ ይሆናል።
የኦነግ-ኦነሰ ከፍተኛ ዕዝ
ጥር 11፣ 2026

