የኦሮሞ ህዝብ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ በሃበሾች አምባገነን አገዛዝ ስር ከወደቀበት ግዜ ጀምሮ፣ ግድያ እና ከቀዬው መፈናቀል ሳይቋረጥ 21ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ዘልቆአል። የኢምፓየሪቱ ገዢዎች ከየትኛውም ብሔር ቢመጡም የኦሮሞን እውነታ እና የመብት ጥያቄ በህጋዊ መንገድ ከመመለስ ይልቅ የትግል እንቅፋት በመሆን እና ታጋይ አመራሮችን በመግደል የኦሮሞን ህዝብ ባለራዕይ መሪዎችን እያሳጡት ከዚህ ደርሰዋል።
ዛሬም ይህንኑ ተግባራቸውን አሻፈረኝ በማለት በህወሓት/ኢህአዴግ ስር ሆነዉ “የራሴ ነው” የሚሉትን ዜጋ እንዴት እንደሚገድሉና እንዴት እንደሚሰውሩ በመማርና በመተግበር ባካበቱት ከፍተኛ ልምድ ላይ በመመርኮዝ “የሰላም ኮሚቴ” (ኮሬ ነጌኛ) በሚል ሽፋን የገዳይ ቡድን በመመስረት በጠ/ሚ አብይ አህመድ እዛዥነት እና በኦሮሚያ ክልል ፕሬዘዳንት ሺመልስ አብዲሳ አስፈፃሚነት፣ ኮሚቴው ንጹሃን ዜጎችን በመግደልና ደብዛቸውን በማጥፋት ላይ ይገኛል። ይህንንም የዓለም አቀፍ ሚዲያ የሆነው ሮይተርስ ባደረገው ምርመራ መሰረት ታዋቂ በሆኑ ኦሮሞዎች ላይ ግድያ እየፈፀመ መሆኑ አረጋግጧል።
በዚህ መሠረት ሚያዚያ 9/2024 በምሥራቅ ሸገር ዞን መቂ ከተማ ውስጥ የኦነግ ፖለቲካ ኦፊሰር ጃል በቴ ኡርጌሳ ቡላ ካረፉበት ሆቴል በሌሊት ከተኙበት ተቀስቅሰው ከተወሰዱ በኋላ እዚያው መቂ ከተማ ጊሪሳ ማዞሪያ በሚባለው ቦታ ላይ እጃቸው ወደ ኋላ የፍጥኝ ታስሮ፣ በስድስት ጥይት ተደብድበው ሞተው ተገኝተዋል። እንደዚህ አይነት አሰቃቂ ግድያዎች በአብይ አህመድ አገዛዝ የተለመዱ ሲሆን፣ አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን፣ የከረዩ አባ ገዳዎችንና ሌሎችንም እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይችላል። ይባስ ብሎ በሰላማዊ መንገድ ሃሳቡን የሚገልፅን፣ በትምህርት ደረጃው የላቀ፣ ከፍተኛ ልምድን ያካበተ ቆራጥ የህዝብ አገልጋይ፣ ጃል በቴ ኡርጌሳን መግደል የኦሮሞ ህዝብ አርቆ አስተዋይና ባለ ራዕይ መሪ እንዳይኖረው የተሸረበ ሴራ ሲሆን፣ የተቀሩት የኦሮሞ ፖለቲከኞች ደህንነት ጥያቄ ውስጥ እንደገባ ያሳያል።
ይህ ቡድን በራሱ ሰራዊት እና ከጽንፈኛው የአማራ ታጣቂ ቡድን ጋር ሆኖ ኦሮሚያ ውስጥ የሚፈጸመውን ግፍ ጨምሮ በዙሪያው በባዕድ ኃይሎች ከበባ ውስጥ ያለው የወሎ ኦሮሞ ሕዝባችንን በረመዳን ፆም ወቅት የብልፅግና ኃይሎች እና የጽንፈኛው አማራ ታጣቂዎች እየገደሉትና ቀዬውን በእሳት እያጋዩበት ነው። ስለዚህም የእሮሞ ህዝብ ከጥፋትና ከውርደት፣ ልጆቹን ቀብሮ ከንፈር ከመምጠጥ ይልቅ በአንድነት ተነስቶ ታግሎ መብቱን ማስከበር አለበት በማለት እንደ ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ አቋማችንን እናጸባርቃለን። ይህንንም በመመርኮዝ ህዝባችን፣ ቄሮና ቀሬ: የኦሮሞ ነፃነት ቄሮ የጠራውን ህዝባዊ እምቢተኝነት፣ የገበያ ዕቀባ እና የትራንስፖርት እገዳ ላይ እንድትሳተፉ አጥብቀን እናሳስባለን።
ሚያዚያ 13/2024 ከምሽቱ 12:00 ስዓት ጀምሮ ይህን መግለጫ እስከሚሰጥ ድረስ የኦሮሞ ህዝብ የጃል በቴ ኡርጌሳ እና እንደ ህዝብ የወሎ ኦሮሞን ጨምሮ እየተፈጸመ ያለውን ህገወጥ ግድያ በመቃወም የእኝህን የኦሮሞ መሪን ሀቅና ለሌሎቹ በግፍ ለተገደሉት ኦሮሞዎች ለፍትህ መጠየቅና ፍትህ ለማስፈን ተጠናክረን ግፊት ማድረግ አለብን። የተባበረ ህዝብ ድምፅ እንዳለው እናምናለን፣ ስለዚህም ልጆቻችንን ከእኛ እየነጠለ በመጨረስ ላይ ያለውን የብልፅግና ቡድንን አረመኔነት ለማስቆም እምቢተኝነታችንን መቀጠል እንደሚያስፈልግ እናምንበታለን፤ ስለዚህም የጀመርነዉን ተቃውሞ በማጠናከር ወደፊት መራመድ አለብን።
የኦነግ ፖለቲካ ኦፊሰር ጃል በቴ ኡርጌሳ መገደልን እና እንደ ህዝብ በኦሮሞ ላይ እየተካሄደ ያለው አሰቃቂ ግድያ ለመቃወም በሚደረገው ህዝባዊ ተቃውም ውስጥ የተከለከሉ ነገሮች፦
- በኦሮሚያ ውስጥም ሆነ ከሌሎች ክልሎች ጋር የሚያገናኝ ማንኛውም የትራንስፖርት እንቅስቃሴ አይኖርም (ከሞተር ሳይክል ጀምሮ እስከ ከባድ መኪና ድረስ)
- በኦሮሚያ ውስጥ ምንም አይነት የንግድ እንቅስቃሴ አይኖርም (ሱቆች ዝግ ናቸው፤ ገበያም አይኖርም)
- ትምህርት ቤቶች ዝግ ናቸው
- የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ዝግ ይሆናሉ
- ባንክና ቴሌ ዝግ ይሆናሉ
- የተቃውሞ ሰልፍ እንደ አመቺነቱ ይደረግጋል
- ጥቁር ልብስ ተለብሶ
- ነጭ ጨርቅ እጅ ላይ ይታሠራል
ከላይ የተጠቀሱት እርምጃዎች በኦሮሚያ ውስጥ ሲካሄድ በዉጪ አገር የሚገኙ ኦሮሞዎች ደግሞ፦
- የተቃውሞ ሠልፍ ባሉበት ሀገር የመንግሥቱ ጽ/ቤት ፊት ለፊት ይወጣሉ
- ጥቁር ልብስ ይለበሳል፣ በእጃቸው ላይ ነጭ ሪባን በማሰር፣ የጃል በቴን ፎቶ እንዲሁም የወሎ ኦሮሞን እና የመላው ኦሮሞን ግድያን የሚገልፅ ፎቶዎች በመያዝ በብልፅግና አገዛዝ ላይ የተቃውሞ መፈክር ያሰማሉ
- ለሀገራቱ መንግሥታት ጽ/ቤት ስለተቃውሞው የሚገልፅ ደብዳቤ ለሚመለከተው ይገባል
ተሽከርካሪ ያላችሁም ሆነ አሽከርካሪዎች ይሄንን የኦሮሙማ ጥሪ ተቀብላችሁ ከቤት እንዳትወጡ በማክበር እናሳስባለን።
ህዝባችንም ይህንን ጥሪ በሰፊው በመረዳት መግዛት ያለባችሁን በመግዛት በቤታችሁ በመሆን ይህንን እምቢተኝነት እንድትሳተፉ እንዲሁም በዚህ የእምቢተኝነት ተቃውሞ ምክንያት ከሚደርሰው አደጋ ለመራቅ ከመንቀሳቀስ ተቆጥቡ እንላለን። ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞም በተለያዩ ቦታዎች ህዝባችንን በማንቃት በዚህ እምቢተኝነት ላይ መሳተፍ እንጂ በሰብዓዊና በንብረት ላይ እርምጃ መውሰድ ወንጀል መሆኑን አውቃችሁ የሰላማዊ ትግል ሥርዓት ተግባራዊ እንድታደርጉ እናሳስባለን።
ይህ የገበያ ዕቀባና የትራንስፖርት እገዳ ማንሳት ህጋዊ ስርዓቱን በተከተለ መንገድ በአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO) መግለጫ እስከሚሰጥ ድረስ አዋጁ ፀንቶ ይቆያል። ስለዚህም ይህንን ተቃውሞ ለማደናቀፍ ብልፅግና እና ሌሎችም በተለያየ አቅጣጫ በሚፈጥሩት ውዥንብር እንዳትረበሹ እንላለን።
አንድነት ኃይል ነው!
ቀብረን አናለቅስም! #ህዝባዊ_እምቢተኝነት
የኦሮሞ ነፃነት ቄሮ
ድል ለኦሮሞ ህዝብ!
ሚያዚያ 13, 2024
ፊንፊኔ-ኦሮሚያ

