Site icon Qeerroo Bilisummaa Oromoo

የጄነራል ብርሃኑ ልመናና ማታለል በምዕራብ ኦሮሚያ

ቡድኑ 2018 የኦሮሞን ህዝብ አብዮት ጠልፎ ስልጣን ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ ህዝቡ የተሻለ ኑሮን የመኖር ተስፋውን፣ በሰላም ወጥቶ የመግባት መብቱን ተነጥቆዋል። መዘረፍ፣ መቀጥቀጥ፣ አሰገድዶ መደፈር፣ በግድ ታፍኖ ወደ ጦር ማሰልጠኛ መጋዝ የኦሮሞ ህዝብ እጣፈንታ ከሆነ ውሎ አድሮዋል።

ሰላም እንደምን ከረማቹ የተከበራቹ የአራታ ቢዮሌሳ አድማጭ ተመልካቾቻችን ዛሬ የብርሃኑ ጁላ ልመና እና የማታለል ሙከራ በምዕራብ ኦሮሚያ የሚለውን ፕሮግራም የማቀርብላቹ እኔ ሃቃፈን ፈዬራ ነኝ። እስከ መጨረሻው ትከታተሉኝ ዘንድ ግብዣችን ነው።

በአሁኑ ዘመን አንድ ሀገር የተሻለች ሰለመሆኗ በዓለም ላይ የምትደነቅበት ጉዳዮች፦ የተሻለ ዲሞክራሲ፣ የሰብዓዊ መብት አያያዟ ጥሩ ሲሆን እና በአጠቃላይ የዛች ሀገር ዜጎች በሁሉም ሴክተሮች ውስጥ ስራ ተሰርተው ራሳቸውን እንዲለውጡ ማገዝ እንደ ሆነ ይታወቃል።

በዚህ ሳምንት የአብይ አህመድ ሚዲያዎች በሴንጋፖር ሰውዬው ያደረገውን ጉብኝት ሲዘግቡ አይተናል። ሴንጋፖር እንደነ ኬኒያ በ20ኛው ክ/ዘመን ውስጥ ማለትም ከ1960 በኋላ እንደ ሀገር ተመስርታ ዛሬ ሴንጋፖር ፈጣን እድገት ካመጡ ሀገራት ተርታ ተሰልፋ ለዜጎቿ የተሻለ ኑሮ እንዲኖራቸው አድርጋለች።

ሴንጋፖር በኢንግሊዝ ቅኝ ግዢ ስር ነበረች ነገር ግን ዛሬ ላይ ባስመዘገበችው አስደናቂ እድገት ከዜጎቿ አልፋ ለሌሎች ምሳሌ መሆን ችላለች።

ዛሬ የኢትዮጵያ ኢምፓየር ረዥም
ታሪክ አለን የሚሉት ዜጎቻቸውን ለመቀየር ምግብ መጠጥ እና የትምህር አገልግሎት ከመስጠት ይልቅ ክላሽ እና ሞርታር በመላክ ለአካል ጉዳት እና ለንብረት ውድመት እንዲዳረጉ አድርጓቸዋል።

የብልጽግና አይነቱ ቡድን በአፉ የሰላም ከበሮ እየደለቀ በእጁ የጦር መሳሪያ ቃታ እየሳበ ግድያ እየፈፀመ፣ ካቢኔው እና ጦሩ ደግሞ ህዝቡን እያታለሉት ይውላሉ።

ባለፈው ሃሙስ ሰኔ 6, 2024 በምዕራብ ኦሮሚያ ቄለም ወለጋ በደምቢ ዶሎ ከተማ በመገኘት አራት፣ አራት የሃይማኖት አባቶችን በዞኑ ከሚገኙት ወረዳዎች እና ከተማዋ አሰተዳደር ውስጥ ተመርጠው በሰላም ጉዳይ ላይ ከጀኔራል ብርሃኑ ጋር ተወያይተዋል።

እውሸት፣ ማታለል፣ ማስመሰል፣ ማስፈራራት እና የሌለ ተስፋ ሲሰጥ እና ብርሃኑ እንደ ጦር መሪ ሳይሆን እንደ ብልጽግና ካድሬ ሲናገር ነበር። ይሄው ግለሰብ ባለፈው ጊዜ እኛ የፖለቲካ ፓርቲ አደለንም ከህዝቡ ጋር እና ከሚመጣው ማንኛውም መንግስት ጋር ልንሰራ እንችላለን በማለት ሲናገር የነበረውን ትቶ ከሚድያው ውጪ ህዝቡን ማታለል፣ ለብልጽግና መስራት፣ ለአብይ መላላክ እና ስልጣን ላይ መቆየት እንደሚፈልግ ሲናገር ነበረ።

የቀድሞ TPLF ምርኮኛ እና ተላላኪ የዛሬው የብልጽግናው ገዳይ ጀነራል ብርሃኑ ጁላ በደንቢዶሎ መድረክ ላይ በውይይቱ ላይ ለነበሩት ሃይማኖት አባቶች እና ሽማግሌዎች፦ የኦሮሞን መንግስት ለመጣል ፋኖ እና ኤርትራ ተባብረው እየሰሩ ይገኛሉ፣ እኛ ደግሞ ተግባብተን የውስጥ ችግሮቻችንን እንዴት መፍታት እና ኦነሰን እንዴት እናስገባለን በሚለው ላይ ሃሳቡን ሲሰነዝርላቸው ነበረ።

ወደ ተሳታፊዎቹ መልስ ከመግባታችን በፊት። የኦሮሞ መንግስት ማነው? የኦሮሞ መንግሰት በሚለው ማታለያ ቃል ስልጣን ላይ ለመቆየት የሚሰራ አውሬ ተቀባይነት የለውም። የድሮ OPDO የዛሬው ብልጽግና የኦሮሞ መንግስት አይደለም ኦሮሞን መወከል አይችልም። ጄነራል ብርሃኑ ፋኖ እና ኤርትራ ተባብረው መንግስታችንን ሊጥሉ እየሰሩ ነው የሚለውን ንግግርም ብናይ፣ የእውነትም እየሰሩ ከሆነም ኢምፓየርዋን ለማቆየት የሚሰራን ብድን ለመጣል ነው። ይሁን እንጂ እውነታው ብርሃኑ ጁላ እና አብይ አህመድ ፋኖን እና የኤርትራን ሰራዊት ጋብዘው በዙ ህይወት አጥፍተዋል።

በፓርላማ ላይም የራስ ጥላ እንኳን በሚከዳበት ኤርትራ ትልቅ ውለታ ውላልናለች በማላት ህዝባችንን ስትገድል የነበረችውን ኤርትራ ሲያንቆለጳጵስ፣ ፋኖን ደግሞ እስከ ሶማሌ ክልል አዘምታለው ሲል ተደምጦ ነበር። ዛሬም በብልጽግና እውቅና በምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ እና ሰሜን ሸዋ ውስጥ በህዝባችን ላይ ከባድ ጉዳት በማድረስ ላይ ይገኛሉ።

ብልጽግና፣ ፋኖም ሆነ ኤርትራ ማንኛው ከብልጽግና ጋር ተሰልፎ ህዝባችንን የገደለ ያስገደለ እንዲሁም የኦሮሞ ህዝብ ጭቆና ስር እንዲቆይ የሚሰራ ማንኛውም አካል የኦሮሞ ህዝብ ትግል ጠላት ነው።

ብርሃኑ ጁላ፦ አንድነት የለንም፣ በውስጥ አንድ እንሁን፣ ልጆቻችሁን አስገቡ፣ ኤርትራና እና ፋኖ ተባብረው መንግስታችንን ሊጥሉ ነው በማለት ቢናገርም ከተሰብሳቢዎቹ መልስ አላገኘም።
“በድርጅት ደረጃ ከሚንቀሳቀሰው ጦር ጋር በመነጋገር መፍትሔ ታስቀምጣላችሁ እንጂ እኛን ይዛችሁ አሁን በምታወሩት ምርጫ እና ሀገራዊ ምክክር የሚመጣ ሰላም የለም” ብለዋል ታዳሚዎቹ።

“ሰዎቹ እናንተን የተጠራጠሩበት ምክንያት አላቸው። ሁሉም የብልጽግናን ጥቅም እና ስልጣን ላይ ስለመቆየት ያወራል። ይህን ደግሞ እንኳን ኦነሰ ህዝቡ ራሱ በእናንተ ላይ ጥርጣሬ አለው።” አንድ ከአንፊሎ ወረዳ የመጣ ተሳታፊ እንዲህ በማለት ብርሃኑ ጁላን አበሳጭቶታል “እንዲያውም የሚቃወማችሁ ህዝብ አለ። የኦሮሞን ሕዝብ ችግር ኦነሰ ካልተሳተፈበት የሚፈታ ችግር የለም።” በማለት በድፍረት ተናግረዋል።

ሲጠቃለል የብልጽግናው የጦር አዛዥ ብርሃኑ በደምቢ ዶሎ እና ነቀምቴ ከተሞች ከሽማግሌዎች እና ከሃይማኖት አባቶች ጋር ያደረገው ተመሳሳይ ውይይቶች፣ ተሳታፊዎቹ “እኛ የምናውቀው ነገር የለንም። እኛ የምንላችሁን አትቀበሉም። ህግ አክብሩ፣ ኦነሰ የሚላችሁን ተቀበሉና ችግራችንን ፍቱ። ቀሪውን ደግሞ እኛ በምርጫ እንወስናለን።” በማለት መልስ ሰጥተዋል።

በመድረኩ ላይ የተለያዩ የማታለያ ሃሳቦች ቢቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። ይሁን እንጂ ብልጽግና ተቀባይነትን ለማግኘት ብዙ እየለፋ ይገኛል። በተለይ ለወደፊቱ የውሸት ምርጫ እየተዘጋጀ ይገኛል። ሕዝባችን ስድስት ዓመት ሙሉ ብልጽግና ሲያወራ የነበረው ንግግሮች ሁሉ ውሸት እንደነበሩ በመገንዘብ የኦሮሞን ሕዝብ የሐገር ባለቤትነት እና ነጻነቱን ለመጎናፀፍ አለኝታው የሆነውን ከኦነሰ ጎን በመቆም ትግሉን እንዲያቀጣጥል ጥሪ በማቅረብ ፕሮግራሜን እቋጫለው።

ከአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ባለሞያውች ጋር አዘጋጅቼ ያቀረብኩላችሁ እኔ ሃቃፈን ፈዬራ ነኝ።

ሆራ ቡላ!

ድል ለኦሮሞ ህዝብ!

Exit mobile version