Site icon Qeerroo Bilisummaa Oromoo

በምዕራብ ወለጋ ዞን፣ ቂልጡ ካራ፣ ነጆ፣ ለታ ሲቡ፣ መና ሲቡ እና ጃርሶ ወረዳዎች ውስጥ የፋሺስቱ ብልጽግና ሰራዊት ዘረፋ፣ አፈና፣ እስራት እና ግድያን አጧጡፎ ቀጥለዋል 

ግንቦት 19፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ህዝብ ላይ ጭካኔ የተሞላበት ግድያ፣የዝርፍያ፤እስራት ወንጀሎችን አጠናክሮ እየፈፀመ መቀጠሉ የታወቀ ስሆን፣በዚሁ መሰረት

የማፍያው ብልፅግና ሰራዊት በጀግናው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የደረሰበትን ክስረት ተከትሎ ሰላማዊ ኦሮሞዎችን መዝረፍ፣ ማሰር፣ በጅምላ አፍኖ የደረሱበትን ማሳጣት እና ጭካኔ የተሞላበት ግድያን አባብሶ ቀጥሏል።

ቂልጡ ካራ ወረዳ

ሚያዝያ 30፣ 2024 በዋንዲ ዳሌ ቀበሌ፣ ዶዮ በሚባለው አካባቢ ከቄሮ አብዲ ቡልቴ ሞተር ብስክሌቱን በመዝረፍ ወደ ቂልጡ ጫራ ከተማ ጭነው መውሰዳቸው ለአቢኦ ተናግረዋል።

ሚያዝያ 29፣ 2024 የፋሺስቱ ብልፅግና ቡድን በዚሁ ቀበሌ፣ ኦቦ ዋና በየና፣ ኦቦ ሰንበቶ አቶምሳ እና ኦቦ መልካሙ ነገሪ የሚባሉትን ሰላማዊ ሰዎች ማሰራቸው ተረጋግጦዋል።

ሚያዚያ 15፣ 2024 በቡንዲ ዳሌ ቀበሌ ውስጥ የፋሺስቱ ብልፅግና ሰራዊት ሁለት ቄሮዎችን ዱላ ሻፌ ኤጄርሶን እና ታሪኩ መንገሻን ክፉኛ ሲያቆስሉ፣ ቄሮ አብርሃም መንገሻን መግደላቸውን ለአቢኦ ተናግረዋል። 

በዚሁ ወረዳ ውስጥ በቡኬ አካቼ እና ውስጥ ዝርፊያ አጧጡፈው ቀጥለዋል። ዋንዲ ዳሌ ቀበሌ ውስጥ ቱሉ-ዋንዲ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ከኦቦ ቂጣታ ቤት ከራሳቸው ንብረት ሌላም የዕድር እና የሃይማኖት እቃዎችን ሁሉ ዘርፈው ሄደዋል። ከኦቦ ዋቅኬኔ ደሳኣ ቤት ለመስራት የገዙትን ቆርቆሮና የቡና ሚዛን ሲወስዱ ኦቦ ተርፋሳ ደሳ የሚባሉትን ደግሞ ይዘዋቸው መሄዳቸውም ታውቆዋል። 

ነጆ ወረዳ 

ሚያዚያ 15፣ 2024 ከአቦኖ ዲላ ቀበሌ፣ ወሎ በሚባለው አካባቢ ይኖሩ የነበሩትን ደረጄ ሆርዶፋ የሚባሉትን ግለሰብ የብልፅግና ሚሊሻ ይዞ ወደ ጃቦ ቀበሌ ወስዶ እዚያው ገድሎዋቸው ተገኝተዋል። 

ለታ ሲቡ ወረዳ

ሚያዚያ 16፣ 2024 በጎሪ ከተማ 02 ቀበሌ ውስጥ ቄሮ ማርቆስ ሰንበታን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደሉ አቢኦ  መረጃ አግኝቶዋል። 

መና ሲቡ ወረዳ 

ሚያዝያ 19፣ 2024 ቀላ ዳቡስ ቀበሌ ውስጥ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በፋሺስቱ ብልፅግና ሰራዊት ላይ ወታደራዊ እርምጃ መውሰዱ ተከትሎ ኦቦ ጂሬኛ እና ኦቦ ቡልቲ የሚባሉትን ሰላማዊ ሰዎች በኢምፓይሪትዋ ሰራዊት ስገደሉ፣ ከ25 በላይ ኦሮሞዎችን ደግሞ ወደ ቤንጋኣ ከተማ መወሰዳቸው ታውቋል።

ጃርሶ ወረዳ

ሚያዚያ 20፣ 2024 በኦሮሚያ ውስጥ ለመግደል የተሰማራው የፋሺስት ብልፅግና ጦር ሳሙኤል ተስፌ ጃርሶን እና አብዲ ሃፍቴ የተባሉ ቄሮዎች በጃርሶ ወርዳ 01 እና ኦዳ Dhንቃ ቀበሌዎች ውስጥ ጥይት እላያቸው ላይ አዝንበው ገድለዋቸዋል። ቄሮዎቹ በአካባቢው ሕዝብ ከመወደድም በላይ ብሩህ እና የወደፊት የሐገር ተስፋዎች እንደነበሩም ለአቢኦ ተናግረዋል።

እነዚህ የተገደሉት ወጣቶች ቄሮና የነገ የአገሩቱ ተስፋዎች እነደነበሩ ኗሪዎች ይናገራሉ፤ በተጨማሪም የነዚህ ልጆች መገደል አከባቢውን ህዝብ እንዳስቆጣም ተናግረዋል።

ፋሺስት አብይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦

“የኦሮሞን ሕዝብ መዝረፍ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ማድረግ፣ ከዚህም እልፎ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ እና ለዱር አራዊትም እንዲጣሉ ትዕዛዝ የሚሰጥ የ አውሬነት ባህርይ የተላበሰ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኤምፓየሪትዋ ያስተናገደች፣ ሰብዓዊነት የጎደለው የለየለት ጨካኝ አምባገነ መሪ ነው።”

Exit mobile version