Site icon Qeerroo Bilisummaa Oromoo

የፋሺስቱ ብልፅግና ስርዓት ሰራዊት በምዕራብ ሸገር ዞን የእሮሞን ህዝብ ክፉኛ መደብደብ፣ ሃብቱን መዝረፍ፣ ቤት ከነንብረት በእሳት ማውደም እና መግደል በሰፊው ቀጥሎበታል

ሰኔ 21፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

ይህ ለመውደቅ የተቃረበው የማፍያው ብልፅግና ቡድን በሰላማዊ የኦሮሞ ዜጎች ላይ አሰቃቂ ግደያ፣ አስሮ ማሰቃየት፣ መዝረፍ እና ቤትና ንብረትንም ማውደሙን ስራዬ ብሎ ቀጥሏል። ከዚህም ሌላ እነዚህ የስርዓቱ ታጣቂዎች በብዙ ቦታ የህዝቡን ሥነ-ልቦና በመጉዳት ላይም ይገኛሉ። 

ደንዲ ወረዳ

የብልፅግና ስርዓት ጠባቂዎች በዳኒሳ ሾኖ ቀበሌ ውስጥ ሰኔ 6፣ 2024 ወደ መንደሩ ገብተው የህዝቡን የቀንድ ከብቶች ዘርፈው ነዋሪዎቹም ላይ የአካል ጉዳት የሚያደርስ ከባድ ድብደባም ሲፈጽሙ ውለዋል።

በዚህ መሠረት እነዚህ ታጣቂዎች ከኦቦ ገረመው ሶና አንድ የደለበ ከብት እንድሁም ከኦቦ ኩማ ጫላ አንድ ላም ከነ ጥጃዋ ዘርፈው ወደ ጋሌሳ ከተማ እንደሄዱ የቀበሌው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል። እነዚህ የተዘረፉትም ግለሰቦች ኑሮዋቸው ደካማና እና ለግለሰቦች የግብርና ስራዎችን በመስራት ቤተሰባቸውን የሚያስተዳድሩ ሲሆን፣ በዚህ ድርጊት እና የዛቻ መልዕክት የቤተሰቦቻቸው የኑሮ ሁኔታ ችግር ውስጥ ገብቷል።

ጀልዱ ወረዳ

ሰኔ 3፣ 2024 በቀርሳ ምርጢ ቀበሌ ውስጥ የፋሽስቱ ብልፅግና ሰራዊት ኦቦ ፈዬ ደንደአ ከሚባሉት ግለሰብ መዝረፍ የሚችሉትን ንብረት ዘርፈው የቀረውን ንብረታቸውን ከሁለት ቤታቸው ጋር በእሳት አጋይተው አውድመውባቸዋል። አንዱ ቤት ባለ 65 ቆርቆሮ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ 30 ቆርቆሮ እንደሆነና የቤት ውስጥ መገልገያዎች አንድም እንዳልወጣ እና ሙሉ በሙሉ ማቃጠላቸውን ለአቢኦ ዘግበዋል።

በተጨማሪም በተመሳሳይ ቀን እዛው ቀበሌ ውስጥ ለጊዜው ስማቸው ያልታወቁ የሶስት ሰዎችንም ንብረት እንደዘረፉ ታውቋል።

ኡጫሌ ወረዳ 

የፋሺስት አብይ አህመድ ብልፅግና ገዳይ እና አውዳሚ ቡድን ግንቦት 27፣ 2024 የሚከተሉትን ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶች በበቾ ፋልሚ ቀበሌ ውስጥ ሲፈፅም ውለዋል።

  1. ሶስት ንፁሃን ኦሮሞዎችን ገድለዋል
  2. 23 የገበሬ ቤቶችን በእሳት አውድመዋል
  3.  ሁለት ቀሬዎችን፥ ቡርቱካን አምበሳ እና መገርቱ መንጋሳ የተባሉትን ተኩሰው አቁስለዋቸዋል። እነርሱም ህክምና እንዳያገኙ በመከልከላቸው ለህይወታቸውም አስጊ ሁኔታ ላይ እንዳሉ ለአቢኦ ምንጮች አክለው ገልፀዋል።

ይህንንም የዘር ማጥፋት ድርጊት የሚፈጽሙት የቀበሌውን ነዋሪዎች በሙሉ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ናቸው በሚል የሃሰት ውንጀላ መሆኑን የቀበሌው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል። አክለውም “በእርግጥ ወቅቱ የእርሻ ወቅት ነው ሆኖም ግን ህዝብን ለማጥፋት ተደራጅቶ በመጣብን የፋሺስት ኃይል እቤታችን ተኝተን ከምንገደል፣ በአንድነት ተፋልመን ስርዓቱን ከጫንቃችን ማራግፍ የሚገባን ግዜ አሁን ነው።” ብለዋል። 

ባኮ ቲቤ ወረዳ

ግንቦት 12፣ 2024 የፋሺስቱ ብልፅግና ጦር ቡድን በአዱላን ቀበሌ ነዋሪዎች ላይ ያነጣጠር ተኩስ ከፍተው የሰዎችን ቤትም ሙሉ በሙሉ ፍተሻ ሲያደርጉ እንደ ነበረ ተናገሩ። በዚህም የሽብር ጥቃት ኦሉማ ቤኛ የተባለ ግለሰብ ሊገድሉት አነጣጥረው ቢተኩሱም ስለሳቱና ስላልሞተ ከባድ ድብደባን እንደፈጸሙበት የአካባቢው  ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናገራሉ።

ልጃቸው ባለመሞቱ የተቆጩት የፋሺስት አብይ አህመድ የጦር ሎሌዎች  በእድሜ የገፉትንም አባቱን ኦቦ ቤኛ ጀቤሳን ክፉኛ ጭንቅላታቸውንም ጭምር በመደብደባቸው ለተወሰነ ሰዓታት ራሳቸውን ስተው እንደነበረ የቀበሌው ነዋሪዎች ገልጸዋል። 

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያወጀው የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት እና የሀገር ባለቤትነት እስኪረጋገጥ ድረስ በተለየ መልኩም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሎአል።

Exit mobile version