Site icon Qeerroo Bilisummaa Oromoo

ጀግናው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በሰሜን ኦሮሚያ በወሎ ዞን እና በደቡብ በቦረና ዞን እየተክለፈለፈ የሚመጣውን የጠላትን ጦር አድፍጦ በማጥቃት የተወሰኑትን ወደማይመለሱበት ሲሸኝ በርካቶችን አቁስሎ ብዙ መሳሪያም ለነፃነት ትግሉ ገቢ አድርጓል

ሐምሌ 10፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

የታላቁ የኦሮሞ ህዝብ ጋሻና መከታ የሆነው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሽኒጋውን ቃል-ኪዳን ዘመቻ በማጠናከር የፋሺስት አብይ አህመድን ተላላኪዎች ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ በሚያደርገው የተቀናጀ የማጥቃት እርምጃ እያስበረገገ፣ እያደነጋገጠ እና እያስፈረጠጠ አኩሪ ድሎችን ማስመዝገቡን ቀጥሎበታል።

ቦረና ዞን፣ በአሬሮ ወረዳ

የደቡብ ዞን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ‘ጭብራ መዳ አልቡዳ’ እና ‘ጭብራ መታ ገፈርሳ’ በተቀናጀ መልኩ ሰኔ 27፣ 2024  ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በዳዋ ሪቂቻ መንደር አካባቢ ባደረጉት አድፍጦ የማጥቃት እርምጃ የአሸባሪውን የአብይ አህመድ ጦር፣ ‘የጋሞ ጦር’ ተብሎ የሚጠራው ሊያገግም በማይችልበት ደረጃ ጉዳት አድርሶበታል።

በዚህ ከባድ እርምጃም የፋሽስት ብልፅግና ጦር ሙትና ቁስለኛ በቁጥር በርካታ እንደሆነ የኦነሰ የአካባቢው ቃል አቀባይ ለአቢኦ አሳውቆዋል። አክሎም የፋሽስት ብልፅግና ጦር ከተጎዱበት መካከል ማለትም የተወሰነ አስከሬን እና ቁስለኞችን መርጦ በአምስት አይሱዙ መኪና እና በሶስት ፓትሮል ወደ ዱራሜ ከተማ ማጓጓዙን ገልጾዋል።

እነዚህ ‘የጋሞ ጦር ወታደሮች’ ተብለው የሚጠሩት ከዚህ በፊትም ሶዶም ቦሮ ላይ በተወርዋሪው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ኃይል ተመትተውም ነበር። ይሁን እንጂ ሸጢ አካባቢ ያለውን የመዓድን እና የወርቅ ክምችት ብዝበዛ እና ኮንትሮባንድ ላይ ተሰማርተው ከሚሰሩ ባለሃብቶች ጋር በመመሳጠር የጠላት አጋሮች ሆነው እየሰሩም እንደነበረ ታውቋል። 

ወሎ ዞን፣ ሃርጡሜ ፉርሲ ወረዳ

በሰሜን ዞን የኦሮሞ ህዝብ ተስፋ የሆነው የኦነሰ ሀራ ዳሬሳ በምትባል ከተማ ውስጥ ሰኔ 23፣ 2024 ከምሽቱ 5:00 ሰዓት እስከ ለሊት 8.00 ስዓት ድረስ ባደረገው የማጥቃት እርምጃ በ10 መኪና ተጭኖ ከመጣው የብልፅግና ወራሪ ሰራዊት 18ቱን በሙት እና 25ቱን ደግሞ ክፉኛ አቁስሎ ሸኝቶዋቸዋል።

ከዚህም በላይ በመሳሪያ በኩል፦

በተጨማሪም አንድ የፋሺስት ብልፅግና ፖሊስ ሲማርክ የተረፋት ሙት እና ቁስለኞቻቸውን ሰብስበው ተጨማሪ ኃይል እንዲመጣላቸው ጠይቀው እየተጠባበቁም እንደነበር የአቢኦ ምንጭ ተናግሮዋል። 

#የሺኒጋው_የቃልኪዳን_ዘመቻ ይቀጥላል

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያወጀው የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት እና የሀገር ባለቤትነት እስኪረጋገጥ ድረስ በተለየ መልኩም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሎአል።

ድል ለኦሮሞ ህዝብና ለጭቁን ብሔር ብሔረሰቦች!

Exit mobile version