ነሐሴ 13፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
የመደ አልቡዳ ዞን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት፣ የቢፍቱ በሪ ብርጌድ እና የለገ ደንቢ ጭብራ ጥምር ኃይል ሐምሌ 29፣ 2024 በምስራቅ ጉጂ በሰባ ቦሩ ወረዳ ውስጥ የፋሽስት ብልፅግና የጦር ኃይል፣ ከአራት ቀበሌዎች አንድ ላይ በመሰባሰብ በኦዴ ቀበሌ እና በዱበና ቀበሌ ውስጥ የህዝቡን ሃብት ሐምሌ 28፣ 2023 በእሳት እያጋዩ ሲያወድሙ የነበሩትን ጠዋቱ 1:30 እስከ 5:40 ሰዓት በወሰደው የማያዳግም አድፍጦ የማጥቃት እርምጃ አኩሪ ድል አስመዝግቧል።
በተጨማሪም ሐምሌ 29፣ 2024 ወደ 6:30 ሰዓት አከባቢ የብልፅግና አጋዥ ኃይል ከሰባ ቦሩ ወረዳ፣ በስሬ ቡቂ ቀበሌ በኩል ውስጥ ለዉስጥ በሩጫ ሲያልፍ በነበረው ላይ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አድፍጦ በመጠበቅ በወሰደው እርምጃ ሙታቸውን እና ቁስለኞቻቸውን አስይዞ ወደ መጡበት ወደ ኃላ መልሶአቸዋል።
ሕዝቡን ነፃ ለማውጣት ፅኑ አቋም ያለው፣ አንበሳው እና አይበገሬው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የማፍያው የአብይ አህመድ የጦር ኃይል ላይ በሁለት ቀናት ውግያ፦
- የሺ አለቃ አብራሃ ነጋሽ ሞኮነን ጨምሮ ከ 100 በላይ የጣላትን ጦር ከአፈር ቀላቅሎዋል።
- ብዙ ቁጥር ያላቸውንም በማይሽር ቁስል ሸኝቷል።
- አምስቱን የፋሽስት ብልፅግና ጦር አባል በመማረክ አኩሪ ድል አስመዝግቦዋል።
ጀግናው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ከላይ በተጠቀሱት ቦታዎች ባደረገው ውጊያ በሙት፣ በማይሽር ቁስለኛነት እና የፋሺስት አብይ ዙፋን ጠባቂዎችን ከመማረክና የተረፉትም እግር አውጪኝ ብለው ከመፈርጠጥ ጎን ለጎን የሚከተሉትን የጦር መሳሪያዎች፦
- አንድ ድሽቃ
- ከ 1000 በላይ የድሽቃ ጥይቶች
- አንድ ኢስናይፐር
- ከ 1500 በላይ የPKM ጥይቶች
- 20 AKM ክላሽ
- ከ 1630 በላይ የ AKM ክላሽ ጥይቶች ከጠላት ጀርባ በመፍታት ለነፃነት ትግሉ ገቢ አደርጓል።
በዚህም የጥቃት እርምጃ የኢምፓየሪትዋን ዙፋን ጠባቂዎች እና የፋሺስት ብልፅግና መሪዎችን ሲያስደነግጥ የትግሉ አባት የሆነውን የኦሮሞ ህዝብን ደግሞ አኩርቷል።
#የሺኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ ይቀጥላል!
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያወጀው የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት እና የሀገር ባለቤትነት እስኪረጋገጥ ድረስ በተለየ መልኩም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሎአል።
ድል ለኦሮሞ ህዝብና ለጭቁን ብሔር ብሔረሰቦች!

