ሐምሌ 13፣ አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
የኦሮም ነፃነት ሰራዊት በስምንቱም ዞኖች የሀርሰዲ ዞንንም ጨምሮ የኢምፓየሪቱ እምብርት ፊንፊኔ ዙሪይም በጠላት ጦር ቡድኖች ላይ ላይ የሚወሰደው ስኬታማ የማጥቃት እርምጃ እንደቀጠለ ነው።
የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት የሀርሰዲ ዞን የጨፌ ቱማ ብርጌድ፣ ኤረር ኮርማ ጭብራ
ሊበን ጩቃላ ወረዳ
አንበሶቹ የኦነሰ የጨፌ ቱማ ብርጌድ የኤረር ኮርማ ጭብራ፤ ጩቃላ ተራራ ላይ ሙሚቻ በሚባል መንደር አካባቢ ሐምሌ 3፣ 2024 ምሽት ላይ ህዝብን ሲያሰቃይ የነበረውን የቅኝ ገዢው ብልፅግና ጦር በሁለት ፓትሮል ወደ ከተማ ለመግባት እየገሰገሰ እንዳለ አድፍጦ የማያዳግም እርምጃ ወስዶዋል። በዚህም የማጥቃት እርምጃ 13ቱን ከደቼ ሲቀላቅል አምስቱን ደግሞ በማያገግም ቁስል ቀጥቷል።
አነሮቹ የኦነሰ የኤረር ኮርማ ጭብራ ግንቦት 28፣ 2024 በወሰደው አድፍጦ የማጥቃት እርምጃ የፋሺስት ብልፅግና ሰራዊት ክፉኛ ተደናግጦ ነበር። በዚህም ሽንፈታቸው የፋሺስት አብይ አህመድ ዙፋን የመደርመሻ ቀናቶች እየተቃረበ መሆኑን ቢገባቸውም አልሞት ባይ ተጋዳይነታቸውን ለማሳየት ሰኔ 29፣ 2024 ከዱግዳ እና ቦራ ወረዳዎች ያሉትን ኃይሎቻቸውን በማሰባሰብ ተደራጅተው በመጓዝ ላይ እያሉ አንበሳው የኦነሰ በቦራ እና ዱግዳ ወረዳዎች ድንበር፣ ልዩ ስሙም ጮሬቲ በሚባል ቦታ ላይ ከብቦ እርም የሚያስብል ውጊያም አካሂዶ በርካቶችን ወደ እማይመለሱበት አለም ሸኝቶዋል።
ይህንንም እርምጃ የኦነሠ የወሰደው ከጠዋቱ 4:30 እስከ እኩለ ቀን 6:00 ሰዓት ድረስ ነበር። በዚህም ውጊያ ከ240 የፋሺስት አብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂዎች 69 ገድሎ 26 ደግሞ ክፉኛ በማቁሰል ሸኝቶዋቸዋል።
አያርሜዎቹ ተጨማሪ ኃይል በማቀናጀት ሬሳቸውን እና ቁስለኞቻቸውን ለማንሳት ቢያመጡም እነሱንም ነብሩ የኦነሰ ቀደም ብሎ በማረካቸው ቦምብና ጥይቶች 14ቱን ከአፈር ቀላቅሎ በርካታ ቁጥር ያላቸውንም በማቁስል የተረፉትም ወደ ኋላ እንዲሸሹ እስገዶ።ዋቸዋል።
ዱግዳ ወረዳ
ከመቂ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው ቱቺ ራሳ የገጠር ቀበሌ ውስጥ ሰኔ 29 ከሰዓት በኃላ ወደ 11:00 ሰዓት ላይ በፋሽስት የብልፅግና ጦር ላይ በወሰደው ድንገተኛ እርምጃ የፋሽስት የብልፅግና ጦር በሙት እና በቁስለኛ ሲቀጣ ውሎዋል።
ሙቱ እና ቁስለኞቻቸውንም ሰላማዊ ህዝቡን በማስገደድ በፈረሰ እና በጋሪ አስጭነው ወደ መቂ ከተማ በመውሰድ ቁስለኞቹን በመቂ ሆስፒታል እየታከሙ እንደሚገኙ አቢኦ ከምንጮቹ ተነግሮታል።
ጀግናው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሽኒጋውን ቃል-ኪዳን ዘመቻ በመቀበል አንድ ሳምንት ባልሞላ ግዜ ውስጥ ከ100 በላይ ገድሎ ከ30 በላይም አቁስሎ በርካታ የጦር መሳሪያዎችንም አስፈቶ። ለነፃነት ትግሉ ገቢ አድርጎዋል።
#የሺኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ ይቀጥላል!
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያወጀው የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት እና የሀገር ባለቤትነት እስኪረጋገጥ ድረስ በተለየ መልኩም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሎአል።
ድል ለኦሮሞ ህዝብና ለጭቁን ብሔር ብሔረሰቦች!

