Site icon Qeerroo Bilisummaa Oromoo

የመደ አልቡዳ ዞኑ ግስላ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በ5 ቀናት ጦርነት የፋሽስት ብልፅግና ጦርን በማሽመድመድ ከ100 በላይ ገድሎና አቁስሎ በርካታ የጦር መሳሪያዎች እና ወታደሮችን ማርኳል

መስከረም 19፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

የኦሮሞ ህዝብ ዋስትና እና ጋሻ የሆነው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በሁለቱ የጦር ዞኖች ውስጥ የተጎናፀፈውን አመርቂ ድል እንደሚከተለው እናተነትለዋለን፦

ምሥራቅ ቦረና ዞን፣ ጎሮ ዶላና ልብን ወረዳዎች እና ምሥራቅ ጉጂ ዞን፣ ሰባ ቦሩ ወረዳ

ጎሮ ዶላ ወረዳ

መስከረም 17፣ 2024 በጎሮ ዶላ ወረዳ፣ አዳዲ ቀበሌ የኦነሰ አሰሳ በሚል ሽፋን የኦሮሞን ህዝብ ሲያሰቃይ የነበረን የፋሺስት ብልፅግና ጦር ላይ ወርሳመላ በሚባል ቦታ ላይ ባደረገው የደፈጣ ውጊያ የኦነሰ ድልን ተጎናፅፏል። ይኸውም በርካታ ወታደሮቹን ገድሎና የማይሽር ቁስልም አከናንቦ ሸኝቷቸዋል። የተረፉትም ቁስለኞቻቸውን እና አስከሬናቸውን ተሸክመው ወደ ቀርሳ መሌ ቀበሌ ለመሸሽ ተገድደዋል። 

መስከረም 5፣ 2024 የፋሺስት አብይ አህመድ ጦር ከጅዶላ ከተማ ወደ ሃርቀሎ ከተማ እየሄዱ ሳለ የኦነሰ አድፍጦ በወሰደው እርምጃ የሚከተለውን ድል ተጎናፅፏል፦

  1. በላምበል ቀበሌ፣ ማዞራ ጅዶላ በሚባለው ቦታ ላይ በመኪና ወደ ሃርቀሎ እየተጓዙ ከነበሩት መሃል 7 ወታደሮችን ገድሎ በርካታ ቁጥር ያላቸውን አቁስሏል።
  2. ኑራ ህምባ ቀበሌ፣ ደባቃ በሚባል ቦታ 4ቱን ከአፈር ሲቀላቅል፣ በርካታ ወታደሮቹም ክፉኛ ቆስለዋል። የፋሺስት ብልፅግና ጦርም ቁስለኞቹን ጭኖ ወደ ሃርቀሎ ከተማ ሲያጓጉዝ ታይቷል። 
  3. በዚሁ ዕለት ወደ ሃርቀሎ ከተማ እየሄደ የነበረ የፋሺስት ብልፅግና ጦርን ከተማው አካባቢ ሲርባ ቀበሌ፣ ብዬ ዲምቱ በሚባል ቦታ ላይ አድፍጦ በወሰደው እርምጃ 20 የሚሆኑ ወታደሮችን ወደ ማይመለሱበት ሸኝቷል። 

ሰባ ቦሩ ወረዳ

መስከረም 3-4፣ 2024 በሰባ ቦሩ ወረዳ፣ ኡቱሉ ቀበሌ እና በጎሮ ዶላ ወርዳ፣ በላምበል እና በሃdha Dhaደቻ ቀበሌዎች የኦነሰ አሰሳ በሚል ሽፋን የኦሮሞን ህዝብ ሲያሰቃይ የነበረን የፋሺስት ብልፅግና ጦር ላይ ባደረጉት የደፈጣ እርምጃ የኦነሰ አመርቃኝ ድልን ተጎናፅፏል። በዚህ ሁለት ቀናት ቢያንስ ከ40 በላይ የብልፅግናን ሰራዊት ወደ ማይመለሱበት ሲሸኙ በጣም ብዙ ቁጥር ያላቸውም ክፉኛ ቆስለዋል። ይህም በመሆኑ አስከሬን አንስተው ለመሄድ እንደተቸገሩም ተስተውሏል።  

ሊበን ወረዳ

በሊበን ወረዳ መስከረም 6፣ 2024 “የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን እናስሳለን” በሚል ሰበብ በተሰማራው የፋሺስት አብይ አህመድ ጦር ላይ የኦነሰ በወሰደው የማያዳግም እርምጃ አመርቂ ድልን ተጎናፅፏል። ይኸውም፦ 

በመሳሪያ በኩልም፦ 

በዚህ የኦነሰ በወሰደው እርምጃም የጠላት ካምፕ እየተናወጠ ሳለ፣ ቄሮ የጠራው  የገበያ እና የትራንስፖርት እቀባም በዞኑ መጠናከሩ ታውቋል።

#ጨቋኙ_ኃይል_በኦነሰ_ኃይል_ይገረሰሳል!

#የሺኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ በተጠናከረ መልክ ቀጥሏል!

Exit mobile version