Site icon Qeerroo Bilisummaa Oromoo

የምዕራብ ዞኑ የኦነሰ በምስራቅ ወለጋ ዞን፣ ሳሲጋ ወረዳ እና በጅማቴ ከተማ አስተዳደር የፋሺስቱን ብልፅግና ጦር እየቀጣ ሲሆን፣ በምዕራብ ወለጋ ደግሞ ሙቱን እና ቁስለኛውን ይዞ ወደሗላ አፈግፍገዋል

መስከረም 30፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO) 

የኦሮሞ ህዝብ ክንድ እና ጋሻው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በፋሽስት ብልፅግና ጦር ላይ የሚወስደውን የማያዳግም እርምጃ በማጠናከር አመርቂ ድልን አስመዝግቧል።

ሰበር ዜና፣ ምሥራቅ ወለጋ

መስከረም 29፣ 2024 የምዕራብ ዞኑ የኦሮሞ ነፃነትሰራዊት፣ በምስራቅ ወለጋ በሳሲጋ ወረዳ እና በጅማቴ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የማፍያው ብለፅግና ጦርን አይቀር ቅጣት እየሰጠው ይገኛል።

ሙሉ ዘገባው እንደደረሰን በቴሌግራም፣ በፌስቡክ፣ በትዊተር እና ረምብል ገፃችን ላይ  እናካፍላችሗለን።

በምዕራብ ወለጋ ዞን፣ ሃሩ ወረዳ 

መስከረም 14፣ 2024 በሃሩ ወረዳ፣ አሌበንታ ቀበሌ፣ ቱሉ በከኮ በሚባል ስፍራ ቀበሌ እንገነባለን በሚል ሰበብ ህዝብን ስያሰቃይ የቆየ የፋሺስት ብልፅግና ጦር ቡድን ላይ በወሰደው የማጥቃት እርምጃ 9 ወዲያው ሲገድል 13ቱን ደግሞ በማቁሰል ወደ ኋላ እንዲመለሱ አስገድዷቸዋል።

ቁስለኛ እና አስከሬኖቹን በሁለት መኪና የጫነ ሲሆን፣ በዚህ ጦርነት ሆስፒታል የገቡ የፋሺስቱ ጦር አባል ቁስለኞችን ጨምሮ ህይዎታቸው ያለፈ ከዚህ በላይ መሆን እንደሚችል ከቦታው ያገኘነው ዜና ያስረዳል።

#የሺኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል!

ድል ለኦሮሞ ህዝብና ለጭቁን ብሔር ብሔረሰቦች!

Exit mobile version