Site icon Qeerroo Bilisummaa Oromoo

በምሥራቅ አርሲ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ ከመሞት መሰንበትን መርጠው ቤት ንብረታቸውን ትተው ወደ ጫካ የሸሹትን እና የ14 ዓመት ልጅ ሳይቀር የፋሺስት ብልፅግና ጦር በጅምላ እየረሸነ ይገኛል

መስከረም 19፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

ፋሺስት አብይ አህመድ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ውስጥ ለውስጥ ያወጀውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በዙፋኑ ጠባቂ ጦር ባልደረቦች እውን መደረግ ከጀመረ አመታትን አስቆጥሮዋል። ወንጀሉንም ለመተግበር የሃሰት ወንጀሎችን በኦሮሞ ህዝብ ላይ በመመስረት ነው። ከነዚህም ውስጥ ደጋግመው የሚጠቀሙት “የኦነግ-የኦነሰ ደጋፊዎች ናችሁ።” የሚለውን ነው።  

ይህንንም ምክንያት በማድረግ ከመሞት መሰንበትን መርጠው ቤት ንብረታቸውን ትተው ወደ ጫካ የሸሹትን ንፁሃን ኦሮሞዎችን ሳይቀር በጅምላ እየረሸኑዋቸው እንደሆነ የጀጁ ወረዳ ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናገሩ።

በከተማ መሃል እና በቤተሰብ ፊት ጥይት በማርከፍከፍ የሚገደሉትም ቤት ይቁጠር የሚባልበት ደረጃ ተደርሷል። የኦሮሞን ሃብት ንብረት ዝርፊያ፣ ቤት ከነ ንብረት በእሳት ማጋየቱም ተባብሶ ቀጥሏል።

ጀጁ ወረዳ፣ ሁሩታ ዶሬ ቀበሌ

ነሐሴ 10፣ 2024 ኦቦ ሰይዳ አልዪ የተባሉትን አዛውንት ከቤታቸው በማውጣት ያለምንም ጥፋታቸው ኦሮሞ በመሆናቸው ብቻ በጥይት ደብድበው ገድለዋቸዋል በማለት የቀበሌው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል። እኝህም አዛውንት በህብረተሰቡ ውስጥ የተከበሩ እና የሚወደዱም እንደነበር ነዋሪዎቹ አክለው ገልፀዋል። 

በዚሁ ቀበሌ ውስጥ ኦሮሞዎችን ከስራ ገበታቸው በጅምላ በመያዝ ወደ እስር ቤት እያጎሯቸው ሲሆን ከእነርሱም መሃከል ለጊዜው ስማቸው የደረሰን፦

  1. ከሪም አማን፣
  2. ሀሰን ገና፣
  3. ቦንጃ ዋቆ፣
  4. ቦከና ዋቆ እና
  5. ቱና ናቸው።

በዚሁ ቀበሌ ውስጥ የፋሺስት ብልፅግና ቡድን ቤት እስከነ ንብረታቸው በእሳት ያወደመባቸው፦ 

  1. ኢማም ሀጂ ከድር፣
  2. ሲራጅ ከድር፣
  3. አህመድ ሁሴን፣
  4. ሱልጣን ሀሰን፣
  5. ናጃማ ሁሴን፣
  6. ከማል ሁሴን፣
  7. ጃለኒ ቡና፣
  8. አብዱልዋይድ ሸሪፍ፣
  9. ጁንዲ በdhaሶ፣
  10. ቃሲም ጀዋር፣
  11. አብዱልአዚዝ አቡበከር፣
  12. ኑሪ ጁንዲ፣
  13. ሰይዳ ጁንዲ፣
  14. አህመድ ማሚዮ እና 
  15. ሰኢዳ ማሚዮ

የተባሉ እንደሆነ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። ነዋሪዎቹም እነዚህ ንፁሃን በዚህ ክረምት ወቅት መጠለያ፣ ልብስ እና ምግብ በማጣታቸው ከባድ ችግር ላይ መሆናቸውንም አክለው ለአቢኦ ገልፀዋል። 

ሮቤ ዲዳ ወረዳ

ጄና ገደምሳ ቀበሌ

ነሐሴ 10፣ 2024 አዴ ቡልቡሌ ሀጂ በኮ ሱቢ የተባለች ሴት የፋሺስቱ ብልፅግና ጦር አንድ ጥይት አልበቃ ብሏቸው በዘጠኝ ጥይት ደብድበው ገድለዋታል።

ጄና ሁሉሊ ቀበሌ

የአምስት ልጆች አባት የነበረውን ኦቦ ዚያዶ ሰኢድ አደምን ከቤቱ አውጥተው በሩ ላይ በቤተሰቦቹ ፊት ጥይት እንደ ዝናብ በማርከፍከፍ ገድለውታል።

ከዚህም ሌላ ከነሐሴ 10፣ 2024 ጀምሮ በተከታታይ ቀናቶች 9 የቀንድ ከብቶች እና 63 ፍየሎችን ከአምስት ቤተሰቦች በመዝረፍ አርደው ሲበሉ እንደነበረም የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል። ንብረታቸው የተዘረፉትም፦

  1. ከመሀመድ ኡሴን 3 የቀንድ ከብቶች፣
  2. ከአብዱለጢፍ አብደላ 3 የቀንድ ከብቶች፣
  3. ከዛሩ ቀሶ 4 የቀንድ ከብቶች እና 24 ፍየሎች፣
  4. ከበያን ቃሲም 19 ፍየሎች እና
  5. ከሌንጮ መሐመድ 20 ፍየሎች

ናቸው።

መርቲ ወረዳ፣ ወተሮ ዲኖ ቀበሌ 

ነሐሴ10፣ 2024 የፋሺስት ብልፅግና ጦር ቡድን በባቁላ መንደር ውስጥ ይኖር የነበረውን እና የሁለት ልጆች አባት ዚሁ ኦቦ ገቢ ገና ሃጂቻ ቤቱን ከፍተው እሱ ሲወጣ ያለምንም ጥያቄ በጥይት ደብድበው ሲገድሉት ቤተሰብ ሲያለቅስ “ለምን ታለቅሳላችሁ እናንተንም ጨምረን እንገድላለን ፀጥ በሉ!” በማለት እንዳስፈራሯቸው ለአቢኦ ምንጮች ተናግረዋል።

በዚሁ መንደር ከአንድ ቀን በፊት ማለትም ነሐሴ 9፣ 2024 የኦነሰን ለማሰስ በሚል የተሰማሩት የፋሺስት ብልፅግና ወታደሮች  ከቤት ወደ ቤት እየዞሩ የ14 ዓመት ጨቅላ ወጣቱን አብዱረማን ሮባ ገርቢ ከአባቱ ቤት በማውጣት ጥይት እንደ ዝናብ በማርከፍከፍ የሰውነት ክፍሉን እስኪለያይ ጭንቅላቱንም ጭምር ገድለውታል። በዚህም አሰቃቂ ግድያ ሳይረኩ ቤተሰቡ ሬሳውን እንዳያነሱ በመከልከል ለአንድ ቀን ዝናብን ፀሐይ እንዲፈራረቅበትም እንዳደረጉ የአካባቢው ሰዎች ለአቢኦ አሳውቀዋል። 

ፋሺስት አብይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦

“የኦሮሞን ሕዝብ ንብረትና ቤት በማዉደም ለረሃብ፣ ለእርዛት፣ ለመጠለያ አጥነት አጋልጦ ለመግዛት እና የኦሮሞን ሕዝብ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ለማድረግ፣ ከዚህም እልፎ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ ትዕዛዝ እንዲሰጥ መንበር የተሰጠው፤ የ አውሬነት ባህርይ የተላበሰ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኤምፓየሪትዋ ያስተናገደች፣ ሰብዓዊነት የጎደለው የለየለት ጨካኝ አምባገነ መሪ ነው።”

ግድያ፣ እስራት፣ ስቃይና ዝርፊያ የሚፈራረቅባት ኦሮሚያ እስከ መቼ የኢምፓየሯ አካል ሆና ትቀጥላለች? 

የኦነግ – ኦነሰ ቃል ገብቷል።

#የሺኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ እስከ ነፃነት ይቀጥላል!

Exit mobile version