ሐምሌ 16፣ 2024 አራት ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በብልጽግና ታጣቂ ሃይሎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሰው ግድያ፣ ዘረፋ እና የንብረት ውድመት በገፍ ቀጥሎዋል። ይኸውም የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን በጦር ሜዳው ፍልሚያ ላይ መቋቋም ባለመቻሉ ቁጭቱን በሰላማዊ ህዝብ ላይ እየተወጣ መሆኑን በግልፅ እያሳየ ነው በማለት ነዋሪዎች እሮሮዋቸውን ለአቢኦ እያሰሙም ይገኛሉ።
የተገደሉት፣ ቤታቸው የተቃጠለባቸው እና ንብረታቸው የተዘረፈባቸው በግብርና ስራ የተሰማሩ ሲሆኑ እራሳቸውን እና ቤተሰባቸውን የሚያስተዳድሩ እንዲሁም በፖለቲካ ውስጥ ምንም ሚና የሌላቸው መሆኑንም የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል።
ቄለም ወለጋ ዞን፣ ሳዮ ወረዳ
ሐምሌ 3፣ 2024 በጉቴ ሶዮማ ቀበሌ፣ አውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ድንገተኛ በከፈተው የማጥቃት እርምጃ ሞትና ቁስለኛ አድርጎ ሸኝቶዋቸዋል።
በዚህም ሽንፈት በመንገዳቸው እንደለመዱት ቁጭታቸውን ለመወጣት በአካባቢው ወደሚገኘው ገባ ደፊኖ ወደ ተባለው መንደር ገብተው ኦቦ ሙልጌታ የተባሉትን ሰላማዊ ሰው መኖሪያ ቤታቸው ድረስ ሄደው ከቤትም እንዲወጡ ጠርተዋቸው ወዲያው በቤተሰቦቻቸው ፊት ጥይት እንደ ዝናብ አርከፍክፈው መግደላቸውን አቢኦ ከምንጮች አግኝቶዋል።
ደቡብ ምዕራብ ሸገር ዞን፣ ቶሌ ወረዳ
ሐምሌ 5፣ 2024 በቶሌ ወረዳ በሁሉም ቀበሌዎች ውስጥ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ቤተሰቦች ላይ እስራት፣ ግድያ፣ ዝርፍያ እና ቤት ከነንብረቱ ማውደሙን በሰፊው መቀጠላቸው ለአቢኦ ምንጮቹ አሳውቀዋል።
ሐምሌ 4፣ 2024 ያያ ሰኮራ ቀበሌ፣ መዳናልም ተብሎ በሚጠራው መንደር የሚኖሩትን የ ጃል ሂን-መቁን ቤተሰብ ቤት ከነንብረቱ በእሳት አጋይተው ከማውደማቸውም በላይ ሶስት ሰንጋም ዘርፈው መሄዳቸውን የመንደሩ ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል።
በዚሁ መንደር ኦቦ ያሬድ ስለሺ የተባለ ሰላማዊ ሰው ቤቱን ካቃጠሉ በኋላም ሁለት የቀንድ ከብቶችን እና 25 ፍየሎችን እንደዘረፉም ነዋሪዎቹ አክለው ገልፀዋል።
ፋሺስት አቢይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦
“የኦሮሞን ሕዝብ ንብረትና ቤት በማዉደም ለረሃብ፣ ለእርዛት፣ ለመጠለያ አጥነት አጋልጦ ለመግዛት እና የኦሮሞን ሕዝብ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ለማድረግ፣ ከዚህም እልፎ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ ትዕዛዝ እንዲሰጥ መንበር የተሰጠው የፋሺስታዊ መንግስት መሪ።”
#የሺኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ ይቀጥላል!

