• Wed. Nov 25th, 2026

የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት የሰሞኑ ወታደራዊ እርምጃዎች ዘገባ: ከመጋቢት 1- 4/2024 ዓ/ም የኦሮሚያ ብሔራዌ ሚድያ

Mar 7, 2024

ጀግናው የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት በኦሮሚያ በተለያዩ ዞኖች ዉስጥ በጠላት ላይ እየወሰደዉ ያለዉን የማጥቃት እርምጃ በቁርጠኝነት እንደቀጠለ ነዉ። በዚሁም መሰረት በምዕራብ ወለጋ ዞን፣ በምዕራብ ጉጂ ዞን እንዲሁም በሰሜን ሸዋ ሰላሌ ዞን ስር በሚገኙ ወረዳዎች ላይ ከበባድ እርምጃዎችን በመዉሰድ የፋሽስቱን ብልጽግና ሠራዊትን አከርካሪ መስበር ችሏል።

በተለይም በሰሜን ሸዋ ሰላሌ ዞን ፋሽስቱ ያሰማራው ሁለት ክ/ጦር በአብዛኛው ላያንሰራራ ድባቅ እንደተመታ ከስፍራዉ የተገኘ ዘገባ ያመለክታል። በዚህም መሠረት በሰሜን ሸዋ ሰላሌ ዞን ሥር በሚገኙት እንደ ያያ ጉለሌ፣ ሂdhaቡ አቦቴ፣ ደገም፣ ደራና ኩዩ ወረዳዎች ላይ በወሰደው መጠነ-ሰፊ እርምጃ ፋሽስቱ ባሰማራው ሠራዊት ላይ ከባድ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሷል። በዉጊያዉም ከ200 በላይ የፋሽስቱ ሠራዊት ሲገደሉ እጅግ በርካታ ቁጥር ያለው የወራሪዉ ሰራዊት አባላት ላይ ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሷል።

በተመሳሳይ መልኩ ጀግናዉ ሰራዊታችን በምዕራብ ወለጋ ዞን ገንጂ ወረዳ በወሰደው ድንገተኛ እርምጃ ከ10 በላይ የሚሆኑ የፋሽስቱን ወታደሮች በመደምሰስ 6ቱን ደግሞ ክፉኛ አቁስሏል።

በሌላ በኩል ፍትሓዊ የሆነን ህዝባዊ አላማ አንግቦ እየተዋደቀ ያለዉ ጀግናዉ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ትናንትና መጋቢት 4/2024 ዓ.ም ከጠዋቱ ሁለት ሰኣት (8:00 AM) ላይ በምዕራብ ጉጂ ዞን በገላና ወረዳ ኤጄርሳና ኮምቦልቻ ከተሞች ዉስጥ በጠላት ላይ በወሰደዉ የማጥቃት እርምጃ ከ20 በላይ የሚሆኑትን የፋሽስቱን ወታደሮች እስከወዲያኛዉ ሲያሰናብት ከ12 በላይ የሚሆኑትን በማቁሰል የኮምቦልቻንም ከተማ ተቆጣጥሮት እንደነበር ታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪም በተመሳሳይ ጊዜ በምዕራብ ጉጂ ዞን በዱግዳ ዳዋ ወረዳ ልዩ ስሙ ሳተላይት ቀዲዳ በተባለ ሥፍራ ላይ ልክ ከጧቱ ሁለት ሰኣት (8:00 AM) ስንቅ ጭኖ ሲጓዝ የነበረ አነስተኛ የፋሽስት ኃይልን በመክበብ ድባቅ መቷል። በዚህም የሰራዊታችን ቁርጠኝነትና ብስለት በታየበት ልዩ ኦፕሬሸን 15 የፋሺስቱ ወታደሮች ሲገደሉ ከ10 በላይ ደግሞ ክፉኛ ቆስለዋል።

ጀግናዉ ሰራዊታችን ያሳረፈበትን መብረቃዊ ምት መቋቋም ያልቻለዉ የፋሽስቱ ጦርም ከባድ ድንጋጤና ፍራቻ ዉስጥ ተዘፍቋል።

Leave a Reply