መጋቢት 19/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
ይህ ራሱን “የእሮሞ አንድነት ኃይሎች” በሚል ራሱን የሰየመ አካል የገበያና የትራንስፖርት ዕቀባ መግለጫ ያወጣ ሲሆን፤ ይህንን መግለጫ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በመልቀቅ በህዝባችን ዘንድ ግራ ማጋባትን እየፈጠረ መሆኑን የቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ ኮሚቴ ገልጿል።
ይህ ራሱን “የእሮሞ አንድነት ኃይሎች” በሚል ራሱን የሰየመ አካል ዕቀባውን የጠራው ለ24/3/24 ሲሆን በዚህም መሠረት ገበያ፣ ትራንስፖርትና የፊንፊኔ የመጠጥ ውሀ አቅርቦት መቁረጥን ያጠቃለለ ዕቀባ ይህ ጥሪ መሠረት የሌለው ሲህን አሁን እየተሠራበት ያለውን የአሰራር ስልት የሚቃረን ጥሪ መሆኑንና ህዝባችንን ግራ ለማጋባት የወጣ መሆኑን የኦሮሞ ነጻነት ቄሮ ኮሚቴ ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ገልጿዋል።
የቄር ቢሊሱማ ኦሮሞ ቀደም ሲል በየካቲት 2/2024 የገበያና የትራንስፖርት ዕቀባ መነሳቱን በገለፀበት ወቅት ወደፊት ያሉትን ሁኔታዎች በማጥናት ጠንካራ በሆነ መንገድ ጥሪ እንደሚያወጣ ገልጾ እንደ ነበረ የሚታወስ ሲሆን፤ ይህ ኮሚቴ በአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ በኩል ጥሪውን ይፋ እስከሚያደርግ ድረስ ህዝቡ በንቃት እንዲጠባበቅ ኢያሳሰበ አሁን ወጣ የተባለውን ጥሪም ሆነ ሌሎች የሚያወጡት ጥሪ የኦሮሞ ነጻነት ቄሮ (QBO) እንዳልሆነ እና ህዝባችን ግራ እንዳይጋባ እናሳስባለን ብሏል።
አንዳንድ ኃይሎች የኦሮሞን ትግል ለማቀጨጭ ግራ ማጋባት እንዲሁም ትግሉ በአንድ አመራር ሥር እንዳይሆን በተለያዩ ቦታዎች ሆን ብለው የጠላትነት ሥራ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ የሚሠሩ ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እያሳሰብን፤ አሁን ባለንበት ወቅት ምንም ዓይነት የትራንስፖርትና የገበያ ዕቀባ እንደሌለ ለማሳሰብ እንወዳለን።
