• Sat. Sep 26th, 2026

በጅምላ የኦሮሞ ህዝብን ወደ እሰር ቤት ማጎር፣ ማስቃይት ከዚያም በጅምላ መረሸን የአቢይ አህመድ መራሹ ብልጽግና ቡድን የዕለት ዕለት ተግባሩ ሆኗል

Mar 21, 2024

መጋቢት 21/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

የእቢይ አህመድ መራሹ ሰራዊት ቡድኖች 18 ንጹሃን ኦሮሞዎችን ከ15 እመት ልጅ እስከ 70 አመት አዛውንት በምስራቅ ወለጋ ዞን ጂማ አርጆ ወረዳ እና በምስራቅ ሸገር ዞን በቦራ እና ዱግዳ ወረዳዎች ከእስር ቤት አውጥቶ ረሽኗል። ይህንንም ፋሽስታዊ ድርጊት በመላው ኦሮሚያ እየተገበሩት ይገኛል።

ምስራቅ ወለጋ ዞን፤ 

በምስራቅ ወለጋ ዞን፣ ጂማ አርጆ ወረዳ፣ ቆናን ቡላ ሜታ ቀበሌ ነዋሪ የነበሩት የ70 አመት አዛዉንቱ እና የ14 ቤተሰብ አስተዳዳሪ ኦቦ ገመቹ ተሰማን ‘ልጅህ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አባል ነው’ በማለት አስረው ሲያሰቃዩዋቸው ከቆዩ በኃላ መጋቢት 7/2024 ከእስር ቤት አውጥተው ረሽነዋቸዋል።  

ከገደሏቸዉም በኃላ ሕዝቡ በጊዜ ወስዶ እንዳይቀብራቸው የከለከሉ ሲሆን ቤተሰብና የአካባቢው ሕዝብ የገዳይ ቡድኑ ከአካባቢው መሄዱንን ካረጋገጡ  በኃላ መጋቢት 8/2024 ከተጣሉበት  መንገድ አንስተው ግብዓተ መሬት ፈጽመዉለቸዋል። ኦቦ ገመቹ ተሰማ፣ በአከባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ተወዳጅና የተጣላን ማስታረቅ ሚናን ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎቶችን በመስጠት ከህብረተሰቡ አንቱታን ያገኙ የዕድሜ ባለጸጋ ነበሩ። 

ምስራቅ ሸዋ ዞን፤

የፋሽስት አቢይ አህመድ ብልጽግና አሳሪና ገዳይ ቡድን በምስራቅ ሸዋ ዞን፣ በቦራ እና ዱግዳ ወረዳዎች ሰላሚዊ ህዝብን በገፍ ወደ ማጎሪያ ሥፍራዎች በመውሰድ ከዚያም በማውጣት መግደላቸዉን አጠንክረው እንደቀጠሉ ነዋሪዎች ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ በመናገር ላይ ናቸው። በአረመኔው የብልፅግና ገዳይ ቡድን ከተረሸኑት መሃል ስማቸው ለጊዜው የደረሰን፦

ከቦራ ወረዳ

  • የ15 አመቱ ጂማ ነdhi ቁፋ በጂሪሜ ቦራ ቀበሌ፣
  • የ17 አመቱ አባታ ጅቦ ዶሪ በጂሪሜ ቦራ ቀበሌ፣ 
  • የ19 አመቱ ሲዳ መልካ ጉደታ ከኤላን ቀበሌ፣
  • የ21 አመቱ ቆሪቾ በራቃ ቶላ ከማሊማ ባሪ ቀበሌ፣ 
  • የ22 አመቱ ዲታ አያኖ ዶሪ፣ ከጎራ ላማ ቀበሌ፣ 
  • የ22 አመቱ ፋይሳ ቱጁራ ከዶዶ ወደራ ቀበሌ፣ 
  • የ22 አመቱ በሻዳ ሃዬ ከቢቴ ደሃባ ቀበሌ፣ 
  • የ23 አመት ዲታ ዳሌ ከኤላን ቀበሌ፣
  • የ23 አመቱ ዳቃቦ ሻንቆ ከቢቴ ዳባ ቀበሌ፣
  • የ31 አመቱና የ5 ቤተሰብ አስተዳዳሪ አቡ በdhሃሶ ከኤላን ቀበሌ፣
  • የ45 አመቱና የ5 ልጆች አባት ጋሮ ፈይሶ ደጋጋ ከዶዶ ወደራ ቀበሌ፣
  • የ49 አመት የ5 ልጆች አባት በDhadha ደጋጋ በጂሪሜ ቦራ ቀበሌ እና
  • የ70 አመቱ ጌታቾ ከፈኒ በጂሪሜ ቦራ ቀበሌ ናቸው።

ከዱግዳ ወረዳ

  • የ4 ልጆች አባት ቃቻ ነጎ፣ ከዳራራ ዳለቻ ቀበሌ፣ 
  • የ6 ልጆች አባት እና 45 አመቱ ኢርጋ ሻንቆ ነጋ ከወልዳ ቃልና ቀበሌ፣ 
  • የ28 አመቱ ኩርፋ ጉሬ ቤለሞ ከዋልዳ ቃሊና ቀበሌ፣ እና
  • የ4 ልጆች አባት እና 30 አመቱ ፈይሳ ፊታላ፣ ከሹቢ ጋሞ ቀበሌ ናቸው።

የአቢይ አህመድ መራሹ ቡድን በነደፈው ስልት መሰረት የኦሮሞን ሕዝብ የትውልድ ዘርፍ ፍሰትን ማደናቀፍ ብቻ ሳይሆን ከእድሜ ባለጸጎቻችን የሚገኘውንም እውቀት ለማደብዘዝ የተነሳብን ፋሽስት መሆኑን ሕዝባችን ተገንዝቦ ይህን የመጨረሻውን የነፃነት ትግል ካለምንም ማወላወል መቀላቀል ይኖርበታል።

ከወሎ ሕዝባችን ጎን በአንድነት እንቁም!

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading