• Tue. Nov 24th, 2026

የብልጽግናው ኤታማጆር ሹሙ ብርሃኑ ጁላ በሠራዊታቸው ፊት ማንም ሊቆም እንደማይችል በመገናኛ ብዙኃን ላይ ፉከራ ቢያሰሙም ይህ ፉከራ በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከባድ ምት ባዶ ቀረርቶ መሆኑ ታይቷል

Mar 25, 2024

መጋቢት 25/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መጋቢት 12/2024 በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሐንጫር ወረዳ በአከባቢዉን ህዝብ እያሰቃየ ባለ የጠላት ሃይል ላይ እርምጃ ወስዷዋል። 

በዚህም ዉግያ 16 የኢምፓየሪቷ ጠባቂዎች ሲገደሉ በርካቶች ቆስለዋል። በተካሄደው ጦርነት የተደናገጡት የብልጽግና ሃይሎች በተጨማሪ ወታደሮቻቸዉን በአራት አቅጣጫ ወደዚህ ወረዳ በማስገባት መልሶ ለማጥቃት ቢሞክሩም ድሉ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ሆኖዋል። 

ጀነራል ብረሀኑ ጁላ ማንም በሰራዊታችን ፊት ሊቆም አይቻለዉም እያለ በመገናኛ ብዙሃን ከእዉነት የራቀ ዲስኩር ቢያወሩም የዛሬውን ጨምሮ ወታድሮቻቸዉ በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በብዛት እየተገደሉ፣ እየቆሰሉ እና እየተማረኩ መሆናቸዉ የአደባባይ ሚስጥር ሆኖ ቀጥሎዋል።

ጽኑ አላማን አንግቦ የተነሳው የኦሮሞ ሕዝብ ስራዊት የቅኝ ግዛት ስርዓት መልሶ እንዲያንሰራራ በግዴታ ተመልምሎና ሰልጥኖ የተሰማራውን የኮረኔል አብይ አህመድ ጦር አሽመድምዶ ከአባት ሐገሩ ለመንቀል ከምን ጊዜም በላይ ዝግጁ መሆኑን ሕዝባችን አእቆአል፤ ወዳጅም ሆነ ጠላት ሊገነዝብ ይገባል። 

ከወሎ ሕዝባችን ጎን በአንድነት እንቁም!

Leave a Reply