መጋቢት 25/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
በብልጽግና አገዛዝ ሰላማዊ ዜጎችን ለመግደል የተሰማራዉ ህገ-ወጡ ኃይል የህብረተሰቡን ቤትና ንብረት እየዘረፈ እንዲሁም አረጋውያንን እና ዕድሜያቸው ለውትድርና ያልደረሰ ህፃናትን ወደ ማሰልጠኛ እንዲላኩ እና ከባድ መከራ እንዲደርስባቸው እያደረገ ይገኛል።
ይኸውም በምእራብ ሸዋ ዞን ቶኬ ኩታዬ ወረዳ የአገዛዙ ማፍያ ሰራዊት አና የብልጽግና ካድሬዎች መጋቢት 13 ቀን 2024 ከጉደር ከተማ ወደ ዳዳ ገላን ቀበሌ ተጉዘዉ አረጋውያንን ወደ ስልጠናም እንዲሄዱ እያስገደዱ መሆናቸዉ ታዉቋል። በዚህ ወረዳ ንብረት ዘረፋ ፣ ሰላማዊ ዜጎችን ማሰርና በነዋሪዎች ላይ ድብደባ መፈፀም ተባብሶ መቀጠሉን እና ህብረተሰቡ በከባድ ችግር ዉስጥ መሆኑን ምንጮቻችን አክለው ገልጸውልናል።
እንደዚሁ በምዕራብ ሀረርጌ ዞን ጪሮ ወረዳ፣ በጪሮ ከተማ አንድ የዱባ ወረዳ ነዋሪ በአገዛዙ ታጣቂዎች መገደላቸው ታዉቆዋል። መጋቢት 14/2024 ኦቦ ሙሐመድ ኡስማን የተባሉ አዛውንት በጪሮ ከተማ በፋሽስቱ አቢይ አህመድ ገዳይ ቡድን ተይዘው ሁለት ሺ ብር ተዘርፈው፣ ከዛም ተደብድበዉ መገደላቸውን የዶባ ወረዳ ነዋሪዎች ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ተናግረዋል።
የተገደሉበትም ምክንያት ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ምስራቅ ወለጋ ዞን ሳሲጋ ወረዳ ልጃቸውን ለማየት ሄደው በመመለስ ላይ እያሉ ጪሮ ከተማ ላይ እንደተያዙና የሄዱበትንም ምክንያት የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊትን ለመርዳት እንጂ ልጃቸውን ለመጠየቅ አይደለም በማለት ነው።
ኦሮሞን ከቦታ ወደ ቦታ እንደማንኛውም ሰው በሐገሩ (ኦሮሚያ) ውስጥ እንዳይዘዋወር መግታት፣ ማሰር፣ መግደል እና እድሜ ሳይገድበው ለውትድርና አስገድዶ መውሰድ ኢ-ሰብዓዊ ብቻም ሳይሆን ወንጀልም ነው።
ከወሎ ሕዝባችን ጎን በአንድነት እንቁም!
