• Tue. Nov 24th, 2026

ፋሺስት አብይ አህመድ የኦሮሞ ነፃነት ታጋይ ግለሰብ ዘመድ በመሆናቸው ብቻ በመላዉ ኦሮሚያ በኢምፓየርዋ ጦር ውስጥ ባደራጃቸው አጥፊ ቡድኖች አስገድሎ ክቡር ሰዉነታቸዉንም ለጅብ እያሰጣለ ይገኛል

Apr 3, 2024

ሚያዚያ 2/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

ነዋሪነቱ በምስራቅ ወለጋ ዞን ሲቡ ስሬ ወረዳ ቡርቃ ጣሎ ቀበሌ ዉስጥ የሆነ፣ ጌቱ ሶሬሳ ዲርበባ የተባልን የ27 ዓመት ወጣት መጋቢት 18/2024 ወንድምህ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አባል ነው በማለት በኢምፓየርዋ የጦር ሰራዊት አባላት ከቤቱ በምሽት ተወስዶ ለሶስት ቀናት በጦር ካምፓቸው ዉስጥ ካሰቃዩት በኋላ ጎቡ ሳዮ ወረዳ ገባ ደፊኖ ወደሚባል ቦታ ወስደው ከገደሉት በኃላ ሬሳዉን ለአውሬ ጥለዋል።

የወጣቱ ግድያ የተከናወነው ከሚኖርበት አካባቢሩቅ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ከገደሉት በሁዋላም ክቡር ሰውነቱን ለዱር አራዊት ጥለዉትም ስለነበረ ቤተሰቦቹ አስከሬኑን በጊዜ እግኝተው ስርዓተ ቀብር ሊያደርጉለት አልቻሉም። ማነቱንም ለማወቅ የቻሉት የተቀዳደደ ልብሱን በቦታው በማግኘታቸው ነበር።

ከእንዲህ ዓይነት አሰቃቂ ግዲያ ጎን ለጎንም አስገድዶ መድፈር፣ የንብረት ዝርፍያ እና የቤት ቃጠሎ በፋሺስት አብይ አህመድ የብልፅግና ጦር ቡድን በህብረተሰቡ ላይ እየተፈፀመ መሆኑንም የአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ምንጭ ገልጸዋል።

ፋሺስት አቢይ አህመድ አሊ በቅርሰ ማህደር የሚታወሰው፦
“የኦሮሞን ሕዝብ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ማድረግ፣ ከዚህም እልፎ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ እና ለዱር አራዊትም እንዲጣሉ ትዕዛዝ የሚሰጥ የአውሬነት ባህርይ የተላበሰ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኤምፓየሪትዋ ያስተናገደች፣ ሰብዓዊነት የጎደለው የለየለት ጨካኝ አምባገነ መሪ ነው።”

ከወሎ ሕዝባችን ጎን በአንድነት እንቁም!

Leave a Reply