• Wed. Nov 25th, 2026

የፋሺስት አብይ አህመድ መራሹ ብልፅግና ቡድን ወኪሎች በቄሌም ወለጋ ዞን አንፊሎ ወረዳ የህዝብ ቤትና ንብርት ዘረፋ እና ግድያ መፈጸማቸውን ቀጥለዋል

Apr 14, 2024

ሚያዚያ 13/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

ኦሮሚያ ከተወረረች ጊዜ ጀምሮ ኢምፓየሪትዋን ሲመሩ የነበሩ መንግሥታት በሰው ልጆች ላይ ሊደረጉ የማይገባቸዉን አሰቃቂ ድርጊቶች እያስተናገደ ያሳለፈው የኦሮሞ ህዝብ፤ በፋሺስት አብይ አህመድ በሚመራዉ የብልፅግናው ቡድን ዘመን ደግሞ ካለፉት ገዢዎች የባሰ ስቃይን እያስተናገደ ይገኛል።

የተለያዩ ሚድያዎችን በመጠቀም ልክ ለኦሮሞ እንደሚያስብና እንደሚቆረቆር ሲዋሽ የሚውልው ኮረኔል አብይ አህመድ ካቢኔውንና ሰራዊቱን በመላዉ ኦሮሚያ በማሰማራት ንጹሃንን በኢ-ሰብዓዊነት መልኩ እያስገደለ፣ እያዘረፈ፣ እያሳሰረ እና የኦሮሞ ገበሬዎችን ቤቶች ከእነ ንብረቱ እያስጋየ የኦሮሞን ቀዬ በሀዘን ማቅ ማስልበሱን አጠናክሮ ቀጥሏል።

በዚህ መሰረት መጋቢት 28/2024 በቄሌም ወለጋ ዞን፣ አንፊሎ ወረዳ ያቲ ቀበሌ ልዩ ስሙ ያጋበተባለ ሥፍራ የኦቦ ማመድ አብዱራዛቅን ቤት ካቃጠሉ በኋላ የገደሏቸው ሲሆን በዚሁ ዕለት ዳላ ሾር ቀበሌ ውስጥ ደግሞ የኦቦ ዲሪባ ያደታን ቤት በመስበር አምስት ኩንታል ቡና እንደወሰዱባቸው የዜና ምንጫችን ዘግቦልናል።

ፋሺስት አቢይ አህመድ አሊ በቅርሰ ማህደር የሚታወሰው፦

“የኦሮሞን ሕዝብ ንብረትና ቤት በማዉደም ለረሃብ፣ ለእርዛት፣ ለመጠለያ አጥነት አጋልጦ ለመግዛት እና ንጹሃን ኦሮሞን በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ ለማዘዝ መንበር የተሰጠው የፋሺስታዊ መንግስት መሪ።”

Leave a Reply