• Tue. Nov 24th, 2026

በምዕራብ ሸገር ዞን፣ ባኮ ቲቤ ወረዳ የብልጽግናው ማፊያ ጦር ቡድን በጅምላ ማሰርና ማሰቃየቱን አጠናክር ቀጥሏል

May 6, 2024

ግንቦት 6፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

የብልፅግናው ማፍያ ቡድን ሰላማዊ ዜጎችን በጅምላ ማሰር፣ መዝረፍ፣ ማጓጓዝ የማይችሉትን ንብረታቸውን ከመኖሪያ ቤታቸው ጋር በእሳት ማጋየት እና መግደል አጠናክሮ እየፈጸመ ይገኛል። 

በዚህ መሠረት በምዕራብ ሸገር ዞን፣ ባኮ ቲቤ ወረዳ፣ በባኮ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በማፍያው ብልጽግና ታጣቂ ቡድኖች ሕዝቡ እየተሰቃየ መሆኑን ነዋሪዎች ተናገሩ።

የሰብዓዊ መብት ረገጣ እየተፈጸመባቸው ከሚገኙት እስረኞች ውስጥ ጥቂቶቹ ስማቸው ደርሶናል፤ እነሱም፦

  1. ዴዪሳ ተሬሳ፣
  2. ጫላ ኢዶሳ፣
  3. ታጁ ጋቸና፣
  4. ታሪኩ ለቺሳ፣
  5. ሂካ ቦቆኔ፣
  6. ኦቦ ኢዶሳ፣
  7. ተፈሪ ሞሲሳ እና
  8. አዱኛ ቡሊ ናቸው።

በተጨማሪም በባኮ ቲቤ እስር ቤት እየተሠቃዩ የሚገኙት በርካታ እንደሆኑ፣ በሽተኞችም ህክምና በማጣት እንዲሁም በቂ ምግብም ባለማግኘት አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ መሆናቸውን ምንጮቻችን ገልጸዋል።

የፋሺስት አብይ ብልጽግና ቡድን አሰቃቂ ድርጊታቸው ከህግ አንፃርም ሆነ በታሪክ ከተጠያቂነት አያልፉም። 

Leave a Reply