• Tue. Nov 24th, 2026

የኦሮሞ ክነድና ጋሻ የሆነዉ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ኦነሰ) በምዕራብ ጉጂ ዞን በገላና እና ሱሮ ባርጉዳ ወረዳዎች ጠላትን በሞት እና በከባድ ማቁስል ቀጥቷል

May 16, 2024

ግንቦት 11 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

ሚያዚያ 18፣ 2024 በምዕራብ ጉጂ ዞን፣ ገላና ወረዳ፣ ጊዌ ቀበሌ ታፊቻ በተባለ ቦታ የኦሮሞን ሕዝብ ሲዘርፋ፣ በድብደባ ሲያሰቃዩ፣ የኦሮሞ ሴቶችን ሲደፍሩ እና በጭካኔ ሲገድሉ የነበሩትን የፋሺስት ብልፅግና ጦር ቡድንን እርም የሚያሰኝ ቅጣት ጀግናው ኦነሰ ሰጥቶዋቸዋል። ይኸውም ከ18 በላይ ወታደሮቹን በመግደል ከ15 በላይ ደግሞ ሊያገግሙ በማይችሉት ከባድ ቁስል ቀጥቷቸዋል። 

ቁስለኞቹም በዲላ ከተማ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደሚገኙ አቢኦ ማረጋገጥ ችሎዋል።

በዚሁ ቀን ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ላይ በሱሮ በርጉዳ ወረዳ፣ ሃራቱ ሃራ ቀበሌ ጀግናው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የብልጽግና ወታደሮች ላይ በወሰደዉ ድንገተኛ እርምጃ  ከከተማው አባርሮ በማስወጣት ሁለት የብልጽግና ሰላዮችንም ማርኳል።

ኦሮሚያ በጀግኖቹ ልጆችዋ እጅ ነች።

ድል ለኦሮሞ ህዝብ እና ለጭቁን ብሔር ብሔረሰቦች!

Leave a Reply