• Tue. Nov 24th, 2026

የፋሺስቱ ብልጽግና ሰራዊት በምዕራብ ወለጋና በምሥራቅ አርሲ ዞኖች ከባድ ዘረፋና እስራት በሰላማዊዉ የኦሮሞ ሕዝብ ላይ በስፋት እያካሄደ ይገኛል

May 19, 2024

ግንቦት 16፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

ሚያዚያ 9፣ 2024 በምዕራብ ወለጋ ዞን፣ ቆንዳላ ወረዳ፣ ባመሶ ከተማ አስተዳደር ውስጥ አሸባሪው የብልፅግና ሰራዊት ቡድን ኡስማን ሁንዴሳ የተባለን ግለሰብ በሬውን ሽጦ በሞተር ብስኪሌት ወደ ቤቱ በመመለስ ላይ እያለ ከሞተር ብስኪሌቱ  ላይ እንዲወርድ በማድረግ በእጁ የነበረውን 600.000 ብር እንደዘረፉት ምንጮቻችን ዘግበውልናል።

በሌላ ዜና ደግሞ በምሥራቅ አርሲ ዞን፣ ሄጤሳ ወረዳ፣ ጉቱቻ ቀበሌ ውስጥ ሚያዝያ 14፣ 2024 ከለሊቱ ዘጠኝ ሰዓት 10 ሰላማዊ ኦሮሞዎችን ይዘው በማሰር እያሰቃዩዋቸው መሆኑን ምንጮቻችን ለአቢኦ ተናግረዋል። ስማቸውም፦ 

  1. አብዱርሀማን ቃሲም፣ 
  2. ሰኢድ ጉሉማ፣ 
  3. ከማል አደም፣ 
  4. ኪያር ከማል፣ 
  5. ያሲን በሪሶ፣ 
  6. ዱሩ አቡ፣ 
  7. ማማ አቡ፣ 
  8. አቤ ፋጆ፣ 
  9. ዱሩ ከሊል፣ እና
  10. ሀሰን አቤ ይባላሉ።

ፋሺስት አብይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦

“የኦሮሞን ሕዝብ መዝረፍ፣ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ለማድረግ፣ መንበር የተሰጠው የፋሺስታዊ መንግስት መሪ።”

Leave a Reply