• Tue. Nov 24th, 2026

የፋሺስቱ ብልፅግና ቡድን በሰሜን ኦሮሚያ ወሎ ዞን፣ በባቴና ዳዋ ጫፋ ወረዳዎች ኦሮሞዎችን መዝረፍ፣ መደብደብ፣ አስሮ ማሰቃየት እና መግደል ከዚያም አልፎ በምሽት በክተማ ውስጥ የጦር መሳሪያ በመተኮስ ነዋሪዎችን እየረበሸ ይገኛል

Jun 2, 2024

ግንቦት 26፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)  

የፋሺት አብይ አህመድ ብልፅግና ቡድን ሰራዊት በሰሜን ኦሮሚያ ወሎ ዞን፣ በባቴ እና ዳዋ ጫፋ ወረዳዎች ሰላማዊና ንፁሃን ኦሮሞዎችን መዝረፍ፣ መደብደብ፣ አስሮ ማሰቃየት እንዲሁም ጭካኔ በተሞላበት ግድያም እየፈፀመ ይገኛል። ከዚህም በላይ ፖለቲካዊ ክስረቱን ለመቋቋም የኦሮሞ ወጣቶችን በገፍ በማፈስ የስለላ ስልጠናም እያደረግ እንደሚገኝ አቢኦ ከምንጮቹ እግኝቶዋል። 

ዳዋ ጫፋ ወረዳ፣ ቃሎ ከተማ

ሰላማዊ ህዝብን ማስፈራራት፣ በመዝረፍ፣ ማሰርና መግደል በማይደክመው የብልጽግና ስርዓት በሰሜን ወሎ ዳዋ ጫፋ ከተማ ይህንኑ ተግባር በማስፋት ህዝቡን በመጉዳት ላይ እንደሆነ አቢኦ በምንጮቹ አማካይነት አረጋግጧል።

የፋሺስት ብልፅግና ሰራዊት ግንቦት 6፣ 2024 ከምሽቱ 12 ሰዓት እስከ 4 ሰዓት የቃሎ ከተማ ነዋሪዎች ላይ ተኩስ ከፍቶ፣ ሕዝቡም ላይ ከባድ ድብደባና ዝርፊያም መፈፀሙ ተገልጿል። ይህንን የግፍ ወንጀል ለማድረግ ምክንያት የሰጡት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ወደ ከተማ ለመግባት በዝግጅት ላይ መሆኑን አውቀናል በማለትም እንደሆነ ምንጮቻችን ነግረውናል።  

የዚህ ጥቃትና እስራት ሰለባ ከሆኑት መካከል ስማቸውን ያገኘነው፦

  1. ኦቦ ኡማር ሃሴ ጥሬ ገንዘብን ጨምሮ፣ እስከ 200.000 ብር የሚገመት ንብረታቸውን ከዘረፋ በኋላም አስረው እያሰቃዩዋቸውም ይገኛሉ፣
  2. ኦቦ ማሜ በሺር፣
  3. አዴ ፋጡማ አስሌን ከ5 የቤተስብ አባልዎችዋ ጋር ልጆችዋንም ጨምሮ ስትታሰር፣ 
  4. የአቶ አሃመድ ሙሳ ባለቤት (ስምዋን ለጊዜው አላገኘንም) ከ4 ልጆችዋ ጋር ያለ ምንም ምክንያት መታሰራቸው ታውቋል።

ባቴ ወረዳ

ግንቦት 3፣ 2024 የስርዓቱ ታጣቂዎች  በጃልዳቲ ቀበሌ፣ ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ገለልተኛ የሆነውና አርሶ አደር አህመድ ሙዲን የሚባል ወጣትን ከቤቱ በማውጣት ሲገድሉት፣ ሂዴ ኡማር፣ አብዱ ሳዮ፣ አደም አብዱ፣ አህመድ ኢብርሃም፣ ሰይድ እብርሃምና አደም ኢብራሂም የሚባሉት ለእስር ሲዳረጉ፣በሌሎች ነዋሪዎች ላይም ድብደባ መፈጸሙ ተገልጿል።

”እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል!” እንዳለችው አህያና “አጥፍቼ ልጥፋ!” ብሎ የተነሳው የብልፅግና ቡድን በጦር ሜዳ ሊያሸንፈው ያልቻለውን ጀግናውን እና የአለም የጦርነት ህግን እና ደንብን ከእንቀፅ እስከ ዝርዝር ማብራሪያው ጠንቅቆ የሚያውቅና እያንዳንዱን እንቅስቃሴውንም የአለም አቀፍን መርሆ የተከተለ በመሆኑ የኦነሰ አለባበስና የተፈጥሮ ፀጉር ስታይሉን በአርተፊሻል ፀጉር ለውጠው ኦነሰ በመምሰል የኦሮሞ ሕዝብን በመዝረፍ፣ ሴቶችን በመድፈር እና አሰቃቂ ግድያንም በመፈፀም ላይ እንደሚገኙ ለአቢኦ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል። 

ይህንንም እኩይ ተግባር የሚፈፅሙት ለስለላ ተግባር ስልጠና የተሰጣቸውም ሰዎች እንደሆነ ተደርሶባቸዋል። ለዚህም ተግባር ቄሮዎችን ከእምነት ቤት፣ ከት/ቤት፣ ከፑል ቤት እና ከስራ ቦታ ለግዳጅ ትፈለጋላችሁ በማለት ከያዘ በኋላ ስልጠና የሰጠው የባቴ ከተማ ከንቲባ የሆነው ሰኢድ መሐመድ ሰኢድ ኡሩንጉ መሆኑንም ከአቢኦ ምንጭ ተገኝቷል።

በባቴ ከተማ ውስጥ የስለላ ሥልጠና በከንቲባ ሰኢድ መሐመድ ሰኢድ ኡሩንጉ የተሰጣቸውም፦

  1. ሰኢድ አደም፣
  2. አቡበከር ሁሴን፣
  3. ካሊድ ኪቹ፣
  4. ሀምዛ አሊ፣
  5. መሐመድ አደም፣
  6. ኤልሀም መሀመድ፣
  7. አብዱ መሀመድ፣
  8. ሜርኩሪ ሀኡ፣
  9. መሀመድ አብዱ እና
  10. ሙስጤ Dheቢሳ መሆናቸው ታውቋል።

ይህንን እኩይ የስለላ ስልጠና ተቃውመው ‘እኛ በሕዝባችን ላይ የጠላትነትን ሥራ አንሰራም። ነገ በህግና በታሪክ የሚያስጠይቀንን ድርጊት አንፈፅምም።” በማለት እምቢታችውን የገለፁት በአሁኑ ወቅት ታሰረው እየተሰቃዩ መሆናቸውንም የአካባቢው ሕዝብ ገልጾልናል። ከእነሱም መሃል ስማቸው የደረሰን፦

  1. ሰኢድ አደም፣
  2. አቡበከር ሁሴን፣
  3. ካሊድ ኪቹ እና
  4. ሀምዛ አሊ ናቸው።

ይህንን የብልፅግና አሸባሪ ስርዓት ለመገርሰስ የኦሮሞ ሕዝብ በአንድነት መቆም ይገባዋል።

Leave a Reply