• Wed. Nov 25th, 2026

የሙዚቃ አቀንቃኙ አኑማ ተክሉ በቡራዩ ከተማ በብልጽግና ጦር ቡድን ተይዞ መታሰሩ ተገለጸ

Jun 11, 2024

ሰኔ 10፣ 2024 አራት ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO) 

በማህበረሰቡ ውስጥ እንደ ዓይን ብሌን የሚታዩትንና ተወዳጅ የሆኑትን ግለሰቦች አድኖ ይዞ በማሰርና በመግደል የሚታወቀው ፋስሽቱ የብልጽግና ቡድን ጦር በቅርቡ “ኢሾ ጉርባ” በሚል ነጠላ ዘፈኑ ተወዳጅነት ያተረፈው አርቲስት አኑማ ተክሉን ከአራት ጓደኞቹ ጋር ሚያዝያ 27፣ 2024 ከሚኖርበት ቡራዩ ከተማ ተይዞ መታሰሩ ታውቋል።

አርቲስቱ በብልፅግና ሰራዊት የተያዘው ከአራት ጓደኞቹ ጋር ቡራዩ ከተማ መንገድ ላይ እየሄዱ ሳለ ሲሆን፣ ወደ ከተማው አስተዳደር  ፓሊስ ጣቢያም ወስደው አስርዋቸዋል። ከታሰሩትም ጓደኞቹ ስሙን አቢኦ ያገኘው ፍራኦል የሚባለውን ብቻ ነው።  

ከትንሽ ቀናትን በኋላ ግንቦት 2፣ 2024 አርቲስት አኑማን ወደ ፊንፊኔ፣ ሜክሲኮ ወደሚገኘው የፌዴራል ፍርድቤት ተወስዶም እንደነበረ እና ፍርድ ቤቱም የዋስትና መብቱ እንዲጠበቅለት የወሰነ ቢሆንም የፋሺስቱ ብልፅግና ስርዓት ግን የፍርድቤቱን ትዕዛዝ በመጣስ ወደ እስር ቤት በመመለስ እያሰቃዩት መሆኑን ጓደኞቹ ለአቢኦ ገልፀዋል።

እስካሁን ድረስ ቤተሰቡም፣ ዘመዶቹም ሆኑ ጓደኞቹ ታሳሪውን ድምፃዊው አኑማ ተክሉን የመጠየቅ እድል በመነፈጋቸው ምክንያት ጤንነቱም ምን ሁኔታ ላይ እንዳለ አለማወቃቸውን የአቢኦ ምንጮች ተናግረዋል።

ፋሺስት አብይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦

“የኦሮሞን ሕዝብ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ለማድረግ፣ መንበር የተሰጠው የፋሺስታዊ መንግስት መሪ።”

Leave a Reply