ሰኔ 13፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
ለማጥፋት የቆርጠ ሀይል ሌላውን ይዞ ከመጥፋት አይመለስም እንደሚባለው ሁሉ የማፍያው ብልፅግና ቡድን የስልጣን ዘመኑ የመጨረሻ ደረጃ መድረሱን በመገንዘብ ሰላማዊውን የኦሮሞ ህዝብ ባገኘው እድል ሁሉ እያሰረ፣ እያሰቃየ እና ንብረቱን እየዘረፈ ይገኛል።
ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን፣ ጂማ ራሬ እና ጂማ ገነቲ ወረዳዎች
ጂማ ራሬ ወረዳ
በወረዳው በአንድ ቀን ማለትም ግንቦት 6፣ 2024 እራት ንፁሃን ኦሮሞዎችን አባትና ልጅንም ጨምር ካሰሩ በኋላ 16 በሬዎችንም ከሁለት ቤተሰቦች ቤት ዘርፈዋል። ስማቸውም፦
- ኦቦ ደሳሌ ጎበናን ከሀሮ ጉታ ቀበሌ ካሰሩዋቸው በኋላ 9 በሬዎቻቸምንም ዘርፈው ሄደዋል
- ከአንድ ቤተሰብ አባት እና ልጅንም ሰማቸውም ኦቦ አዲሱ አየላ እና ኦቦ መስፍን አዲሱ ከበዳ ወርቄ ቀበሌ አስረው እያሰቃዩዋቸው ነው ።
- ኦቦ ደጀኔ ኦላና ከቄቁ ቃሉ ቀበሌ ብካሰርዋቸው በኋላም 7 በሬዎችን ዘርፈው ሄደዋል።
ጂማ ገነቲ ወረዳ
ግንቦት 4፣ 2024 ከሁንዴ ጉዲና ቀበሌ እና ከሚያዚያ 28፣ 2024 ጀምሮ ለሁለት ሳምንት ያህል ከአዲ ሌቃ ቱሉ ጫሊ ቀበሌ ውስጥ ብዙ ሰዎች በኦሮሞነታቸው ብቻ ተይዘው በእስር ቤት እየተሰቃዩ እንደሚገኙ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ገልጸዋል።
ከታሳሪዎቹ እና በአሁኑ ግዜም ስቃይ እየደረሰባቸው ካሉት ስማቸውን ያገኘነው፦
ከሁንዴ ጉዲና ቀበሌ
- ኦቦ ሁንዱማ ጋንፉሬ፣
- ኦቦ ታደሳ ቦዮሳ፣
- ኦቦ ነጋሳ ዳንጉል፣
- ኦቦ ደፋሩ ቤኛ፣
- ኦቦ ጌቱ ታከላ፣
- ኦቦ ዳዌ በቀላ፣
- ኦቦ ጌቱ ባሻ፣
- ኦቦ ነገሮ ጋሉ፣
- ኦቦ ምሬሳ ዊርቱ፣
- ኦቦ ተመስጌን ተረፋ እና
- ኦቦ ነጋሳ ባሻ ሲሆኑ፤
ከአዲ ሌቃ ቱሉ ጫሊ ቀበሌ
- ኦቦ አዱኛ ረጋሳ፣
- አዴ Dhiበሺ ክትሊ፣
- መምህር ቦኬ ከበዳ ከባለቤቱ ጋር፣
- አዴ ፋንቱ፣
- ኦቦ ጉዲና Dheeሬሳ፣
- ኦቦ ጣሶ ቀልቤሳ፤
- ኦቦ ቂጣታ ረጋሳ፣
- ኦቦ ኤቢሳ ፍቃዱ፣
- ኦቦ ጌትነት ማሞ፣
- ኦቦ ወንዲሙ ሂንኮሳ፣
- አዴ ፊጡማ ጊሎ፣
- ኦቦ ዮሴፍ ታመነ ናቸው።
ምስራቅ ወለጋ ዞን፣ ነቀምቴ ከተማ
በነቀምቴ ከተማ አስተዳደር ሰላማዊ ኦሮሞዎችን በጅምላ ማሰር በማፍያው ብልፅግና ጦር ቡድን ተጠናክሮ በመቀጠሉ ብዙዎቹ የከተማዋ ባለሀብቶች እና ሰላማዊ ሰዎች መምህሮችንም ጨምሮ ተይዘው በ05 እና 07 ቀበሌዎች እና በኩምሳ ሞረዳ እስር ቤቶች ውስጥ በመሰቃየት ላይ ይገኛሉ።
ከታሰሩትም ስማቸውን ያገኘነው፦
- ኦቦ ደሳሌ ደበሊ ባለሃብት እና
- ኦቦ ሀይሌ ዬሱስ ቀነኒ ባለሃብት የሚባሉት በነቀምቴ ከተማ 05 ቀበሌ ውስጥ የታስሩ ሲሆን፣ ከዚህ በፊትም ብዙ ገንዘብ ከእጃቸው ወስደው እንደለቀቋቸው አቢኦ ከምንጮቹ አግኝቶዋል።
- መምህር አብደላ የሚባሉት ደግሞ በኩምሳ ሞረዳ ውስጥ እያሰቃዩት እንደሆነ የዓይን እማኞች ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ተናገሩ።
ፋሺስት አብይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦
“የኦሮሞን ሕዝብ መዝረፍ፣ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ለማድረግ፣ መንበር የተሰጠው የፋሺስታዊ መንግስት መሪ።”
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያወጀው የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ ጦርነት የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት እና የሀገር ባለቤትነት እስኪረጋገጥ ድረስ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
